አርበኛ ወ ብዕረኛው ሸህ
★★★★★★★★★
ሸህ ሰይድ ጫሌ በ1870ዎቹ መጀመሪያዎቹ አካባቢ ከአባታቸው ሸህ ኢብራሂም ያሲን እና እናታቸው ወ/ሮ ዘቡራ ሙሀመድ ይማም ተወለዱ። ሸህ ሰይድ ኢብራሂም ፣ እጅግ ሲበዛ ሊቅ ፣ ፈጣን አእምሮ የነበራቸው እና ከፍተኛ የሆነ የግጥምና የዜማ ችሎታ የነበራቸው ሰው ነበሩ።
እድገታቸው በራስ ወሌ ቤት ከእትየ መነን ጋር ሲሆን በጊዜው ከነበሩ የአካባቢ ገዥዎች ጋር ያደረጉት ትግል ፣ ከጣሊያን ጋር ያደረጉት ትግል እንዲሁም የአረብኛ እና የአጅም ፁሁፎቻቸው ሰርተዋቸው ያለፉት በርካታ ናቸው።
.
በፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግሉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ግለሰብ ሙስሊሞችና ታዋቂ የእስልምና ሊቃውንት ቁጥር እጅግ በጣም በርካታ ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጸሀፍት ስማቸው እስካሁን ተነስቶ ከማያውቁ ሊቃውንት መካከል «ከበላይ ዘለቀ» ጋር በመሆን ጣሊያንን ተዋግተው ያዋጉት ውስጥ «የጫሌው ሸህ ሰይድ ኢብራሂም» የሚጠቀሱ ናቸው።
.
ከጣሊያን ጋር በተደረገ ትግል ጋር ተግባራቸው ጎልቶ መነገር ካለበት የእስልምና ሊቃውንት መካከል የጫሌው ሸህ ሰይድ ኢብራሂም አንዱ ናቸው። እነ ሸህ ጫሌ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣሊያኖች ትኩረት ውስጥ የገቡት ሰዎች ሁሉ ለጣሊያን ገዥዎች እጅ እየነሱ የሚያልፉበት ቦታ ላይ ከበቅሎዋቸው ላይ ሳይወርዱ እና ለጣሊያን ገዢዎች ሳያጎነብሱ በማለፋቸው ነበር።
.
የጣሊያን ገዥዎች «ይህ ሰው ማን ነው እጅ ሳይነሳ የሚያልፈው?» ብለው እንደጠየቁ ከኤርትራ የመጣው ኑራ ሁሴን የሚባለው ባንዳ እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች «ይህ ሰውማ እንኳን እጅ ሊነሳ ዙፋን ለመያዝም ይከጅላል» ማለታቸውን በጊዜው የነበሩ አባቶች ይናገራሉ። ይህ የሸህ ጫሌ ለጣሊያን እጅ ባለመንሳት እና ከበቅሎ ባለመውረድ ያሳዩት ልበ-ሙሉነት እንዲሁም ለራሳቸው እና ለህዝባቸው የነበራቸው ክብር ለጣሊያን ገዥዎች አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ በተደጋጋሚ እንዲገደሉ ውሳኔ ተላልፎባቸው ነበር። ነገር ግን ከነበራቸው ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ተቀባይነት አንፃር እርሳቸውን ይዞ ለመግደል ቀላል ሆኖ አልተገኘም።
.
ይዞ ለመስቀል ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን መደበኛ ያልሆኑ ድርድሮች ነበሩ። ሸህ ኦራ የሚባሉት ታላቅ ሊቅ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሸህ ጫሌ ከጣሊያኑ ገዥ ጋር ለመገናኘት እና ለመነጋገር ቀጠሮ ያዙ። በቀጠሮው መሰረት በወሎ ወረባቦ አካባቢ ሲገናኙ ጣሊያናዊው ገዥ ከነ ልጁ እንዲሁም ኤርትራዊው ባንዳ ኑር ሁሴን በተገኙበት ቤት ውስጥ እንዲገኙ ተደረገ። ሸህ ሰይድ ጫሌ ወደ ቤት ሲገቡ ኤርትራዊው ባንዳ ሰይፍ በእጁ ይዞ ከጣሊያናዊው ገዥ ፊት ለፊት ቆሞ ነበር።
.
