╔══════════════════════╗
🌟 #የሙስሊም_ወላጆች_ምሬት_ከጊዜ
#ወደጊዜ_መጨመር
╚══════════════════════╝
ብዙ ወላጆች የሚነቁትና የሚባንኑት ልጆቻቸው ጉዳት ላይ ከወደቁና መዘዙ ከተረፋቸው በኋላ ነው፡፡በተለይ ያሁኑ ወላጆች በቢዝነስና በዱንያዊ ጉዳዮች ስለሚጨናነቁ ለልጆቻቸው ተገቢውን ትኩረት አይሰጡም፡፡ ከዚህም የተነሳ አዳጊ ልጆች ምንም እንኳን ወላጆች አጠገብ ሲሆኑ ጨዋ ቢመስሉም ዳሩ ግን ደጅ ብዙ ሱስና ፀያፍ ነገሮችን መልመዱንና ማዘውተሩን ተያይዘውታል፡፡በተለይ አዳጊ ሴት ልጆች ለበርካታ ፈተናዎች እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡ ከሰፈር ጎረምሳና ምራቁን የዋጠ ዘልዛላ ወንድ አንስቶ፣በትምህርት ቤት፣በመጓጓዣ ላይ፣ የወሲብ ደላሎች ውትወታ ሰለባ መሆን፣ በየመዝናኛ ስፍራው ለተለያዩ ወሲባዊ ትንኮሳዎች፣ ወዘተ የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡ታዲያ በዚህ ላይ የወላጆች እንዝላልነት ከታከለበት መዘዙን አያድርስ ያስብለዋል፡፡
ነገሮች እኛ ከምንገምታቸው በላይ በፍጥነት ይቀናጃሉ፡፡በተለይ በሱስና በብልግናው መስክ ሁሉ ክስተት ቅፅበታዊ ሆኗል ማለት ይችላል፡፡
#ለምሳሌ በአንድ አጋጣሚ ብቻ ከሱሰኛ ጓደኛዋ ጋር ወደጫት መቃሚያና ሺሻ ቤት ጎራ ያለች አንዲት ያልተነካካች ሴት በአንድ ጊዜ ሙዷ ሁሉ ተቀያይሮ ይህቺ ምንም አልተነካችም የምትባለው ልጅ ከሌሎች ጋር ለመመሳሰል ስትል ዓይን አውጣ ሆና ልትገኝ ትችላለች፡፡አንዴ እዚያ ከገባች በኋላ የፈለገችውን ያህል ጨዋና ለቦታውም እንግዳ ብትሆን እንኳን ግን ፋራ ላለመባል ስትል ያቺ ቀድማ በወሲብ አክቲቭ የሆነችው ጓደኛዋ የምታዳርገውን ነገር ሁሉ ታደርጋለች፡፡በዚያኑ ዕለት ከጓደኛዋ ጋር ለመመሳል ስትል ጓደኛዋ ከወንድ ጋር ከወጣች እንግዳይቷም አንዳችም ሳታንገራግር ከወንድ ጋር ትወጣለች፡፡
ታዲያ ይህች ልጅ ይህንን ሁሉ ጉድ የምታደርገው ግንዛቤ ኖሯትና አውቃ ላይሆን ድንገት ያላዩት ሀገር ይናፍቃል እንደሚባለው ሄዳ በዚያው ለዝሙት ተጋልጣ ነው፡፡ ከዚያም የሰማይን ያህል እሩቅ ለሚመስለው ያልተፈለገ እርግዝና ትጋለጣለች፡፡ እርሷ የምትባንነው ምናልባትም ሆዷ ከፍ ሲል ይሆናል፡፡ታዲያ ይህ ሁሉ ጉድ ወላጆች ዘንድ የሚደርሰው የዚህን ጊዜ ነው፡፡የዚህን ጊዜ ወላጆች የልጆቻቸውን ገመና ሳይሆን መዘዙን ነው የሚያዩት፡፡ይህ እየተለመደ በመምጣቱም በርካታ ወላጆች ስሞታቸውን እያሰሙና ምሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ፡፡
✏️✏️በተደጋጋሚ ከሚሰሙ የወላጆች ምሬት መካከልም
