📣 ኮሽታ 📢


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


ስለሁሉም ነገር ፈጣሪያችን ይመስገን
ዛሬ በህይወት አለን
ፍ ቅ ር ለ ፍ ጡ ራ ን
ሰ ላ ም ለ ሀ ገ ራ ች ን

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri






________ dan repost
! ወንድ ልጅም ቁስል አለዉ !!
ከእለታት አንድ ቀን ሚስት ባሏ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ እያለ እሩቅ ቦታ ለመሄድ ብላ ልብስ ለብሳ ቦርሳ ይዛ ትወጣለች። እንዳጋጣሚ ሆኖ የትራንስፖርት ገንዘብ ቤት ውስጥ ረስታ መውጣቷን አስታውሳ ወዲያውኑ ቤት ተመለሳች፤ ባሏ መኝታ ክፍል ገብቶ እንዴ ሕጻን ስቅስቅ ብሎ እየለቀሰ ሰማች። የባሏ እንደዚህ ማልቀስ የገረማት ሚስት በምን ምክንያት ነው የሚያለቅሰው ብላ ወደ በሩ ጠጋ ብላ መስማት ትጀምራለች።
እሱም አምላኬ ሠርቼ ልጆቼን እና ሚስቴን በደስታ እንዲያኖራቸው ሠላም እና ጥንካሬ ስጠኝ። በጉልበት ስራ ቤተሰቤን ማስተዳደር አልቻልኩም። በዚህ ሁኔታ እንዴት ለሚስቴም፣ለልጆቼም መስራት እና በደስታ ማኖር እችላለሁ ብሎ ያለቅሳል በዚህ ሰአት የሚስትቱ ቅስም ተሰበረ። እስከ ዛሬ ለምን ጥሩ ልብስ አይገዛም፣ለምን ጥሩ ቤት አይሰራም፣ለምን ጥሩ ገንዘብ ይዞ አይመጣም እያለች ትቆጣና ትናደድ የነበረው ሁሉ ስህተት መሆኑ ገባት፤ ባሏ በህመም እየተሰቀያ ለሷ እና ለልጇ ሲል የጉልበት ሥራ ስርቶ እንደሚመጣ ዛሬ ገና አወቀ። ከዛም ይቅርታ ጠየቀች።
#ሞራል(Moral value)
ባልሽ ምናልባት ሁለም ቆሻሻ ልብስ የሚለብስ ሊሆን ይችላል።
ባልሽ ምናልባት አልጋ ላይ ጎበዝ ላይሆን ይችላል ? ባልሽ ምናልባት የጓደኛሽ ባሎች የሚገዙላቸውን ልብስ ጫማ መግዛት ላይችል ይሆናል
ባልሽ ምናልባት ሁለም ፊቱ የሚያበራ ሊሆን ይችላል ♥ ባልሽ ምናልባት ሳቅ እና ጨዋታ የማያውቅ ሊሆን ይችላል
ባልሽ ላንቺ ከሁሉም የተሻለ ሰው ነው! ከበስተጀርባሽ ሆነው እኔ እወድሻለሁ እኔ እሻልሻለሁ የሚሉ ጥሩ ልብስ የሚለብሱ ጥሩ ምላስ ያላቸው ቆንጆ እና ውብ የሆኑ ወንዶች እንደ ባልሽ ህመም ውስጥም ችግር ውስጥም ስትሆኚ አንቺን አንቺን ብቻ አይሉም። ውበትሽ ሲያልቅ ውበትን ፍለጋ ጥሎሽ ይሄዳል፡፡ሙቀትሽ ቀዝቃዝ ሲል ሌላ ትኩስ ደም ፍለጋ ጥሎሽ ይሄዳል።ቆሻሻው ባልሽ ግን ላንቺ ውበት ብሎ ለልጆችሽ ውበት ብሎ ሁሌም ቆሻሻ መስሎ ካንቺ ጋር ይኖራል።
ስለዚህ እህቴ ባልሽን ከማንም ጋር ማወዳደር የለብሽም ለችግሮች አብራችሁ መፍትሄ ፈልጉ እንጂ ብዙ ችግር አለበት ብለሽ ንቀሽ ጥለሽ ለመሄድ አትችኩይ።ምክንያቱም አንድ አንድ ወንዶች ውበታቸውን ጉልባታቸውን የሚያጡት ለሚወዱት ቤተሳብ ብለውና መልካም ነገን ለማየት ሲሉ ነው።እስኪ ለእናታቸው ሲሉ ራሳቸውን የጣሉ፣ለእህታቸው
ሲሉ ራሳቸውን ለጣሉ፣ለልጆቻቸው ሲሉ ራሳቸውን ለጣሉ፣ለሚስታቸው ሲሉ ራሳቸውን ለጣሉ ወንዶች ሸር በማድረግ አድርሱላቸው።
እግዚአብሔር ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን እግዚአብሔር ብርሃኔና-መድሃኒቴ ነው።

