Postlar filtri


ISLAMIC MINDset dan repost
አላህን ሳንጠይቀው ብዙ ነገር ሰጥቶናል። እንዲሁም በህይወት ስንኖር ጥቂት ነገሮችን እንድንፈፅም ግዴታ አድርጎብናል። ግዴታዎቻችንን በአላህ ፍቃድ ከተወጣናቸው ቀን በቀን እናመስግን። አሁን ካለንበት ደረጃ በላይ እንዲሰጠን ከፈለግን, ግዴታ ካደረገብን ነገሮች በተጨማሪ ወደን እና ፈቅደን ኢባዳ እናድርግ። ..ነገር ግን ግዴታ ያደረገብንን አላህ በፈለገው መልኩ ሳንወጣ ትርፍ የምንጠይቅው ከሆነ ከውስጣችን ጋር ተጋጭተናል እና ራሳችንን እንመልከት፤ ግዴታ ያደረገብንን ሳንወጣ ተጨማሪ አልያም ትርፍ የሆነን ነገር አላህ እየሰጠን ከሆነ ትልቅ የሆነ ፈተና ውስጥ ሰለሆን ሳናባክን ለሚገባው የሚገባውን ነገር ብቻ እናድርግ። ወደ አላህም እንቃረብ🙏

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
አላህ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ሊያረጋጋህ ሲፈልግ በዱንያ ላይ ችግሮችን በችግር ላይ ደራርቦ ይሰጥህና ምን እንደምታደርግ ይመለከተሃል። ያኔ አስተንታኝ ከሆንክ በትግዕስት ወደሱ መሸሽን ትመርጣለህ!..የዚህም ምሳሌው ወርቅ ወርቅነቱ ጥርት እንዲል ዘንድ በእሳት እንደሚቀልጠው እና ለብቻው ዋጋ እንዳለው እንደሚለየው ማለት ነው!

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
ልባችን ከመድረቁ የተነሳ አላህ ምንም የማያደርግ ይመስለናል። ጨካኞች ሁሌም በድሎት ላይ እንደበደሉ አይኖሩም። ተበዳዮችም ሁሌ እንደተበደሉ አይቀጥሉም። ምክንያቱም በዚች አለም ሆነ በቀጣይቱ አለም በፍርድ የማያዳላው አላህ(ሱ.ወ) ስላለ!
#join #like #shrae




ISLAMIC MINDset dan repost
አሁን አሁን ላይ ሲታሰብ ምክንያታችን አፈንግጦ የወጣ ይመስላል። ወረርሽኝ ሲነሳ በዚህ ምክንያት ነው ብለን ትንታኔ ለመስጠት እንጂ ወደ አላህ ለመመለስ ስንጣደፍ አንታይም። ጦርነት መጣ ሲባል እንደለመደብን ለትንታኔ እንሯሯጣለን። የጎርፍ አደጋ ተነሳ ሲባል እንደለመደብን የለመደብንን እንጂ አላህ እያስጠነቀቀን እንደሆነ አናስተነትንም። ከዚህም ባስ ብሎ የእሳተ ጎመራ እና የመሬት መንቀጥቀጥን አብሮ አምጥቶብናል። እንደለመዱት ምክንያት ከሚተነትኑ ሳይሆኑ ካሉበት የወንጀል ጫካ ለመውጣት ለተውበት ከሚሯሯጡ ያድርገን🤲

ISLAMINDSET.




ISLAMIC MINDset dan repost
እሁድ ከቀኑ 8:30 በዩትዩብ ቻናላችን ይጠብቁን።
#subscribe #share #like


ISLAMIC MINDset dan repost
እጅህን አንስተህ የምትፈልገውን ጠይቀህ ምላሽ ካልሰጠህ፤ አልሰጠኝም ብለህ ከመበሳጨት ይልቅ, አላህ ሊሰጥህ የፈለገውን ለመቀበል መዘጋጀት ጀምር። ምክንያቱም አንተ ፈልገህ የጠየከውን ካልሰጠህ እሱ የፈለገው ይበልጣልና ..!

ISLAMINDSET.




ISLAMIC MINDset dan repost
ሐሙስ ከቁኑ 8:30 በዩትዩብ ቻናላችን ፕሮግራሙ እንዳያመልጦዎ!


ISLAMIC MINDset dan repost
እጅህን አንስተህ አላህን ከልብህ ስትጠይቀው ምላሽ ሰጥቶኻል። ነገር ግን ምላሹ አንተ እንደፈለከው ሳይሆን አላህ ላንተ በዱንያም በአኺራም እንዲጠቅምህ ዘንድ በፈለገው መልኩ ነው የሚመልስልህ!..ይህንን ሁሌ እጅህን ስታነሳ አስታውስ!