☞ልጄ እኮ ተበላሸች
☞ልጄ እኮ እንደዚህ ሆና ሱሰኛ ሆነችብ
☞ልጄ እኮ ለቅሶ ታበዛለች፤ ምን እንዳስነኳትም አላውቅም»፣
☞«ልጄ እንደዚህ ዓይነት መዘዝ አመጣችብኝ፣
☞«ልጄ እንደዚህ ዓይነት አዲስ ጠባይ አመጣች,, የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ሳይቃጠል በቅጠል እንደሚባለው አንዴ የአዳጊ ልጆች ሕይወት ከተበላሸ በኋላ የወላጆች ወይታ የአዞ እንባ ከመሆን አይዘልም፡፡
ሴት ልጅ አንዴ የህይወት መስመሯ ከተበላሸ ሳይክሪስት ጋር ብትሄድ..ሩቃ እያለች ጂን ነዉ እየተባለ ቁርአን ቢቀራባት .ሀገር ከተማ ብትቀይር አንዴ መስመር ከሳተች ሳተች ነዉ፡፡ የባቡር ሀዲድ ሀዲዱ መስመሩን ከሳተ ገደል እንደሚገባ ሴትም ልጅ ህይወቷ ከተባላሸ እንደባቡሩ ነዉ የመጨረሻ ህይወቷ፡፡
«አሳዳጊ የበደለው ልጅ, እንደሚባለው ልጅህ ላይ አስቀድመህ የወላጅነት አሻራ ካላኖርክ፣ የአላህን ተቆጣጣሪነት ካላስተማርከው ልጁ በልብ ፅላቱ ላይ የሚያፅፈው የጓደኛውን ምክር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ በልጆች ልብ ላይ የወላጆች አሻራና የአምላካቸው ትዕዛዝ በልባቸው ፅላት ላይ ሳይፃፍ ልጆች በየሄዱበት ሁሉ በማንም የሚነዱ ጭፍን ተከታዮች ይሆናሉ፡፡
ይህ የወላጆች ምሬትና ስሞታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ችግሩም ሥር እየሰደደ መጥቷል፡፡ ቢያንስ በየቤቱ በሴት ልጁ ወይ በወንድ ልጁ የሚያማርር ቤተሰብ በየሁላችንም ቤት አለ፡፡ችግሩ የብዙዎችን በር ያንኳኳ ይመስላል፡፡ችግሩን የበለጠ ያባባሰው ደግሞ የልጆቹ ዕድሜ ገና ለጋ መሆኑና ምንም አያውቁም የሚባሉ አዳጊዎች ተበላሽተው መገኘታቸው ነው፡፡በተለይ በርካታ ወላጆች አዳጊ ሴት ልጆቻቸው በሚያመጡት ዝሙት ክብራቸውና ሞራላቸው እየተነካ ይገኛል፡፡ ይህም ዝሙትና ሌሎችም ሱሶች በሙስሊሙ መካከል መስንራፋቱንና ሥር መስደዱን ይጠቁማል፡፡
=======\=======\======\======
✍ቤተሰብ ሆይ ለልጅህ የሱሀቦችን ገደል እያስተማርክ አሳድጋቸዉ፡፡የ15,000 ስልክ ገዝተህ ቲክቶክ ላይ ተዘፍዝፈዉ ከሚዉሉ...አሁን ላይ መፅሀፍ ዋጋዉ ስለጨመረ 50መፅሀፍ ገዝተህ እዉቀት ብትሰጧቸዉ መጥፎና ጥሩዉን እንዲለዩ ማድረጉ ይሻላል፡፡
አንድ ሌባ የትልቅ ሰዉ ስልክ መስረቅ ፈልጎ ሲከታተል ስልካቸዉ ጠራ...ሌባዉ ስልካቸዉን ለመዉሰድ ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት...ፋዘር ስልኩህ እየጮሀ ነዉ አላቸዉ
...እሳቸዉ ግን ይጩህ ግድ የለም ቡሀላ እኔ ከምጮህ ስልኩ አሁን ቢጮህ ይሻላል አሉት፡፡