https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0


________ dan repost
አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል

ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል

በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው በኃላ እይነ ስውሩን አስፈቅዶት ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ገልብጦት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት

ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ሞላው

የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል

"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው: እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት

ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው ።

https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0


________ dan repost
ልክ ዝናቡ መዝነብ ሲያቆም መጠለያ የነበረው ጥላ ሸክም ይሆናል። አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት አስፈላጊውን ከለላና ሽፋን እንዳልሰጠ ሁሉ ኋላ ላይ እንደ ሸክምና አላስፈላጊ ነገር ይቆጠራል።

አንተም ልክ እንደጥላው ጥቅምህ በሚፈለግ ሰዓት ሁሉም ወዳንተ ይሮጣል፤ ሁሉም አንተ ጋር ለመጠለል ይገፋፋል። ከዚያ ግን ካንተ የሚገኘው ጥቅም እየቀነሰ ሲሄድ ሁሉም ይወረውርሃል፤ ውለታህን አፈር ይበላውና ሸክም ትሆናለህ። ማንም ቢሆን ደስተኛ ሆኖ አይዝህም።



............Telegram................
ልክ ዝናቡ መዝነብ ሲያቆም መጠለያ የነበረው ጥላ ሸክም ይሆናል። አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት አስፈላጊውን ከለላና ሽፋን እንዳልሰጠ ሁሉ ኋላ ላይ እንደ ሸክምና አላስፈላጊ ነገር ይቆጠራል።

አንተም ልክ እንደጥላው ጥቅምህ በሚፈለግ ሰዓት ሁሉም ወዳንተ ይሮጣል፤ ሁሉም አንተ ጋር ለመጠለል ይገፋፋል። ከዚያ ግን ካንተ የሚገኘው ጥቅም እየቀነሰ ሲሄድ ሁሉም ይወረውርሃል፤ ውለታህን አፈር ይበላውና ሸክም ትሆናለህ። ማንም ቢሆን ደስተኛ ሆኖ አይዝህም።



............Telegram................
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0


https://qwickbirr.com/?aff=46358
ሊንካቸውን ጠቅ በማድረግ ቀጥታ ጨዋታ ላይ ያስገባቹሀል

ሁሉንም ቨርቹዋል ጨዋታ በስልካችን ብቻ ቤቲንግ ቤት መሄድ ቀረ

ከ#1000 ጨዋታ በላይ አሉ እየትዝናናቹ ከ#1 ብር ጀምሮ እስከፈለጋቹበት ድረስ ትጫወታላቹ
በ#1 ብር እስከ #10,000 ብር ድረስ በቀን ውስጥ ይሰራሉ

ኩዊክ ብር ላይ በኦላይን በመጫወት ደና ጠቃሚ ገንዘብ ይያዙ

ገንዘብ ወጪ እና ገቢ ለማድረግ በሲቢ , ቴሌብር , ቻፖ እና ሳንቲም ፔይ ማዘዋወር ይቻላል

መልካም ዕድል


በድሪል ሙዚቃ ውስጥ ላላቹ ከሚባለው በላይ የሰፈራቹን መልካምነት ገናናነትን የሚገልፅ ውብ የሆነ የዘፈን ግጥም አለ በቅናሽ መግዛት ለሚፈልግ ይደውሉልን

