‹‹ፈሩትና አስፈራቸው
፤ ››
ሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ
በነሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ ዘመን እንዲህ ሆነ ፤ እርሳቸውን ጨምሮ እነ ሀጅ ራፊዕ ፣ ሸኽ ሰይድ ሙሀመድ ሳዲቅና ሌሎችም ታላላቅ ዐሊሞች በተገኙበት አንድ ለቅሶ ላይ የዳንዮች ልጅ ሸኽ አህመድ በሻሻ ሲገቡ በወግ ደምቆ የነበረው ድንኳን ፣ እንዳትተነፍሱ የተባለ ይመስል በአንድ ጊዜ ጸጥ ረጭ አለ ፡፡
እርሳቸው ዱዐ አድርገውና
ሀዘንተኞችን አጫውተው ፣ ፈቃድ ጠይቀው ገና እግራቸው ከድንኳኑ እንደወጣ ሰዎች መተንፈስ ጀመሩ ፡፡ የተቋረጡ ወጎች ቀጠሉ ፡፡ ሁኔታውን በትዝብት ሲከታተሉ የነበሩት ሀጅ
ሙሀመድ ወሌ ፡- «አሁን ማን ዝም በሉ ብሎን ነው እርሳቸው ሲገቡ ለመተንፈስ እንኳ
ያልደፈርነው?» በማለት በግርምት ጠየቁ ፡፡ የሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ መልስ ጥበብ አዘል
ነበር ፡፡ « ፈሩትና አስፈራቸው » አሉ ፡፡
አዎ ፣ አላህን የፈራ ሁሉም ይፈራዋል ፤ የአላህን ትእዛዝ ያከበረ ሁሉም ያከብረዋል ፡፡
ዑለሞቻችን በየማህበረሰቦቻቸው ዘንድ ያተረፉት ክብር አላህን የመፍራታቸው ውጤት
እንደሆነ ጥርጥር የለውም ፡፡
ከዚህ ውጭ ሌላ ምን ትርጉም ሊሰጠው ይችላል ?
መሻኢኾችን በእጅጉ የሚያከብረው ክርስቲያን ማህበረሰብ ተራውን ሙስሊምም ከልብ ያምን ነበር ፡፡ ከርሱ ዘንድ አደራ ያስቀምጣል ፡፡ «ሙስሊም አይዋሽም ፤ አደራ አያጎድልም
፤ ቃሉን አይበላም » የሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ክርስቲያን ማህበረሰብ የዘመናት አምነት
ነበር ፡፡
ሙስሊም ዋሸ ፣ ቃሉን አጠፈ…ማለት ለአገሬ ክርስቲያን 8ኛው ሺ ደረሰ ፤ ዘመን ጠለሸ ፤
ጊዜ ተበላሸ ማለት ነው ፡፡
ይህን ዕምነቱን ከገለጸባቸው ሥነ-ቃሎች መካከል አንደኛው ፡-
«እስላም ካበለ ቀኑ ዘነበለ» ይላል ፡፡ ‹‹ሙስሊም ከዋሸ ዘመን ተበላሸ›› ማለት ነው ፡፡
የጥንቶቹ ሙስሊሞች በሌላው ወገን ዘንድ የነበራቸውን መታመን የጥንቱ የጎንደር አዝማሪ
በግጥሞቹ እንዲህ ገልጾታል ፡-
እስላም አልኩሽ እንጅ እጁ የሚታመን ፤
ሸማኔማ ሞልቷል ደግሞ ለመሸመን፤
ከኑረዲን ዒሳ ‹‹የባንዴራ ታሪክ›› ግጥም የተቀነጨበች ፡፡
በዳኖች ዘመን ዑለሞች እስልምናን በወጉ ተገበሩ ፤ እንዲህም ገዘፉ ፤ ህዝባቸውንም
አስተምረውና አስተግብረውም አስከበሩ ፡፡ ያን የማህበረሰባችንን ገጽታ ፣ ያን የታሪካችንን
ከፍታ እንዴት እንመልሰው ?
ሚስጥሩን ሸኽ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ በጥቂት ቃላት አጠቃለውታል ፡-
‹‹ፈሩትና አስፈራቸው
፤ ›› አላህን ፈርተን ፣ ትዕዛዙን አክብረን የምንከበር ያድርገን ፡፡
ታሪካችንን የመረዳት ጥበብም ይስጠን ፡፡ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እንዳሉት፡- ‹‹ታሪኩን የማያከብር ትውልድ ታሪክ አይሰራምና›› ታሪካችንን አክብረን ታሪክ ለመሥራት ያብቃን ፡፡ ወይም በኔ መረዳት ፡-
‹‹ትላንት የሌለው ነገ የለውምና›› ነጋችን እንዲያምር ትላንታችንን በወጉ አላህ ያሳውቀን
Copy
@ethio_mus