የኡዱሒያን እርድ የሚመለከቱ ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች
~
ኡዱሒያ ማለት በዒደል አድሓ ቀን ወደ አላህ ለመቃረብ ታስቦ የሚታረድ እርድ ነው፡፡ ነብዩ ﷺ በተግባር ፈፅመውታል፡፡ መዲና ላይ አስር አመት ሲኖሩም ኡዱሒያን ያርዱ ነበር፡፡ [ሚሽካት፡ 1475] እንዲፈፀምም አዘዋል፡፡ ስለዚህ አቅም ያለው ሰው ሊፈፅመው ይገባል ማለት ነው፡፡ ነብዩ ﷺ “አቅሙ እያለው ኡዱሒያን ያላረደ ሰው መስገጃችንን እንዳይቀርብ” ብለዋል፡፡
ኡዱሒያ ብዙሃን ዑለማኦች ዘንድ የጠነከረች ሱና ነች። ከፊል ምሁራን ዘንድ ደግሞ ግዴታ ነች። ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - ከሁለቱ ሃሳቦች የሚጎላው ግዴታ ነው የሚለው ነው ይላሉ። ግዴታም ቢሆን ታዲያ ያልቻለ ሰው ኡዱሒያ ለማረድ ብሎ እዳ እንዲገባ / እንዲበደር አይገደድም።
ለኡሑዲያ የሚታረደው እንስሳ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት
1. የሚታረደው እንስሳ ከበግ፣ ፍየል፣ ከብት እና ግመል ውስጥ ብቻ መሆን አለበት።
2. ከብትና ግመልን በጋራ ማረድ የፈለገ አንዱ ቢበዛ ለ7 ሰው ነው መሆን ያለበት፡፡ ከዚያ መብለጥ የለበትም። አንዱ ለ 7 ሰው ከተቻለ ቁጥራቸው ከ 7 ያነሰ ሆነው ቢያርዱ የበለጠ ያብቃቃል። ፍየልና በግ ለጋራ ማረድ አይቻልም፡፡
3. የሚታረደው እንስሳ እድሜው የደረሰ መሆን አለበት፡፡ በግ 6 ወር፣ ፍየል 1 አመት፣ ከብት 2 አመት፣ ግመል ከሆነ 5 አመት የሞላው መሆን አለበት፡፡
4. የሚታረደው እንስሳ መታወሩ ግልፅ የሆነ፤ ህመሙ ግልፅ የሆነ በሽተኛ፤ ግልፅ የሆነ አንካሳ፤ በጣም ያረጀ፣ አብዛሃኛው ወይም ግማሽና ከዚያ በላይ የሆነ ጆሮው፣ ጅራቱ፣ ላቱ፣ ቀንዱ፣ የተቆረጠ ወይም የተሰበረ መሆን የለበትም፡፡ ትንንሽ እንከኖች ችግር አይሆኑም። የተኮላሸ መጠቀም ይቻላል። ነብዩ ﷺ ሁለት የተኮላሹ በጎችን አርደዋል። [ሱነኑል በይሃቂይ]
5. የሚታረደው የግድ በተገደበው ጊዜ መሆን አለበት፡፡ እሱም ከዒድ ሶላት በኋላ እስከ ዙልሒጃ 13 ባለው ነው፡፡ ነብዩ ﷺ (ዒድ) ከመሰገዱ በፊት ያረደ በሷ ቦታ (እርዱን) ይድገም፡፡ ያላረደ ይረድ” ብለዋል፡፡ [ቡኻሪ]
6. ያለ ምንም ልዩነት ከሁለቱም ፆታ ከወንድም #ከሴትም ለኡዱሒያ ማረድ ይፈቀዳል፡፡ [ኢብኑ ባዝ፣ ፈታዋ ኑሩን ዐለ ደርብ፡ ካሴት ቁ. 72]
7. ቆዳውንም ይሁን የትኛውንም ክፍሉን መሸጥ አይፈቀድም፡፡ ለአራጁ የሚከፈለውም ከኡዱሒያው ቆዳ ወይም ሌላ ክፍሉ መሆን የለበትም፡፡ ነብዩ ﷺ “የኡዱሒያውን ቆዳ የሸጠ ኡዱሒያ የለውም!” ብለዋል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2/1055] ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከኡዱሒያው ስጋ፣ ሞራ፣ ቆዳ፣ ወይም ሌላ ነገር መሸረጥ ክልክል ነው፡፡ ምክንያቱም ለአላህ ያወጣው ገንዘብ ስለሆነ ልክ እንደ ሶደቃ መመለስ አይቻልም፡፡ [ፈታዋ ኢብኒ ዑሠይሚን፡ 25/162] ባይሆን ስጦታ የተሰጠው ሰው ቢሸጥ ምንም ችግር የለበትም፡፡
8. ስጋው ምን ይደረጋል? በእለቱ ከቤት ይበላል። ለዘመድ፣ ለጓደኛ፣ ለምስኪን ይሰድቃል ወይም ስጦታ ይሰጣል። ቀሪ ከኖረ ያስቀምጣል፡፡ ስጦታ የተሰጠው ሰው ግን መሸጥን ጨምሮ ሐላል በሆነ መልኩ ለፈለገው አገልግሎት ማዋል ይችላል፡፡
9. ኡዱሒያውን እራሱ ባለቤቱ ቢያርድ በላጭ ነው፡፡ ካልቻለ ወይም ካልተመቸው ግን ሰው መወከል ይችላል፡፡
ከተለያዩ ፈትዋዎች የተሰበሰበ ነው፡፡
=
ሸይኽ ሷሊሕ አል ሉሃይዳን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-
«በወላጆች ላይ ፅድቅን ማድረግ አላህን በኢኽላስ ከማምለክ ጋር የተያያዘ ሲሆን ወላጅን አለመታዘዝ በአላህ ላይ ከማሻረክ ጋር የተያያዘ ነው። ለዚህም ነው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ‹‹ ከከባባድ ወንጀሎች ይበልጥ ከባዱን አልነግራችሁምን?» አሉ። ሰሃቦችም፦ «አዎን ይንገሩን» አሏቸው።
እሳቸውም፦ “በአላህ ላይ ሽርክን መፈፀም ነው፣ ከዛም ወላጆችን አለመታዘዝ ነው።» በማለት መለሱ። ምስጋናን በተመለከተ አላህ በቁርኣኑ ፦ « እኔን እና ወላጆችህን አመስግን።» ይላል።
@Khalid_islamawi_studio