0976135267 ይደውሉ
HABESHA DRILL & RAP


ተቀበል አዝማሪ


የሰካራም ሀሳብ ቤት ማይመታ ግጥም፣
አፍህ ላይ ባያምር ለማሲንቆህ ባይጥም።
ተቀበል ግድ የለም ልስጥህ አንዲት ቃላት፣
ግና አደራህን ሺ ጊዜ ደጋግማት።

አንቺ ማለት በላት……

አንቺ ማለት ሴት ነሽ አዳምን ያሳትሽው፣
ክብር ለመቀበል ክብሩን ያስነጠቅሽው፣
ብዬ ሴትነትሽን ልንቀው አልኩና…

ሴትነትን ክብሯ አድርጋ የኖረች፣
ለካስ ካንቺ ሌላ ሌላ ሴት ልጅ አለች።
ታድያ ባንቺ ምክንያት ፣
የሴትነት ክብርን ለምን አዘቅጣለው፣
አንቺ ብታንሽ እንኳን ሴትነት ትልቅ ነው።

ብለህ ንገርልኝ ከማሲንቆህ ጋራ፣
የሰከረው ቃሌ ባንተ ቤት ከሰራ።
አንቺ ማለት በላት……

ልክ እዳረቄዬ አፍ ላይ የምትመሪ፣
በተስፍ ምትገዪ ባሳብ ምታሰክሪ።
እንደ ሲጋራዬ ካፌ ማትጠፊ፣
በልብ የማትረጊ እንደጪስ ምጠፊ፣
ከማሲንቆህ ጋራ ይህን ደጋግምላት፣
ምን እንኳን ባይገባት ትንሽ ከተሰማት።

አንቺ ማለት በላት……

ለጆቼ መታሰር ለግሮቼ ስብራት፣
ላይኖቼ መታወር ለልቤ ውልቃት።
ለስከዛሬው በደል ለስከዛሬው ጥፋት፣
ስላንቺ ሀጥያት ነው የህይወቴ ቅጣት።

እንካ ተቀበለኝ እኔም ልበቀላት፣
አደራህን ይህን በደንብ ደጋግምላት።

የምትበሪበት ክንፍ ይርገፍ ይሰባበር፣
በረከሰው ገላሽ ሴትነትሽ ይክበር።
ልክ እንደ ቀሚስሽ አይጠር ሀሳብሽ፣
ቆንጅናሽን ወስዶ ልብ ይቀይርልሽ።

ያዝማ ተቀበል አንድ የመጨረሻ፣
ባይኔ ባላይ እንኳን ያንቺን መጨረሻ።
ምን እንኳን ባይገባት፣
ይህን ደጋግምላት።
አንቺ ብጠይኝም እኔ አልጠላሁሽም አትጠራጠሪ
ጠላትህን ውደድ ስላለኝ ፈጣሪ!!!
Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   . 
@TADE_KEBRARAW


