"ምክር ለእህቶች"
① እህቶቼ ሆይ! እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ ተዛዘኑ፤ ተከባበሩ፤ ተናነሱ . . በተውሒድና በሱና ገመድ መተሳሰር የስኬት ሁሉ ቁንጮ ነው።ሸይጧን እናንተ መካከል ቁርሾ ለመፍጠር፤ ለማጣላት፤ ለማነቋቆር የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም! ለምን ምኞቱን ታሳኩለታላችሁ።
② እርስ በርስ በነገር አትወጋጉ!
③ ከምንም በላይ አላህን ፍሩ! «እከሊት'ኮ እከሊትኮ. .» እያላችሁ አትተማሙ!
④ በዘር፥ በሃብት በሌላም አንዳችሁ ሌላኛዋን እህት ዝቅ አትድርጉ! በዱኒያ ጉዳይ ስትጣሉ ወደ ዲንና መንሃጅ አስጠግታችሁ አትዘላለፉ! ለከት የሌለው ቀልድና መነቋቆር ይቅርባችሁ!
⑤ እርስ በርሳችሁ ያላችሁን ግንኙነት አጠናክሩ!
⑥ የዲን ትምህርቶችን ተማማሩ!
⑦ ቅንነትና ግልጽነት ይኑራችሁ!አንዷ እህት ብታጠፋ ወይንም ብታስከፋችሁ ለሌላኛዋ እህት ሄዳችሁ «እንዲህ አደረገችንኝ. .» ከምትሉ ለራሷ ቀርባችሁ ወይንም ደውላችሁ «እንዲህ እንዲህ በማድረግሽ ቅር ተሰኝቼብሻለሁ..» ብላችሁ በግልጽ አሳውቁ።
⑧ በመካከላችሁ ያሻከራችሁ ጉዳይ ካለም በግልጽ ተወያዩበት። ይቅርታም ለመጠየቅ ነፍሲያ አትያዛችሁ።
⑨ አጥፍታችሁ እንኳን ባይሆን የአላህን አጅር ፈልጋችሁበት ይቅርታ ለመጠየቅ አትፈሩ። «ይቅር በይኝ» ስትባሉ ክንፋችሁን ዝቅ አድርጋችሁ ይቅር በሉ።
①0 አንዲት እህት ጠፍታባችሁ ወይንም ካያችኋት ከቆየባችሁ ደውላችሁ አሊያም በአካል ሄዳችሁ «ምን ሆነሽ ነው እህቴ የጠፋሽው?» ብላችሁ ተጠያየቁ።
①① አንዳችሁ የአንዳችሁን ችግር ተካፈሉ፣ያስጨነቃችሁ ጉዳይ ካለ ለብቻችሁ እያብላላችሁ ከምትሰቃዩ ለእህቶቻችሁ በግል አማክሩ ተመካከሩ።
①② ማንኛችሁም በማንኛችሁም ላይ አትቀናኑ፣ሸይጧን በዱኒያ ጉዳይ በእህታችሁ ላይ የቅናት መንፈስ ካመጣባችሁ እንዲያውም እጃችሁን ወደ ላይ ዘርግታችሁ « አላህ ሆይ ለእከሊት እህቴ የሰጠሃትን ጸጋ ባርክላት!» ብላችሁ ዱዐ አድርጉና ሸይጧንን አቃጥሉት ነፍሲያችሁንም ለውስዋስ ቦታ የለሽም በሏት።
✍ወንድማችሁ አብዱል አዚዝ ገለታው
https://t.me/Abu_nuh12/1259https://t.me/Abu_nuh12/1259