የሴቶችን አቅም ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነዉ
=====================================
(መስከረም 22/2014ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሴት ሰራተኞችን አቅም፣ ክህሎትና ተሳታፊነት ለማሳደግ እንዲሁም ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ ለሴት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቢሾፍቱ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።
ወ/ሮ ማህሌት በቀለ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ስልጠናዉ በጾታ፣ ስርአተ ጾታ እና አስቻይ ህጎች ዙሪያ ለተቋሙ ሴት ሰራተኞች የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
አላማዉም ስርአተ ጾታንና የሴቶችን ጉዳይ በሁሉም ስራ ላይ ለማካተት፣ የሴቶችን አደራጃጀትና ተሳትፎ ለማሳደግ ነዉ ብለዋል።
ወ/ሮ ማህሌት አያይዘዉም ይህ ስልጠና በተለይም ሴቶች በተናጠል ከሚደረገዉ እንቅስቃሴ ይልቅ ተደራጅተዉ ያላቸዉን ችሎታ፣ እዉቀትና አቅም በጋራ በመንቀሳቀስ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ እንዲሁም ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥና ተሳትፎቸዉን ለማሳደግ የሚረዳ ነዉ ብለዋል።
በስልጠናዉ የተቋሙ ሴት አመራሮች፣ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።