የትም ይወደቃል ወዴትም ቢሄዱ
የመጣው ዘጠኝ ሞት የሚገባው አንዱ
ከሺ መሀል ተርፎ ኑሮ ይሸመታል
ቀኑ የደረሰ ሺ ሲተርፍ ይሞታል


________ dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
#ምንድነው በጣም የናፍቀክ ነገር..?🥹💔🥀

ያው አይባልም እንጂ...
...... #እናቴ እንድትመለስ ነበር..😭💔🥀

#አይሆንም_ግን🥹💔🥀


❤️
              

Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


ስሙማ ዛሬ አንዱ ምን አለኝ መሰላቹ አግቢኝ ከዛ በምን ታኖረኛለህ ስለው ቆሎ እየቆረጠምን አለኝ🫢

አገባው ነበረ 🙄

ቆሎ እየቆረጠምን እንኖራለን ውዴ
ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ🥰
አንቺ ውሀ አጣጬ የእግዜር ባላደራ
እሺ በይኝ ላግባሽ ቤታችንም ይድራ 💍
አለኝ የኔ ሚስኪን አገባህ ነበረ😊
ቆሎ ባልቆረጥም እርሀብ ባይደፋኝ😁
ሊያውም በዚ ዘመን ያልከው ውዴ ዝምብለህ ስታየኝ የኤርፎራ ዶሮ እመስላለው እንዴ
ጭራሹን ልጅ በልጅ ሆኜልህ🙄
አንዱን በኋላዬ ሌላውን ከፊቴ
ቀሚሱን በግራ ቀሚሱን በቀኜ
እሪ እቧ ሲሉብኝ መንምኜ መንምኜ🙄
የድስት ፍቅፋቂ በጋራ ስንበላ 🙄
ጎረቤት ቢረብሽ ይደብራል ኋላ🤷‍♀
እኔም ተማርሬ እግዜር ከሚከፋው
ቆሎህን ለብቻህ ተደብቀህ ብላው
🤗

Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


________ dan repost
አንዳንዴ ራስህ ዝቅ ስታደርጎ፣ ከፈጣሪህ ፊት ስትሰግድ፣ ከትልልቆችህ ፊት ራስህ ዝቅ ስታደርግ አዲስ ፈጣሪ ላንተ የሚቸርህ ነገር አለ። ይህም ምህረትና እኩልነት ነው።

ዝቅ ስትል አብሮህ ዝቅ የሚል አምላክ አለ። ስለዚህ ሰው ዝቅ ስላደረገህ ብቻህን አይደለህም። ዝቅ ያለ ሁሉ ያለቀለት አይምሰልህ!

እስኪ የእጅህን እጣቶች ግጠምና ወደ አንተ አዙረህ እጠፋቸው።
አየህ ዝቅ ስትል እኩል ትሆናለህ!

Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


________ dan repost
አስቡት ምስጋና ከምን እንደሚጀምር፣ አሁን ላይ ካለህ ተጨባጭ ሁኔታ ሲሆን ቢሞላህም ቢጎለህም በህይወት እስካለህ ድረስ ፈጣሪን ማመስገን ነው።
ስታመሰግን የሆነ ነገር ከውስጥህ እየቀረበ ይመጣል፣ ያ የገደበህ ነገር፣ የምትፈልገውን እንዳታገኘው በየጊዜው የሚርቅብህ፣ እየቀረበ ሲመጣ ይሰማሃል። ሁሉም በምስጋና ግን ቅርብ ይሆናል።

እንዲደረግልህ የምትፈልገው ነገር ካለ መጀመሪያ የምትፈልገውን ነገር ለፈጣሪ ንገረው። ያኔ ርሳው ቀኑን ጠብቆ ያንተ ሆኖ ታገኘዋለህ!


Join and invite your friends
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


ልጅ መንገድ እየሄደ ይመሽበትና ወደ አንድ ደሳሳ
ቤት ጎራ ብሎ አሳድሩኝ ይላል! እነሱም
ቤት የፈጣሪ ነው ግባ አሉት!

እግሩን አጠበችለት ና እራት ቀርቦ በልተው ቡና ጠጥተዉ ወደ መኝታ ለመሄድ ያመራሉ!
ነገሩ አሁን ችግር ሆነ ...!

በመጨረሻም የልጅቷን አልጋ
በትራስ ለሁለት ከፍሎ ልጅቷ
አልጋ ላይ አሳደረው....!

ከቤቱ ወጥቶ መንገዱን ሊጀምር ሲል
ጊቢ ውስጥ አያትና "ሳልሰናበትሽ
ኮ....በአጥሩ መጥቼ ልዘይርሽ?" አላት...!

እሷም "ማታ ትራስ መዝለል ያቃተህ አሁን አጥር
ብትዘል ምን ጥቅም አለው!" አለችው....!

እሱም "ማታ መሀላችን የነበረው ትራስ ብቻ ሳይሆን
የአባትሽም እምነት ነበር! ብሏት መንገዱን ቀጠለ!

@Sisko24k

https://www.instagram.com/sisko24k


________ dan repost
ኃይለ ሥላሴ በፎቶ ሲታዩ ሁልጊዜ የሚያሳዩት ምልክት ነበር፡፡ ይህን
ምልክት አንዳንዶች የሰይጣናዊ (Satanic Freemasonry) ምልክት
ነው ሲሉ ይስተዋላል፡፡ የሰይጣናዊው ፍሪሜሰን ማኅበር ምልክቱ በጋር
(Compass) ስለ ነበር ኃይለ ሥላሴም የዚያ ማኅበር አባል በመሆናቸው
ምልክቱን ያንጸባርቁ ነበር የሚሉ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የግብጻውያንን ጣዖት
ሆረስ ለማመልከት ነው ይላሉ፡፡ ነገር ግን እውነታው ይህ አይደለም፡፡
በእጃቸው የሚያሳዩት ምልክት ኮምፓሱን አይመስልም፡፡ በተደጋጋሚ ንጉሠ
ነገሥቱ እጃቸውን አጠማምረው የሚታዩት የሰሎሞን ዘር መሆናቸውን
ለማመልከት ነው፡፡ ይህች ኮከብ (✡ ) የእስራኤልን ነገድ የምትወክልና
የሰሎሞን ማኅተም መሆኗ ይታወቃል (ከታች ያለውን ምልክት በአጽንዖት
ይመልከቱ)፡፡
ይህን የጃን ሆይ ምልክት ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን የመሩ ነገሥታት
ተጠቅመውበት አያውቁም፡፡ በእጃቸው ላይ ያመላከቱት ኮከብ ከላይ አንድ
ሠረዝ ባዶ ሆኖ ቢታይም ከታች ያጠላለፉት እጃቸው በዓይነ ኅሊናችን
ኮከቡን እንድንሥል እጅግ ይረዳናል፡፡ ይህ ውስብስብ የጃን ሆይ ጥበባዊ የፈጠራ ምልክት ዓለምን እጅግ አስደምሟል፡፡ አሁን ላይ የራስ ተፈሪያን ተከታዮች ምልክቱን አብዝተው ይጠቀሙታል፡፡
# ክብር_ለጃንሆይ

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


________ dan repost
እኛ የት ነበርን⁉️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍ሁለት ጓደኛሞች አብረው ከተማ ውስጥ እየዞሩ ሳለ አንደኛው ወደ ትላልቅ ህንፃዎች ተመለከተና ለጓደኛው እንዲህ ብሎ ጠየቀው።
:
"ይህንን ሁሉ ሀብት ሲታደል እኛ የት ነበርን?" አለው
:
ጓደኛውም "ና" ብሎ እጁን ይዞ ወደ ሆስፒታል አስገባውና "ይህንን ሁሉ በሽታ ሲታደል እኛ የት ነበርን?" ብሎ ጠየቀው።
*

ለማለት የተፈለገው!
የተሰጠንን እናመስግን ነው‼️

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


________ dan repost
አልወድህም አፈቅርሃለሁ

    ጓደኛዋን ሁልጊዜም እንደምትወደው ትነገረው ነበር፤ ሆኖም እንደቀልድ ይወስደው ስለነበር በጣም አዝና አንድ ቀን፡- እንደምወድህ ስነግርህ ለምንድነው የምትስቀው ብላ ጠየቀችው።
ልጁም፡- እንደምትወጂኝ ሳይሆን እንደምታፈቅሪኝ ስለማውቅ አፈቅርሃለሁ ከማለት ይልቅ እወድሃለሁ ማለቱን ማዘውተርሽ ስለሚገርመኝ ነው ብሎ መለሰላት።
ልጅቷም ጭንቀት እና ሃዘን የተሞላበት ፊቷን ወደ ፈገግታ ቀይራው ኦ… የኔ ፍቅር በጣም አፈቅርሃለሁ አለችው።
ልጁም፡- የኔ ውድ አንድ ለየት ያለ ነገር እንድታደርጊልኝ እፈልጋለሁ
ልጅቷም፡- ምን?
ልጁም፡- ማታ ቤት ስትገቢ እናትሽን አመስግኚልኝ
ልጅቷም፡- እሺ… ግን በምን ምክንያት?
ልጁም፡- በሕይወቴ መጥታ ደስታን የሰጠችኝኝ ነገ ደግም የትዳር አጋሬ የምትሆኚውን አንቺን ስለወለደች ነው። ብሎ መለሰላት

