💙 ምኞቴ 🔸
#ክፍል_ 1️⃣9️⃣
አለቻት እሺ እደውልልሻለው ኤዲዬ ደህና ሁኝ ብላ ረዲ ስልኩን ዘጋችው።
...ቢኒያም ከስራ መጥቶ ወደ ቤቱ ሲገባ ኤዲ ቤት የለችም፡፡ "ኤዲ...ኤዲዬ!" እያለ ተጣራ
ምናልባት ወደ ጓዳ ዉስጥ እንደሆነች ብሎ ኤዲ ግን የለችም ነበር፡፡ ወደ ዉጭ ወጣና
እማማ በለጡን ተጣራና...
..."ኤዲ የት ሄዳ ነዉ?" አላቸዉ፡፡ እማማ በለጡም
..."እ...ሐኪም ቤት ሄዳ ነዉ፡፡" አሉት፡፡ ቢኒ ድንግጥ አለ፡፡
..."መቼ? ምን ሆና? ምን አገኛት? እና አትከተሏትም ነበር ወይም አደዉሉልኝ?" እያለ ጥያቄ
በጥያቄ ላይ እየደራረበ እማማ በለጡን የጠየቃቸዉን ጥያቄ የመመለሻ አፍታ አሳጣቸዉ፡፡
ይሄን ከማለቱ ወዲያዉ የግቢዉ በር ተከፈተና ኤዲ መጣች፡፡ በጣም አምሮባት፤ ከደስታ
ብዛት ፊቷ ላይ ፀሐይ የወጣች እስኪመስል ድረስ አብርታለች፡፡ በረዶ የሚመስሉት ነጫጭ
ጥርሶቿ ይፍለቀለቃሉ፡፡ ቢኒያም እንዳያት በጣም ደስ አለዉ፡፡ አሟት ነበር የመሰለዉ እሷ
ግን እንደጨረቃ ፈክታ፤ ከፀሐይ አብርታ ብቅ አለች፡፡ ገና የነጋ መሰለዉ፡፡ ለሱ ንጋቱ ኤዲ ነች፡፡ ያለ ኤዲ ሁሌም ጨለማ ነዉ የሚሆንበት፡፡ ወደነሱ ቀረበችና..."ቢኒ ና ወደ ቤት እንግባ" ብላዉ እጁን ይዛ ሳበችዉ፡፡ ሰላምታ እንኳን አልሰጠቻቸዉም ነበር፡፡ ደስታ አስክሯታል፡፡ ቢኒም ምንም አልተናገረም ዝም እንዳለ ተከተላት፡፡ እማማ በለጡ ..."ኤዲዬ ደህና መጣሽ?" ፊቷን ሳታዞር ወደ ቤቷ እያመራች "አዎ እማማ" አለቻቸዉ፡፡ ዉስጧ የሆነ ነገር አለ፡፡
ለቢኒያም እስከምትነግረዉ ቸኩላለች፡፡ ቤት ከገቡ ቡኋላ እየተፍለቀለቀች በደንብ ሳቀች፡፡
..."ኤዲዬ ምን ተገኝቶ ነዉ? ሆስፒታል አይደለም እንዴ የሄድሽዉ" አላት ቢኒ
..."አዎ ሆስፒታል ነበር የሄድኩት" አለችዉ
..."ምንሽን አሞሽ ነዉ?"
..."ሆዴን"
..."ወይኔ በፈጣሪ እንዴት አደረገሽ የኔ ፍቅር" ብሎ እጆቹን ሆዷ ላይ አድርጎ አይን አይኗን
ያያታል፡፡ ኤዲ አሁንም ጥርስ በጥርስ እንደሆነች ናት፡፡ የምትስቀዉ እሱን ላለማስጨነቅ
እንደሆነ አድርጎ ነዉ ያሰበዉ - ቢኒ፡፡
..."የኔ ፍቅር" አለችዉ ድምፅዋን ለስለስ አድርጋ
..."ወዬ የኔ ቆንጆ"
..."የሆነ ነገር ልንገርህ?"
..."አዎ ንገሪኝ ፍቅሬ...ምንድን ነዉ እሱ?" እያለ ይመለከታታል፡፡
..."የ ሶስት ወር እርጉዝ ነኝ!" አለችዉ፡፡ ቢኒ የሰማዉን ማመን አቃተዉ፡፡ አራት አመት
እምቢ ብሏት እንዴት አሁን??
