የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ የሚጠቀም ታክስ ከፋይ ኃላፊነት
ታሕሳስ 15/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 149/2011 መሠረት
1/ ታክስ ከፋዩ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ጥቅም ላይ ለማዋል ሶፍትዌር
በሚያለማበት ጊዜ በሶፍትዌሩ ከመጠቀም በፊት የሶፍትዌር
ፕሮግራሙን ያለማውን ሰው ለታክስ ባለስልጣኑ ማሳወቅ እና
የሶፍትዌር ፕሮግራሙን ማቅረብ አለበት፡፡
2/ የታክስ ባለስልጣኑ በተራቁ 1 በተገለጸው መሰረት የቀረበለት የደረሰኝ
ሶፍትዌር ፕሮግራሙ ለታክስ አስተዳደሩ አመች መሆኑን በማረጋገጥ
ሶፍትዌር ጥቅም ላይ እንዲውል ሊፈቅድ ይችላል፡፡
3/ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ እንዲጠቀም የተፈቀደለት ታክስ ከፋይ
የተጠቀመበትን የሽያጭ እና ወይም የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ብዛትና
ቁጥር በመግለጽ በየሩብ ዓመቱ ታክስ ለሚከፍልበት ቅ/ጽ/ቤት
ሪፖርት ማቅረብ አለበት፡፡
4/ ይህ መመሪያ ከመውጣቱ በፊት የደረሰኝ ሶፍትዌር አልምቶ
የሚጠቀም ታክስ ከፋይ ሶፍትዌሩን ለታክስ ባለስልጣኑ ማስመዝገብ
እና እውቅና ማግኘት አለበት፡፡