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

@KEBRARAWBOY


6 ትናንሽ ታሪኮች
@KEBRARAWBOY
  1  በአንድ ወቅት በአንድር መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዙ ተገኘ፡፡

(ይህ እምነት ይባላል፡፡)

፣፣፣፣፣፣፣፣፣

2  ህጻን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካች እንጂ አታለቅስም ፡፡ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!!

ይህም እርግጠኝንት ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

3  በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በህይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም(የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!!

ይህም ተስፋ ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣፣፣፣

4 ወደ ፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን)እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!!

ይህ ደሞ በራስ *,መተማማን ይባላል፡፡**

፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣

5 ዓለም ላይ የሚወርደውን መከራና ስቃይ እናያለን ይሁን እንጂ አሁንም እንጋባለን

ይህም ፍቅር ይባላል፡፡

፣፣፣፣፣፣

6 አንድ ሽማግሌ በለመበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት ጉሩም ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች

“እኔ የስድሳ ኣመት ሽማግሌ አይደለሁም ፣የአርባ አራት ኣመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአስራ ስድሰት ኣመት ወጣት እንጂ”

ይህ ለራሳቸእን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

እምንት ፣እርግጠኝነት ፣ተስፋ ፣በራስ መተማማን ፣ ፍቅርና ለራሳችሁ ጥሩ አመለካካት ሳይለያችሁ ኑሩ !!!


________ dan repost
✨አንዲት ህፃን ጓደኛዋ ቤት ለመጫወት ትሄዳለች...

...ጓደኛዋም እንዲህ አለቻት እናቴ እንዳትነሳ ድምፅ አትፍጠሪ እናቴ ተኝታለች....

...ልጅቷም እንዲህ ስትል መለሰች ነይ እሺ የእናቴ መቃብር ጋር ሄደን እንጫወት...☹️

...ለምን?

...እናቴ እንድትነሳ🥺



  አሳማሚ እውነታ...

በህይወት ያሉትን እድሜያቸውን ያርዝምልን
የሞቱትን ፈጣሪ ይዘንላቸው
🤲

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/


________ dan repost
ድንቅ ታሪክ እነሆ !!

አንድ ንጉስ በከተማው ውስጥ የሚገኙ እድሜ ጠገብ ሽማሌዎች እንዲሁም አሮጊቶች #እንዲገደሉ ትዕዛዝ ያስተላልፋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አንድ ወጣት ሽማግሌ አባቱን በጣም ይወደው ነበር። ወጣቱም ይህን አስከፊ የንጉሱን ትዕዛዝ በሰማ ግዜ አባቱን ለመሸሸግ በማሰብ በሚስጥር ሰርቶት የነበረው የመሬት ስር ቤት ውስጥ አባቱን ሸሸገው።ወታደሮቹም ለፍተሻ መጡ። ቤቱ ውስጥ በደንብ ቢፈልጉም ማንንም ስላላገኙ ትተው ተመለሱ።

