አስሩ የደስታ መሰረቶች
1. ደስታ ያለው በአላህ እጅ ብቻ መሆኑን ማመን፦
- እሱ ነው ልቦችን በተውሒድ፣ በኢማን፣ በሱና፣ በዒልም የሚያሰፋው፣
- ደስታ የአላህ ፍጥረት ነው = ከአላህ እንጂ ከማንም አይጠየቅም።
2. ደስታ ከልብ ውስጥ እንጂ ሌላ ቦታ አይደለም ያለው፦
- ደስታ የሚገኘው በምግብ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በመጠጥ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በመልበስ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በአዱኒያ ጌጦች አይደለም፣
- ደስታ እና እርካታ ከልብ ውስጥ ነው ያለው።
3. ወንጀሎችን ሀጢያቶችን እና ስህተቶችን መቀነስ፣ መተው፦
- ወንጀል በቀነሰ ቁጥር = ደስታ፣ እርካታና እረፍት ይጨምራል።
- ወንጀል ሸክም ነው፣ ጨለማ ነው፣ ጥበት ነው፣ ጭንቀት ነው።
4. በሰዎች መካከል በመልካም መወሳት፦
- የሙእሚን ሰው ፈጣን ብስራት ነው፣
- የሰዎችን መልካም ዱዓ ያስገኛል፣
- የሰው ልጅ ሁለተኛ እድሜ ነው።
5. ከችግር በኋላ ድሎት እንዳለ እርግጠኛ መሆን፦
- አላህ ችግርን ያለ መፍትሄ አልፈጠረውም።
- ሀዘንና ትካዜንም ያለ ግልግል አልሰራውም።
- መከራንም ያለ መፍትሄ አልተወውም።
6.ግልግል ከችግር ጋር እንደሚመጣ ማወቅ፣
- ችግር፣ ሀሳብ፣ ትካዜ በተከሰተ ቁጥር = የአላህ እዝነት እና ግልግል ይመጣል።
7. አላህ አንድን ችግር ሲያመጣ ሁለት መውጫ ያደረገ መሆኑን ማወቅ።
8. ትርፍ ጊዜን በኸይር እና በዒባዳ ላይ ማሳለፍ፦
- ስራ ሲያልቅና ሲጠናቀቅ ወደ ዒባዳ መግባት፣
- ስራ ፈቶ ያለ ምንም ነገር ጊዜን አለማባከን።
9. ዒባዳ ከደስታ ማግኛ ሰበቦች አንዱ ነው።
- አላህን ወደ መታዘዝ መግባት፣
- ዒባዳ በጨመረ ቁጥር = የልብ ደስታና እርጋታ ይጨምራል።
- ሶላት፣ እውቀት፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል፣ ዝምድና መቀጠል ... ኸይር ነገር በጨመረ ቁጥር = የልብ ኢማንና ደስታ ይጨምራል።
- እስከ ሞት ድረስ በዒባዳ ላይ መዘውተር።
- የጭንቀት መድሃኒቱ = ዚክር ነው። ወንጀልን መተው።
10. ስራን ባጠቃላይ ለአላህ ብቻ ማጥራት
- ስራን ለአላህ ማጥራት ፣ ነው ነጃ መውጣት።
• ደስታ ከፈለክ እነዚህን አስሮቹን ነገሮች ተጠባባቅ። ወላሁ ተዓላ አዕለም።
~
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲላህ ባሙሳ
ኡሰሉ ሰ፞ዓደቲል ዐሸራህ ኪታብ ተመልከት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/MOhamedAljawi
1. ደስታ ያለው በአላህ እጅ ብቻ መሆኑን ማመን፦
- እሱ ነው ልቦችን በተውሒድ፣ በኢማን፣ በሱና፣ በዒልም የሚያሰፋው፣
- ደስታ የአላህ ፍጥረት ነው = ከአላህ እንጂ ከማንም አይጠየቅም።
2. ደስታ ከልብ ውስጥ እንጂ ሌላ ቦታ አይደለም ያለው፦
- ደስታ የሚገኘው በምግብ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በመጠጥ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በመልበስ አይደለም፣
- ደስታ የሚገኘው በአዱኒያ ጌጦች አይደለም፣
- ደስታ እና እርካታ ከልብ ውስጥ ነው ያለው።
3. ወንጀሎችን ሀጢያቶችን እና ስህተቶችን መቀነስ፣ መተው፦
- ወንጀል በቀነሰ ቁጥር = ደስታ፣ እርካታና እረፍት ይጨምራል።
- ወንጀል ሸክም ነው፣ ጨለማ ነው፣ ጥበት ነው፣ ጭንቀት ነው።
4. በሰዎች መካከል በመልካም መወሳት፦
- የሙእሚን ሰው ፈጣን ብስራት ነው፣
- የሰዎችን መልካም ዱዓ ያስገኛል፣
- የሰው ልጅ ሁለተኛ እድሜ ነው።
5. ከችግር በኋላ ድሎት እንዳለ እርግጠኛ መሆን፦
- አላህ ችግርን ያለ መፍትሄ አልፈጠረውም።
- ሀዘንና ትካዜንም ያለ ግልግል አልሰራውም።
- መከራንም ያለ መፍትሄ አልተወውም።
6.ግልግል ከችግር ጋር እንደሚመጣ ማወቅ፣
- ችግር፣ ሀሳብ፣ ትካዜ በተከሰተ ቁጥር = የአላህ እዝነት እና ግልግል ይመጣል።
7. አላህ አንድን ችግር ሲያመጣ ሁለት መውጫ ያደረገ መሆኑን ማወቅ።
8. ትርፍ ጊዜን በኸይር እና በዒባዳ ላይ ማሳለፍ፦
- ስራ ሲያልቅና ሲጠናቀቅ ወደ ዒባዳ መግባት፣
- ስራ ፈቶ ያለ ምንም ነገር ጊዜን አለማባከን።
9. ዒባዳ ከደስታ ማግኛ ሰበቦች አንዱ ነው።
- አላህን ወደ መታዘዝ መግባት፣
- ዒባዳ በጨመረ ቁጥር = የልብ ደስታና እርጋታ ይጨምራል።
- ሶላት፣ እውቀት፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል፣ ዝምድና መቀጠል ... ኸይር ነገር በጨመረ ቁጥር = የልብ ኢማንና ደስታ ይጨምራል።
- እስከ ሞት ድረስ በዒባዳ ላይ መዘውተር።
- የጭንቀት መድሃኒቱ = ዚክር ነው። ወንጀልን መተው።
10. ስራን ባጠቃላይ ለአላህ ብቻ ማጥራት
- ስራን ለአላህ ማጥራት ፣ ነው ነጃ መውጣት።
• ደስታ ከፈለክ እነዚህን አስሮቹን ነገሮች ተጠባባቅ። ወላሁ ተዓላ አዕለም።
~
የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲላህ ባሙሳ
ኡሰሉ ሰ፞ዓደቲል ዐሸራህ ኪታብ ተመልከት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/MOhamedAljawi