ቤተሰብ የኔ ልጅ ትለያለች ብለዉ ሽንጣቸዉን ገትረዉ መከራከሩን ያቁሙ..አስተዳደግ ላይ ሴት ልጅህን ሚስጥረኛህ እስከምትሆን ድረስ ቅረባት አባት ልጅህ እህትህ አድርገህ ያዛት...ወንድምም ለእህትህ ቀርበህ ትክክለኛ ወንድም ሁናት፡፡
በራሴ አመለካከት ከእናት በላይ ሴትን ልጅ ማስተካከል የሚችቸዉ አባት ነዉ ብየ አስባለሁ፡፡ለምን ብዙ ሴቶች እየተሸወዱ በአጂነብይ ወጥመድ የገቡት ከወንድ ልጅ ያጡት የአባት ፍቅር ወይም የወንድም እንክብካቤ መንስኤ ነዉ፡፡ቦይ ፍሬንድ እሷን ለማበላሸት አዳማጭ ሰሚ ያጣችዉን ወንድ አባት ይተካና ህይወቷን አበላሽቶ እንደመኪና ጥቁር ዘይት በየአቅጣጫዉ ይደፋታል፡፡
ሴቶች ሆይ የመኪና ጥቁር ዘይት ጠቁሮ ከመዳፋቱ በፊት መጀመሪያ ላይ ታሽጎ ከፋብሪካ ሲወጣ የሚያምር መልክ የታሸገ ነበር ግን በሂደት መኪና ዉስጥ ገብቶ ሲሰራ ሲታዘዝ የመጨረሻ እድሉ ጥቁር ሁኖ አስጠልቶ ቆሻሻ ቦታ መደፋት ሆነ እጣዉ፡፡ አንቺም በሀራም ፍቅር በወንዱ እንደፈለገ በየካፌዉ በየፔንሲዩኑ የወደደሽ መስሎሽ ሲያዞርሽ ኑሮ በርገር ፒዛ በልተሽ ቡሀላ አግልግሎትሽ ሲያልቅ ኤክስፓየርድ ስትሆኝ እሱ አዲስ ሞዴል ይዞ በመጨረሻም እንደ መኪና ጥቁር ዘይት ቆሻሻ ቦታ እንዳትደፊ ተጠንቀቂ...አንቺ ሶብረኛ አላህን ፈሪ ከሆንሽ ትዳርና እንቅልፍ በራሷ ጊዜ ይመጣል፡፡
✨ #ብዙ ሴቶች ትዳር እየተላለፋቸዉ እየዘለላቸዉ ያለዉ ትዳር ፈላጊዉ በዉጭ በሚያቃት ቤተሰብ ሲያስጠይቅ ቤተሰብ እንደሚያቃት ደግሞ ልጄ ለእሱ አመጥነዉም የኔ ልጅ እኮ እንዲህ ናት ብለዉ ይከለክላሉ፡፡አረ ወገን አላህ ይድረስልን ሴትልጅና ቤተሰብ ሳይተዋወቅ በማስመሰል ተደባብቆ አንድ ላይ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡
ይቅርታ አርጉልኝና ከሴቶች የምታስቀኝ ቃል አለች...ወንድ ልጅ ለትዳር ገና መስመር ሊጀምር ሲል የሚላት ቃል ኮስተር ብለዉ እኔ እንደሌሎች ሴቶች እንዳልመስልህ🙄የሚሏት ቃል አለች...በጣም የምትአጅበኝ የምታስቀኝ ቃል ነች ከምር ለምን እንዲህ የምትል ሴት እሷን ጨምሮ አንድ ስለሚሆኑ ሳክስ ነዉ ወዳጄ
#በቀጣይ ክፍል
በአዲስ አበባ ታዋቂ የግል ትቤት
9ሴቶች 11ወንዶች በትምህርት ቤት ፓርቲ አዘጋጅተዉ ምን ሲሰሩ አደሩ?ወላጅስ?ከዛስ ምን ተፈጠረ የሚለዉን የሚያሳፍር እዉነተኛ ታሪክ አቀርባለሁ ..እየተከታተላችሁ ሼር እያደረጋችሁ ስለሆነ አላህ ምንዳችሁን እጥፍ ድርብ ያርግልኝ
#ምዕራፍ ➎...ይቀጥላል
join👇👇👇
t.me/IslamisUniverstiy_public_group
t.me/IslamisUniverstiy_public_group