ቀናቶች አለፋ...።ንጉሱም ይህ ወጣት ሽማግሌ አባቱን እንደደበቀ ይሰማል።ይህንንም ሊያውቅ የቻለው በሰላዬቹ አማካኝነት ሲሆን ይህንን ወጣት አስሬ አባቱንም ከምገድለው ለምን አልፈትነውም ብሎ በማሰብ፤ወታደሮቹን በጠዋት ወደ ልጁ ቤት በመላክ እንዲህ እንዲሉት አዘዛቸው።ንጉሱ "ተሳፍረህና እየተራመድክ እንድትመጣ ያዝሃል" ወጣቱም ግራ ገባው😳 ወደ አባትየውም በመጓዝ አማከረው። አባትየም የመገረም ፈገግታን ፈገግ ካሉ በኋላ እንዲህ አሉት "ትልቅ ክይዘራ ይዘህ ና እና እሱ ላይ ተደግፈህ እየተራመድክ ሂድ" አሉት። ወጣቱም የተባለውን አድርጎ ሄደ። ንጉሱም በወጣቱ ብልጠት ተገርሞ "ሂድ ተመለስ ነገ ጠዋት ደግሞ ጫማ ለብሰህና በባዶ እግርህ ና" አለው።ወጣቱም ወደ አባቱ ዘንድ በመጓዝ ነገሩን አጫወታቸው። አባትየውም "ጫማህን ስጠኝ" አሉት። የስረኛውን የጫማ ሶል አወለቁት እና "ይህንን ንጉሱ ዘንድ ለብሰህ ሂድ" አሉት።ወጣቱም የተባለውን አደረገ።

በድጋሚ ንጉሱ በወጣቱ ብልጠት እጅግ በጣም ተገረመ።ከዚያም እንዲህ አለው"ሂድና ነገ ጠዋት ጠላትህንና ወዳጅህን ይዘህ ና" አለው። ወጣቱም ስለጉዳዩ አባቱን አማከረ። መፍትሄ የማያጡት አባት እንዲህ ሲሉ ጠቆሙት " ነገ ስትሄድ ሚስትህንና የቤትህን ውሻ ይዘህ ሂድ ንጉሱ ዘንዳም ስትደርስ ሁለቱንም ደብድባቸው"  አሉት። ወጣቱም"እንዴት!?" አለ። እሳቸውም ይሁን አድርግ ሚፈጠረውን ትመለከታለው አሉት።

ወጣቱም ወደ ንጉሱ ዘንድ በጠዋት ተጉዞ ንጉሱ ዘንድ እንደቁረበም ሚስቱን ደበደባት(መታት)። እሷም በጣም ጮኅች። እንዲህም አለችው "እኔን በመምታትህ ትፀፀታለህ። ብላው ለንጉሱ አባትየውን ደብቆ እንዳለ ተናገረች😂" ትታው ጥላው ሄደች። በመቀጠልም ውሻውን መታው። ውሻውም ሮጦ ሸሸ።ንጉሱም ተገረሞ "እንዴት ታማኝ ወዳጅና ጠላት!?" አለ። ወጣቱም ልጅ ለውሻው ምልክት ሲሰጠው ውሻው እየሮጠ መጣና በደስታ ይታሸው ጀመር። ወጣቱም ለንጉሱ እንዲህ አለው "ይህ ውሻ ለእኔ ታማኝ ወዳጄ ነው። ጠላቴ ደግሞ ወዳጄ የመሰለችኝ ናት" አለው

ንጉሱም በጣም ተደነቀ።ማን እንደመከረውም ሲጠይቀው አባትየው መሆኑን ነገረው። ንጉሱም ለወጣቱ እንዲህ አለው። "ነገ ጠዋት አባትህን ይዘህ ና" ወጣቱም ወደ አባቱ ዘንድ ሄዶ የሆነውን ተረከለት።በጠዋትም ወደ ንጉሱ ዘንድ ሄዱ። ንጉሱም ይህን ሽማግሌ አባት የራሱ #አማካሪ አድርጎ ሾመ። ወጣቱም ከመሞት በአባቱ ምክንያት ተረፈ።


ጭብጡ ምንድነው!? አባት እድሜው የፈለገ ቢገፋም እሱ ዋጋውን የማናውቅለት ትልቅ ፀጋ ነው። የሱን ቦታ የምንረዳው ምናልባት ሲለየን ነው።

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
https://t.me/+tv1OFMgzPx4zZGU0
F O L L O W       M O R E .   .   .
https://www.instagram.com/kebrarawboy?r=nametag

https://vm.tiktok.com/ZMj2aEbhT/

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.