ሴቶችን በአመራርነት እና በውሳኔ ሰጪነት ተሳትፎ ለማብቃት እየተሰራ ነው
ታሕሳስ 15/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
በገቢዎች ሚኒስቴር የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከክልል፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተውጣጡ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች በአመራርነት እና ውሳኔ ሰጪነት ዙሪያ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ቀጥሏል፡፡
በዚሁ መሰረት የገቢዎች ሚኒስቴር ከክልል፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ለተወጣጡ ሴት አመራሮች እና ሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን ያስጀመሩት የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ታደሰ ሴቶችን ወደ አመራርነት እና ውሳኔ ሰጪነት ለማምጣት እንደዚ አይነት ስልጠናዎች አጋዥ ናቸው ብለዋል፡፡
በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ሞገስ በበኩላቸው ስልጠናው ሴቶች በአመራር እና በውሳኔ ሰጪነት የተሻለ ተሳትፎ እና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን የህይወት ተሞክሮአቸውን ያካፈሉ ሲሆን በህይወት ክህሎት፣ በራስ መተማመን ፣ የመግባባት ችሎታ እና ሴቶች በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ውጤታማ መሆን በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በታደሰ ኢብሳ
ፎቶ፡- የትናየት እንዳያፍሩ