የማለዳ ትምህርት
ቀን 04/03/2017 ዓ/ም
ርዕስ፦ ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ ኢግዚአብሔር ተራራ እንውጣ
ውድ የማራናታ ቻናል ተከታዮች እንደምን ሰነበታችሁ የምህረቱ ባለጠጋ አምላክ ከፊቱ እኛን ሳያጣፋ ይህችን ቀን በምህረቱ ባርኮ የሰጠን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላዓለም ይባርክ እያልኩ ወደ ዛሬ መልእክት አልፋለሁ የዛሬ ርዕስ፦ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ እግዚአብሔር ተራራ እንውጣ በሚል ርዕስ እንማራለን።
በመሠረቱ ተራራ ማለት የማይታይና የተጋረደ ነገር ሁሉ ጎልቶ የሚታይ ከፍ ያለ ቦታ ነው። ስለዚህ ሁለት የከፍታ ተራሮች እንዳሉ በእግዚአብሔር ቃል እንረዳለን። ደግሞም ማንኛውም ሰው ከዚህ ከሁለቱም ተራራ ማምለጥ አይችልም። ይህ ማለትም አንድ ሰው አንዴ የሰይጣን መውጣት አለበት ወይንም ከዛ ወርዶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ መውጣት አለበት፣ ምርጫው ግን እንደ ሰው አረዳድ ይለያል። በእሥራኤል ዘመንም የመረገም ወይም የሰይጣን ተራራና የበረከት ወይም የእግዚአብሔር ተራራ በመባል የሚታወቁ ሁለት ትላልቅ ተራሮች እንዳሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገረናል የእነዚህ ተራሮች ስም፦ የበረከተ ተራራ ገሪዛን ተራራ ሲሆን የመረገም ተራራ ደግሞ ጌባል ተራራ በመባል ይታወቃሉ። ከዚህ በታች በሰፈው እንመለከታለን፦
ዘዳ 11: 29፦አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ።
ሁለቱንም ተራራ እንመልከት
1, ሰይጣን የሚያወጣ ተራራ፦ የግብዝነት ተራራ /የውሽት/ የሙስና/ የአመንዝራ/የጣኦት ማምለክ ተራራ ይባላሉ። ይህ ተራራ ጊዜያዊ ስሆን በመጨረሻም የውርደት ይሆናል።
ይህንን ተራራ የወጣ ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ትዕብተኞችን ይቃወማል ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣልና።
የማቴ ወ 4፥8፦....ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።
9፦ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
10፦ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።
11፦ያን ጊዜ ዲያቢሎስ ተወው፥ እነሆም፥ መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር።
2, እግዚአብሔር የሚያወጣ ተራራ፦ የትህትናና ሰማያዊ ተራራ/የፍቅር ተራራ የመንፈስ ቅዱስ ተራራ/ የመሠጠት ተራራ የባልንጀራህን የመወደድ ተራራ..ወዘተ ይባላሉ። እኒኝ ተራሮች ዘላለማዊና የክብር ተራሮች ናቸው። እግዚአብሔር ዝቅ የሚሉትን ከፍ ሊያደርግ ስለሚፈልግ በመጀመርያ በፊቱ ዝቅ የሚሉትን ይፈልጋል።
የማቴ ወ.17፥1፦....ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
2፤ በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
3፤ እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
4፤ ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።
5፤ እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
6፤ ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።
7፤ ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።
8፤ ዓይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም።
በዚህ በሁለቱም ቃል ክፍል የሚንረዳው ነገር፦
☞ ሰይጣን ተራራ አወጥቶ አለምን ያሳያል፦
☞ እግዚአብሔር ተራራ አወጥቶ አምላክነቱንና ሰማይን ያሳያል። ስለዚህ ምርጫችን ምን ይሁን የቱ ይሻለናል? ሰይጣን ዛሬ አለምን አሳይቶ ከፍ ከፍ አድርጎ ያከበረ ይመስላል፤ ከዛው ከተራራው ስጥል ውድቀትና መሰባበር ታላቅ ይሆናል። ስለዚህ ዛሬ እኛ ከሰይጣን ተራራ ወርደን ወደ እግዚአብሔርና እግዚአብሔር ወደሚያሳየን ተራራ መውጣት አለብን።
1ኛየጴጥ.መል.5፥5፦እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
6፤ እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
7፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
8፤ በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤
9፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
በእግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ማዋረድ ወደ እግዚአብሔር ተራራ መውጣት ነው። በእግዚአብሔር ፊት ከፍ ከፍ ብሎ ራሱን ማሳየት ግን ወደ ሰይጣን ተራራ መውጣት ነው፤ ይህንን ልዩነት ማወቅ አለብን። በቤተክርስቲያን ውስጥ ከእኔ ውጭ ማን አለ ብሎ እራሱን Specalize ማድረግ ከጀመረ አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ተራራ ወረደ ማለት ነው። ዛሬ እኔ ስዘምር፣ እኔ ስሰብክ፣ እኔ ስያመልክ፣ እኔ እኔ እኔ..... በቃ እኔ በሌለሁበት ሰአት ለዚህ Church ማን አለ? ማለትና እራሱን ከፍ ከፍ አድርጎ በልቡ እራሱን ማድነቅ ከጀመረ የሰይጣን ተራራ ወጥቶ ከእግዚአብሔር ተራራ ወረደ ማለት ነው። ለዚህ አገልጋይ መውደቁ ታላቅ ይሆናል።
ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።
ምሳሌ 16፥18
እግዚአብሔር ትህትና ዝቅታ ስፈልግ ሰይጣን ግን ግብዝነትን ይፈልጋል፤ ዋና መሣሪያው እሱ ነውና። ስለዚህ ከትህትና ወጥቶ እራሱን እያሳየ እየተመላለሰ ያለው ወንድም ዛሬ ከዛው ከከፍታው ወርዶ በትህትና ራሱን አዋርዶ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አለበት። ምክንያቱም እግዚአብሔር አጥብቆ የሚጠላው ነገር ብኖር ግብዝነት ነውና።
ስለዚህ ከሁለቱም ተራራ የሚበልጠውን በጊዜ መፈለግ ተገብ ነው። ነገር ግን የዚህ አለም ነገር ታይቶን የሰማዩን ጋርዶ እንዳንመለከት አድርጎን ከሆነ ቶሎ ንስሐ መግባት ያስፈልጋል።
(2ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 1) 8፤ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ ሆነው ቢበዙ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋልና፤
9፤ እነዚህ ነገሮች የሌሉት ዕውር ነውና፥ በቅርብም ያለውን ብቻ ያያል፥ የቀደመውንም ኃጢአቱን መንጻት ረስቶአል።
10፤ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና።
በሰይጣን ተንኮል እንዳንሰናከል መጠራታችንና መመረጣችንን እንመልከት። ደግሞም የሰማይ ተስፋችንን እየናፈቅን መመላለስ አለብን።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 15) 1፤ አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2፤ በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
3፤ በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።
4፤ ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።
5፤ ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።