“መንግስት እየሰጠን ያለውን ከፍተኛ ተልእኮ በተለመደው አሰራር ልናሳካው አንችልም” - አቶ ፍቃዱ ታደሰ (በገቢዎች ሚኒስቴር የሚንስትር ጽ/ቤት ኃላፊ)
ታሕሳስ 14/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴርስትር ጽ/ቤት በስራዎች አፈጻጸም እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት አካሂዷል።
ውይይቱን የመሩት የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ በቅርቡ በሚኒስቴሩ የአመራር ሽግሽግ መደረጉን ጠቁመው የአመራር ትውውቅ እና የስራ ውይይት ለማድረግ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
በጽ/ቤቱ ስር የሚከናወኑ ስራዎች ለገቢ አሰባሰቡ ውጤታማነት ያላቸው ድርሻ ከሚገመተው በላይ ነው ያሉት ኃላፊው ስራዎችን በጥንቃቄ በመምራት እና ከእለታዊ ስራዎች መጠመድ በመውጣት ተቋሙን በሚያሻግሩ ብሎም ለተሻለ ውጤት በሚያበቁ ስትራቴጂክ ስራዎች ላይ አተኩሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
አቶ ፍቃዱ አክለውም አሁን ላይ በመንግስት አየተሰጠ ካለው ከፍተኛ ተልእኮ አንጻር በተለመደው አሰራር ሊሳካ አይችልም ብለዋል። በመሆኑም ይህን ታሳቢ ያደረገና ደረጃውን የጠበቀ እቅድ ከልሶ ማዘጋጀት እና ለሌሎች አርዓያ ሊሆን የሚችል ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆን አለብን ብለዋል። በተጨማሪም ጽ/ቤቱ ከሌሎች የሚኒስቴሩ ዘርፎች እና ቢሮዎች ጋር በቅንጅት ስራዎችን በጋራ የመምራት ኃላፊነት አለበት ብለዋል፡፡
በእለቱ የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ስራዎች ዙሪያ መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።