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
አላህ ለባሮቹ ምን ያህል እንደሚያዝን በተጨባጭ ብናውቅ ኖሮ የኛን አጉል ምኞት ትተን የሱን ዉሳኔ ብቻ እንቀበል ነበር!😔

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
ችግሮችን አላህ ካደራረበብህ ትልቅ ለሆነ ጥሩ ነገር እያዘጋጀህ ነውና ታግሰህ የአላህን ስራ ግዜ ሰጥተህ ተመልከት...የሚገርምን ጥበብ ታገኝበታለህ!

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
ምላስህ ዚክር ካበዛች አላህ ለጥሩ ነገር እያዘጋጀህ ነው። በተቃራኒው ምላስህ ዚክር ማድረግ ከከበዳት አደጋ ውስጥ መሆን አመላካች ነውና ዚክር ለማለት ታገል። አላህም እንዲያቀልልህ ዱዓ አድርግ!🤲

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
አሳቢ እና አስተንታኝ ሰው አላህ ያሰዘዘውን ነገር አሳምሮ ሰርቶ "አላህ ስራዬን ተቀብሎ ይምረኝ ይሆን!" ብሎ ይጨነቃል ፤ ማሰብ እና ማስተንተን ተቅቶት የሚኖር ሰው አላህ የከለከለውን ነገር ያለ ጭንቅ በግዴለሽ እየተገበረ " ችግር የለውም አላህ ይምረኛል! " ብሎ በአጉል ተስፋ የሚኖር ነው!

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
የጁሙዓ ቀንን በጤና በኢማን ካደረሰን በርግጥም አላህን እንድንጠይቀው ትልቅ እድል እየሰጠን ነው። በጁሙዓ ቀን ጥቂት ሰዓት አለች የምንፈልገውን ብንጠይቀው የሚመልስበት ... ልባቸው ዝንጉ ከሆኑት አንሁን ! ዱዓ እናድርግ በተለይም ከአሱር እስከ መግሪብ ባሉት ሰዓታቶች🤲

...የISLAMINDSET ቤተሰቦችንም አትርሱ!

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
ሐሙስ ከምሽቱ 3:15 በISILAMNDSET እንገናኝ..ለ1:30 ያህል በቲክቶክ ቆይታ እናደርጋለን ኢንሻአላህ!
ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
ወደዚች ህይወት ስንቀላቀል ምንም ሳንይዝ መጣን፤ በዚች ህይወት ላይ ስንኖር ሁሉም ነገር የኛ እንዲሆን ከታች ላይ ኳተን፤ ከዚች ህይወት ስንወጣ ግን የሰበሰብነው ሁሉ ጥለን እንሄዳለን።

ሁላችንም በዚህ ዑደት እናልፋለን!.. ነገር ግን ብልህ ማለት በዚች ህይወት ሲኖር በብልጠት የማይታለፍበትን ግዜ ቀድሞ ያስታውሳል።ከዚያም ባለው ነገር ሁሉ በህይወት ሲኖር ሙሉ ለሙሉ አራግፎ ሞት ሳይለያየው ቀድሞ ካለው ነገር ጋር ይለያያል። ... ያኔ ዳግም እንዳዲስ ሰዎች ሲባነኑ ከእንቅልፋቸው ይህ ሰውዬ ከተለያየው ንብረቱ ጋር በመገናኘት ነፃ ሊወጣ ዘንድ ሰበብ ይሆንለታል።

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
"
የቀን ምግቡ የተሟላለት በቤቱ ውስጥ, እንዲሁም በሰውነቱ ጤነኛ የሆነ ሰው, ዱንያ ለሱ ጥቅልል ብላ ገብታለታለች

" አሉ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.0.ወ) ...

ለእያንዳንዳችን ከዱንያ የምንፈልገው ይሄንን ይመስለኛል። ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ አላህ ያዘነለት ሰው ካልሆነ በስተቀር ትርፍን ነገር ከአላህ እየተመኘ ዱንያ እንዳልተሰጠችው ፣ እንደጠበበችበት ያስባል። ...አላህ ይዘንልን🤲

ISLAMINDSET.


ISLAMIC MINDset dan repost
የጧት እና የማታ ዚክሮችን ማለት ይለማመዱ። እነዚህ ከላይ የምትመለከቷቸው ዚክሮች ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በህይወት ዘመናቸው ሲሏቸው የነበሩ ሲሆኑ ጧት ከሱብሂ በኋላ እና ማታ ከአሱር ሶላት በኋላ ማለትን ይልመዱ!

አላሁመ ሶሊ አላ ሙሐመድ ወአላ አሊ ሙሐመድ
__ መልካም ጁሙዓ __
ISLAMINDSET.

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.