..."እዉነትሽን ነዉ ኤዲዬ? ለማረጋገጥ ያክል ጠየቃት፡፡ ኤዲ ለአዎንታ እራሷን ነቀነቀች፡፡
ቢኒ ምድር ጠበበችዉ፡፡ ኤዲን እቅፍፍፍ አደረጋት፡፡ ሰዉነቷ ላይ ጥምጥም ብሎባት ይስማት ጀመር፤ ግንባሯን...፤ አይኗን...፤ ጉንጯን...፤ አፍንጫዋን...፤ ከንፈሯን...የቀረዉ የለም፡፡ በየመሃሉ እየጮኸ 'ፈጣሪ ሆይ ተመስገን' ይላል።ኤዲም ትፈለቀለቃለች፡፡ ደስታ ቢገድል ኑሮ ከቢኒ ቀድማ ትሞት ነበር፡፡ ከምንም በላይ ያስደሰታት መፀነሷ ሳይሆን ቢኒያም እንደዚህ ሲደሰት ማየቷ ነዉ፡፡ በርግጥ የደስታዉ
ምንጭ ማርገዟ ቢሆንም...፡፡ቢኒ አሁንም እየጮኸ ጌታዉን ማመስገኑን አላቋረጠም፡፡ 'ጌታ ሆይ አመሰግንሀለው' እያለ ላንቃዉ እስኪበጠስ ድረስ ይጮሃል፡፡ እንደገና ቀጥ ብሎ ፈቲን በመሳም
ያጣድፋታል፡፡ ደስታቸዉ እንደቀጠለ ነዉ፡፡...
.
...ኤዲና ቢኒ ከዚያ ሁሉ ፈንጠዝያ ቡኃላ አብረዉ ቁጭ ብለዉ ራት እየበሉ ረዲ ደወለች፡፡
ቢኒም ስልኩን በኤዲ ሊያስነሳዉ አለና ..."ሆ ሆ ነገሩ እናንተ ወሬ ከጀመራችሁ ስለማታበቁ
እኔ ካዋራኃት በኃላ እሰጥሻለሁ" ብሏት ስልኩን አንስቶት ረድኤትን ማወራት ጀመረ፡፡ እያወሩ
እያለ ኤዲ አላስወራም አለችዉ፡፡ በትክክል እንዳያወራ ታጎርሰዋለች፡፡ በመሃል ትስመዋለች
ቅብጥ ቅብጥብጥ አለችበትና ረበሸችዉ፡፡ ቢኒም "ዉይ እንቺ እስኪ አዉሪያት" ብሎ
ስልኩን ሰጣት፡፡
... ኤዲና ረዲ ማዉራት ጀመሩ፡፡
..."ረዲዬ ራት እየበላን ነዉ፡፡ እንብላ አለቻት ኤዲዬ የተባረከ ይሁን ብሉ እሄ ቢኒ ሽሮ እንኳን መስራት አይችልም ስትላት ሁለቱም ተሳሳቁ በተለይ የኤዲ ሳቅ ከስከዛሬዉ ለየት ያለ ነበር፡፡ ፍንድቅድቅ አለች፡፡
..."ደግሞ ለሽሮ ሌላም አስተምረዋለሁ" አለቻት ረዲ ለፈቲ
..."ሌላ ሌላዉንማ እኔ አስተምሬዋለሁ" ብትላት በሳቁ ላይ ቢኒም ተሳትፎ ነበር ከት
ብለዉ ሳቁ፡፡ ሃሃሃሃ ሂሂሂ ኪኪኪኪ ...
..."ሆ" አለች ረዲ ..."ራትሽን የምትበይዉ ምላስ ነዉ እንዴ ወሬ ለቆብሻልሳ"
..."እረ እሱን ተይዉና ...ይልቅ የምወልዳት ልጅ ሴት ከሆነች ያንቺ ሞክሼ ነዉ የማረጋት ረድኤት ...እላታለሁ፤ ወንድ ከሆነ ግን ቢኒ ነው ስም የሚያወጣለት፡፡" ስትላት ረድኤት ደነገጠች፡፡
..."ኤዲዬ አረገዝሽ እንዴ?"
..."ዉይ ረዲዬ በደስታ ብዛትኮ የነገርኩሽ መስሎኝ ነዉ፡፡ አርግዣለሁ፡፡ ዛሬ ሆስፒታል ሂጄ የሶስት ወር እርጉዝ ነሽ አሉኝ" አለቻት፡፡ ረድኤት...
#ክፍል 20 ይቀጥላል... LIKE ❤️ & Share✅ በማድረግ ታሪኮቹን በፍጥነት ያግኙ።ዮሀንስ...🤌🤍
@Jo_21_19🥀ᴊᴏɪɴ & ꜱʜᴀʀᴇ🥀
🔔
@Kurach_kalat💭
📣
@Kurach_kalat💬