በግንኙነታቸውም ወቅት የባንዳውን ሁለት እጅ በመያዝ ሰይፉን ከቀሙት በኋላ «ሰው እየያዘልህ ነው የምታርደው በጀግንነት?» ብለውት ከቤት በመውጣት በበቅሏቸው ግቢውን ለቀው ሄዱ።
በወቅቱ ጣላናዋዊ ገዥ እና ባንዳዎቹ በመደናገጣቸው በነበሩበት ቤት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ዝምታ ሰፈነ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የገዥው ልጅ ከበር በመውጣት እርሳቸው በሄዱበት አቅጣጫ ጥይት ቢተኩስም ሳያገኛቸው ቀረ። ይሁንና ሸህ ሰይድ ጫሌ ለፈፀሙት ተግባር እንደምንም ተይዘው እንዲሰቀሉ በድጋሜ አዋጅ ተላለፈ።
.
.
ከዚህ ጊዜ በኋላ የሸህ ጫሌ መልስ ለየት ያለ እና በወቅቱ ሊታሰብ የማይችል ነበር።
ሸህ ሰይድ ኢብራሂም ጫሌ ያላቸውን ከፍተኛ የሆነ የግጥም እና የዜማ ችሎታ በመጠቀም ብዕራቸውን በመምዘዝ ጣሊያንን እና አገዛዙን በይፋ የሚያወግዝ የዱዓ መንዙማ ጻፉ፤ በይፋም አዜሙት።
.
ሸህ ሰይድ ጫሌ መንዙማውን የጻፉት በአረብኛ ቋንቋ ቢሆንም ቢያንስ በዙሪያቸው ያሉ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎቻቸውና በመላ ሀገሪቱ ያሉ በርካታ ሺ የእስልምና ሊቃውንትን ግንዛቤ ለመቀየር የራሱን አስተዋጽኦ እንዳደረገ መገመት ይቻላል።
ከመንዙማው ግጥሞች የተወሰኑትን ስንኞች ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉም ለመመልከት ያክል መንዙማው የሚጀምረው በሚከተለው ርዕስ ነው።
.
.
» ህያው አሸናፊ የሆንከው አምላኬን » እለምንሀለው እንድታስወግደው ጭንቀቴን ስጋቴን
.
በዚህ ርዕስ የሚጀምረው መንዙማ በርካታ ስንኞች ቢኖሩትም ለምሳሌ ያክል በአማርኛ በቀጥታ በመተርጎም እንደሚከተለው ቀርቧል።
.
ከተንኮለኛ በዳይ ካህዲ በዙሪያው ካሉት ቆሻሾች ፍርድ ጠብቀን አላህ ሁላችንንም በአንድ እንደው ተሰብስበው አገሩን ወረሩ አንተን የማይፈሩ ገራፊዎች ሁሉ ስንቱን አቆሰሉ ስንቶቹን ገደሉ በየ አካባቢው ሰው እየሰለሉ በሩቅ ተንተግታጊ ጦር እየሰበቁ በነዚህ መናጦች ስንት ሰዎች አለቁ ስንቶቹ ህፃናት ያለ ወላጅ ቀሩ ስንት የተከበረን አዋርደው ሰቀሉ አገሩን በጉልበት በኃይል እየያዙ ስንት የተከበረን ባሪያ አድርገው ገዙ ወግ ልማዳችንን እያደፈረሱ ካገር ሊያባርሩን ሊገርፉን ተነሱ ወደ ሻም ወደ ሮም እንድንሄድ ደገሱ።
.
.
እነ ሸህ ጫሌ ይህን መንዙማ ግጥም ከሰሩ ከጥቂት ወራት በኋላ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ተጠቃሎ ወጣ።
በዚህ ኪነ-ጥበባዊ መሳሪያቸው በመጠቀም ሰዎችን ከጎናቸው በማሰለፍ ከጠላታቸው ጋር ተዋግተው ለድል መብቃታቸው ሳይዘከር ከተዘነጉ የእስልምና ሊቃውንት ገድል አንዱና ዋነኛው ነበሩ ማለት ይቻላል።
.
- ምንጭ
.
(ቀደምት ኢትዮጵያውያን የእስልምና ሊቃውንት እና ኪናዊ ትውፊቶቻቸው)ን ዋቢ አድርጎ "የኢትዮጵያ ዑለማዎች ታሪክ እና አስተምህሮ" የተሰኘው ገፅ እንዳተተው
🍀🍀🍀