ኢሕአፓ፣ የአዲስ አበባ የመንገድ ኮሪደር ልማት “ሕዝባዊ ቁጣ" ሊቀሰቅስ ይችላል ሲል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።
የኮሪደር ልማቱ የነዋሪዎችን “ሰብዓዊ መብቶች የጣሰ" መኾኑን የጠቀሰው ኢሕአፓ፣ የከተማዋ ልማትና ዕድገት ከነዋሪው "መብት መከበር” እና “ከጥቅሞቹ መጠበቅ” በተነጠለ ኹኔታ ሊታይ እንደማይገባ ገልጧል።
የኮርደር ልማቱ፣ የበርካታ ነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች፣ አነስተኛ እና ከፍተኛ የንግድ መደብሮች ማፍረሱን ኢሕአፓ በመግለጫው ጠቅሷል።
ፓርቲው፣ የከተማዋ አስተዳደር ድርጊቶች፣ የነዋሪዎችን "ኹኔታ ያላገነዘቡ" እና ምቹ ጊዜን ያልጠበቁ” ናቸው በማለትም ወቅሷል።
#ዋዜማ