እየሩሳሌም ሶስተኛው የሙስሊሞች ቅዱስ ስፍራ
አንብበው ሲጨርሱ ሼር በማድረግ ለሌሎችም ያዳርሱ
እየሩሳሌም በሙስሊሞች ዘንድ ከመካ እና ከመዲና ቀጥላ ሶስተኛዋ ቅድስት ስፍራ ናት፡፡ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡት ትልቅ ቦታን ባለመረዳት ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች የእየሩሳሌም ጠላት እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፡፡ እውነታ ግን እየሩሳሌም ለሙስሊሞች የተከበረውን መስጂደል አቅሳን ይዛ የምትገኝ የተከበረች ስፍራ ናት፡፡
ሙስሊሞች ወደ መካ እና መዲና እንደሚጓዙት ሁሉ ወደ እየሩሳሌም በመጓዝም መስጂደል አቅሳን ማየትን ይሻሉ፡፡በወራሪዋ እስራኤል አማካኝነት ይህ የተከበረ ቦታ በህፃናት፣በአዛውንቶች እና በሴቶች ደም ሁሌም እንዲጨቀኝ ቢደረግም አንድ ቀን ከወራሪዋ እስራኤል ነፃ የሚወጣበት ቀን መምጣቱ አይቀርም፡፡
አለም ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች ለእየሩሳሌም የሚሰጡትን ቦታ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ጠንቅቀው ሊረዱት ይገባል ስለ ፍልስጤማውያን ስንጮህ በግፍ መሬታቸውን በወራሪዋ እስራኤል ስለተነጠቁ ብቻ ሳይሆን ወይም ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ወይንም አረብ ስለሆኑ ሳይሆን በወራሪዋ እስራኤል በጉልበት የተያዘብን በእየሩሳሌም ምድር የሚገኘው መስጂደል አቅሳም የፍልስጤማውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ሙስሊም ቅዱስ ስፍራ በመሆኑ ነው
እያንዳንዱ ሙስሊም ስለ እየሩሳሌም ፤ስለ መስጂደል አቅሳ ዘወትር ፀሎት ያደርጋል፡፡ ከግፈኞቹ ፂዬናውያን ነፃ ወጥታ ሁሉም ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ በመስጂደል አቅሳ ሰላቱን ሊሰግድ ይናፍቃል፡፡
የሙስሊሞችን እና የእየሩሳሌምን ጥብቅ ትስስር ለመረዳት የተወሰኑ ነጥቦችን በመጥቀስ እንመልከት
1. መስጂድ አል-አቅሷ የቦታና የመስጂድ ሥም ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ሃይማኖት ጋር የሚያገናኙት በርካታ ቁምነገሮች አሉ፡፡ አምላካችን አላህ (ሱ.ወ.) መስጂድ አል-አቅሷን እና ዙሪያውን በሱ የተባረከና የተቀደሰ አካበቢ መሆኑን በቁርአን ላይ ገልፆልናል፡፡
سُبْحَانَ الَّذِي أَسْرَىٰ بِعَبْدِهِ لَيْلًا مِّنَ الْمَسْجِدِ الْحَرَامِ إِلَى الْمَسْجِدِ الْأَقْصَى الَّذِي بَارَكْنَا حَوْلَهُ لِنُرِيَهُ مِنْ آيَاتِنَا ۚ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ ﴿١
ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ውስጥ ያስኼደው (ጌታ) ጥራት ይገባው፡፡ ከተዓምራቶቻችን ልናሳየው (አስኼድነው)፡፡ እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚው ተመልካቺው ነው፡፡((አል-ኢስራእ ፡1)
2. ሌላው አል-አቅሷን ከሙስሊሞች የሚያስተሳስረው የኢስራእና ሚዕራጅ ምድር መሆኑ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ወደ ሰማዩ ዓለም ጉዞ ባደረጉ ጊዜ ከመካው መስጂድ ወደ እየሩሳሌም መስጂድ አልአቅሷ ተጉዘዋል፡፡ ከዚያም በመነሳት ነበር ወደ ሰማዩ ዓለም የተጓዙት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ ወደ በይት አልመቅዲስ መጓዛቸው የቦታውን ታላቅነትና ቅድስና ያመለክታል፡፡
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ወደ እየሩሳሌም ወደሚገኘው አል-አቅሷ መስጂድ በተጓዙበትም ወቅት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ከአላህ የተላኩትን ታላላቅ ነቢያቶችን መሪ ሆነው አሰግደዋል፡፡ከነዚህም መካከል ከነብዩላህ አደም ጀምሮ እስከ እየሱስ ክርስቶስ(አ.ሰ) ያሉት ነብያት ይገኙበታል፡፡
3. የእየሩሳሌም ምድር በርካታ ታላላቅ የአላህ ነብያት የተላኩበት ምድርም ነው፡፡ አባታችን ኢብራሂምን (አብረሃም) (ዐ.ሰ) ጨምሮ ዳውድ(ዳዊት)፣ ሱለይማን(ሰለሞን)፣ ሙሳ(ሙሴ)፣ ኢሳ( እየሱስ ክርስቶስ ) (አ.ሰ) እና ሌሎችም ህዝቦች አላህን በብቸኝነት አንድ አድርገው እንዲገዙ ጥሪ እንዲያደርጉ ከአላህ የተላኩበት ምድር ነው፡፡
