Bahiru Teka dan repost
✅ አስተማሪና አስገራሚ ገጠመኝ
አንድ አላህ ሪዝቁን ያሰፋለት አባት ልጁን ይዞ ለማዝናናት በመኪና ይወጣል ። የሚፈልገው ቦታ ወስዶ እያዝናናው እያለ የሶላት ሳአት እየደረሰ መሆኑን ሲያይ ልጁን ይበቃል የሶላት ሳአት ደርሷል ብሎት ይወጣሉ ። በቅርብ ወደ ሚገኝ መስጂድ እየሄደ እያለ ከእግረኛ መንገድ ወጣ ብሎ አንድ የ9ኝ አመት አካባቢ የሚሆን ፀጉረ ሉጫ በጣም የሚያምር ልጅ ፊት ለፊቱ ትንሽ ቆስጣ ፣ ካሮትና ጎመን በትንሽ የሱፍራ አይነት ላስቲክ ተቀምጦ ልጁ ግራ እጁን አጥፎ በጉልበቱ ላይ አድርጉ አንገቱን ደፍቶ በቀኝ እጁ ጠጠር እየወረወረ ያያል ።
መኪናውን አቁሞ ቀስ ብሎ ጠጋ ብሎ ይሄ ምንድነው ብሎ ይጠይቀዋል ? ልጁም የሚሸጥ ነው ይለዋል ። እንደ መደንገጥ ብሎ ዋጋውን ይጠይቀዋል ። ልጁም የየአንዳንዱን ዋጋ ይነግረዋል ። ሰውየው ከተጠየቀው በላይ ለየአንዳንዱ መቶ መቶ ብር ሰጥቶት በፌስታል ያስገባቸዋል ። ልጁም ይሄ ሁሉ አያስፈልግም ዋጋው ትንሽ ነው ይላል ። ችግር የለም ጎበዝ የኔ ልጅ በጣም ጎበዝ ነህ እናትህ በደንብ እንድታመጣ ንገራት ሌላ ጊዜም እገዛሀለሁ ብሎት ሊሄድ ሲል ልጁ ተነስቶ ይቆምና እጁን ዘርግቶ አላህ ይስጥልኝ ብሎ ወደ እናቱ ሊሮጥ ሲል እጁን ያዝ አድርጎ ቆየኝ ብሎት ወደ መኪናው ሄደ ።
ሰውዬው ልጁ ሲነሳ ያደረገው ጃኬትና ሱሪ እንዲሁም ጫማ የተቀዳደዱ መሆናቸውን አይቶ ነበር ። መኪናው ጋር ሄዶ እቃውን መኪና ውስጥ አድርጎ ልጁን ከሚኪና አውርዶ ይዞት መጣ ። ለልጁ በመኪና ሄደው ልብስ እንደሚገዙ ነግሮት የለበሳቸው ልብሶች ለዚህ ልጅ አውልቆ እንደሚያለብሰው ነገረው ልጁም ሌላ ከገዛህልኝ እሺ አለ ። ይዞት መጣ የልጁን ጫማና ሱሪ አውልቆ አለበሰው ከዛም የልጁን ጃኬት አውልቆ ፊቱን አዙሮ ከኪሱ በዛ ያለ ብር አውጥቶ ኪሱ ውስጥ አደረገና አልብሶት አሮጌዎቹን በፌስታል አድርጎ እዛው አስቀምጦለት ባዶ እግሩን የሆነውን ልጁን አቅፎ ወደ መኪናው አቀና ።
ምስኪኑ ልጅ የተደበላለቀ ስሜት እየተሰማው ልብሶቹን አያቸው ። ልጅነቱ መጥቶበት እጆቹን በኪሱ ከቶ ራመድ ሊል ሲል ብሮቹ እጁ ውስጥ ገቡ አውጥቶ ሲያየው ብዙ ብር ነው ። ጊዜ አልወሰደም ሮጦ ሰውየው ጋር ሄደ አባባ ጃኬቱ ኪስ ውስጥ ብዙ ብር ነበር እንካ አለው ። ሰውየውም ችግር የለም ረስቼው አይደለም አውቄ ነው ለእናትህ ስጣት አለው ። ልጁም አስደንጋጭና አስገራሚ መልስ ሰጠው ።
ቅድም እንድሰራ አበረታተኸኝ አሁን ግን እንድለምን እያደረግኸኝ ስለሆነ አልፈልግም እንካ ብሎት ብሮቹን ጥሎበት ሄደ ። ሰውየውም በሰማውና ባየው ነገር ተገርሞ ልጁን ይዞ ወደ ሱቅ ሄደ ። !!!
ሱብሓነላህ ለልጁ ብሩህ አእምሮና ለሰውዬው ቅን ልቦና የሰጠ ጌታ ጥራት ይገባው ። ለመሆኑ ምን ተሰማችሁ ?
አላህ በተሰጠን ፀጋ ወደርሱ የሚያቃርብ ስራ የምንሰራ ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka