2015 ዓ.ም አዲስ አመት
ከጭጋጋማው ወራት ወደ ፈካው ወር ፣ ከደመና ወደ ፀሐይ ፣ ከትናንት ወደ ነገ በሚወስደው የዘመን ሀዲድ ላይ በመሆን አዲስ አመት ለማየት ስለበቃን ደስ ሊለን ይገባል። ዘመን የሰው ልጅ ነው ። የሰው ልጅ ደሞ በመኖር ሒደት ውስጥ ለሌሎች ትሩፍት የሚሰጥ ፍጡር ነው። መኖራችን ከኛ በላይ ሊሆን ይገባል ፣ መለወጣችን ከዘመን ጋር ሊሆንም ግድነው። ደጁ ሲፈካ በልባችን የተስፍ ብርሀን እንዲፈነጥቅ መፍቀድ አለብን። የጨለመው ሲነጋ እኛም መንጋት እና መንቃት አለብን።
አዲሱ አመት በልባችን የያዝነው መልካም ትሩፍት የሚተገበርበት ፣ ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት ፣ ፍቅር የሚነግስበት እንዲሆን ቅንድል ትመኛለች። በአዲሱ አመት በአዳዲስ ስራዎች ወደናንተ እንደምንደርስ ቃል እየገባን ለመላው የመፅሔታችን አንባቢዎች እንኳን ለዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት
@KendelM