4 . እንደ አብዛኞቹ ዑለማኦች(የእስልምና ሊቃውንት) ስምምነት በእየሩሳሌም የሚገኘውን አል-አቅሷ መስጂድን ለመጀመሪያ ጊዜ የገነቡት አባታችን አደም (ዐ.ሰ.) ሲሆኑ ኋላ ላይ ግን ነብዩላህ ኢብራሂም (አ.ሠ) ካዕባን በድጋሚ እንደገነቡት ይህንንም መስጂድ (የፀሎት ቦታ) አስፍተውታል፡፡ በመቀጠልም የነብዩላህ ዳውድ(ዳዊት) ልጅ የሆኑት ነቢዩ ሱለይማን(ሰለሞን) ሙሉ ግንባታውን በማደስ እንዳጠናከሩት እና እንደገነቡት በታሪክ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
በምድር ላይ አላህን ለማምለክ ታስቦ በነብዩላህ ኢብራሂም) (አ.ሰ)የተገነባው የመጀመሪያው መስጂድ (የፀሎት ስፍራ) መካ የሚገኘው አልሐራም (ከዕባ) መሆኑ ይታወቃል፡፡ አል-አቅሷ ደግሞ በምድር ላይ የተገነባ ሁለተኛው መስጂድ (የፀሎት ስፍራ) ሲሆን በሱ እና በከዕባ መካከል የአርባ አመት ዕድሜ ብቻ ነው ያለው፡፡ ነብዩላህ ኢብራሂም ከልጃቸው እስማኤል ጋር በመካ ካዕባን ከገነቡ ቡኋላ ከ 40 አመታት ቡኋላ በእየሩሳሌምም ይህን መስጂደል አቅሳን (የፀሎት ስፍራ) አስፍተውታል፡፡ ከነብዩላህ ኢብራሂም ቀጥሎ ልጃቸው ይስሓቅ ቀጥሎም የልጅ ልጃቸው ያቆብ (ዐ.ሰ) ወደ ግብፅ እስከሄዱበት ጊዜ ድረስ አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩበትቦታ ሆኖ ቆይቷል፡፡
5. እየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሷ የመጀመሪያው የሙስሊሞች ቂብላ(የሰላት አቅጣጫ) ነው፡፡ ነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለአለም ህዝብ በነብይነት ሲላኩ የሙስሊሞች ቂብላ/የሶላት መቀጣጫ/ ወደ ከዕባ/መካ/ እንዲሆን ከመደረጉ በፊት ለአሥራ ስድስት ወይም ለአሥራ ሰባት ወራት ወደእየሩሳሌም ወደ መስጂደል አቅሳ ዞረው ሰግደዋል፡፡ ካዕባ የሰላት አቅጣጫ ከመደረጉ በፊት ሙስሊሞች ወደ እየሩሳሌም በመዞር ነበር ሰላታቸውን የሚሰግዱት፡፡ ዛሬ ላይ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖች ሙስሊሞች ወደ መካ ካዕባ ዞራችሁ የምትሰግዱት ለጥቁሩ ድንጋይ ነው ብለው ባለማወቅ ውንጀላ ሲያቀርቡ ሙስሊሞች በመጀመሪያ ፊታቸውን ወደ እየሩሳሌም በማዞር ይሰግዱ እንደነበር ቢያውቁ ወደ አንድ አቅጣጫ መዞር የምንሰግድለት አምላክ አንድ ቦታ በመገኘቱ ሳይሆን የአንድነት ተምሳሌት መሆኑን ይረዱ ነበር፡፡
6. ጓዝ ተጭኖና ስንቅ ተቋጥሮ ለጉብኝትም ሆነ ለሶላት ከሚኬድባቸው ሶስት መስጂዶች ውስጥ እየሩሳሌም የሚገኘው አል-አቅሷ መስጂድ አንዱ ነው፡፡ በዚህ በእየሩሳሌም በሚገኘው በአልአቅሷ ውስጥ የሚሰገድ ሶላት በሌላው መስጂድ ውስጥ ከሚሰገደው በደረጃ በአምስት መቶ እጥፍ ይበልጣል፡፡ በአል-አቅሷ መስጂድ ውስጥ የሚሰገደውን ሶላት ሊበልጥ የሚችለው በመካ (መስጂድ አልሐራም) እና በመዲና የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) መስጂድ ውስጥ የሚሰገደው ሶላት ብቻ ነው፡፡ለዚህም ነው ሁሉም ሙስሊም ከመሞቱ በፊት ከመካ እና ከመዲና መስጂዶች ቀጥሎ ወደ እየሩሳሌም ተጉዞ በመስጂደል አቅሳ ለመስገድ የሚመኘው፡፡
7. በርካታ የነብዩ መሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ባልደረቦች እና ትላልቅ ደጋግ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እየሩሳሌም ስለሚገኘው ስለ አል-አቅሷ ደረጃና ቅድስና ያስተማሩትን በመከተል ወደዚያ ሄደዋል፡፡ ጎብኝተውታል፡፡ ሰግደውበታል፡፡ አል-አቅሷ በታሪክ በተለያዩ ገዥዎች ሥር በቅብብሎሽ ከቆየ በኋላ በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር የሆነው በኸሊፋ ዑመር ኢብኑ አልኸጣብ (ረ.ዐ.) ዘመን ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ በርካታ ሶሓቦች በበይት አልመቅዲስ በመገኘት ተምረዋል፣ አስተምረዋል፡፡ እዚያው ቆይተው ከሞቱት ታላላቅ ሶሓቦች መካከል ዑባዳ ኢብኑ አስሷሚት እና ሸዳድ ኢብኑ አውስ (ረ.ዐ.) ይገኙበታል፡፡ የተቀበሩትም ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጭ በሚገኘው ባብ አር-ረሕመህ በሚሰኘው ቦታ ላይ ነው
Join and Share
👇👇
😍@khalid_islamawi_studio