Muhammed Computer Technology (MCT)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው!
በዚህ የቴሌግራም ቻናል ጥሩ ጥሩ ስለኮምፒውተርና ቴክኖሎጅ መረጃዎች እና እውቀቶች ይለቀቃሉ ያለዎትን እውቀት ያሳድጋሉ
አስተያየት ካላችሁ @mctplc ልታገኙኝ ትችላላችሁ
በተጨማሪም የ YouTube ቻናል 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ
ጥሩ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


በማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ አጭበርባሪዎች በዝተዋል፤ ይጠንቀቁ!
******
አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመርን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የተለያዩ ማጭበርበሪያ ዘዴዎችን ተጠቅመው የመረጃና ገንዘብ ምዝበራ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡
አጭበርባሪዎች ከሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች ጥቂቶቹን እና መከላከያ መንገዶችን እንጠቁማችሁ፡፡

1. ፊሺንግ (Phishing)

በዚህ የሶሻል ምህንድስና ጥቃት አጭበርባሪዎች ማኅበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በተለያዩ ዲጂታል የመልእክት መለዋወጫ መንገዶች ሀሰተኛ መልእክቶችን በመላክ ተጠቃሚዎች የግል እና ሌሎች እንደ ሂሳብ፣ የይለፍ ቃል የመሳሰሉ መረጃዎቻቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ፣ እንዲሁም አደገኛ ሊንኮችን እንዲከፍቱ እና ሶፍትዌሮችን እንዲጭኑ ያደርጋሉ፡፡

2. የኢንቨስትመንት ማጭበርበሮች (Investment Scams):

የውሸት በሆኑ ወይም በሌሉ ምርቶች ወይም ንግዶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያበረታቱ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ማስታወቂያዎች ተበራክተዋል። ብዙዎችም የምዝበራ ሰለባ ሆነዋል፡፡

3. ነፃ የሙከራ አገልግሎቶች (Free Trial Products):

በሀሰተኛ የምርቶች ነጻ ሙከራ (Free-trial) ማስታወቂያ ሰዎችን በማታለል ለነጻ የምርት ሙከራው እንዲመዘገቡና የክፍያ ካርድ መረጃቸውን እንዲያስገቡ የማድረግ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው፡፡ ተጠቂው ከሱ እውቅና ውጪ ውል ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ክፍያ ያለባለቤቱ እውቅና ተቀናሽ ይሆናል።

4. የኦንላይን ግብይት ማጭበርበሮች

በኦንላይን ግብይት የተለያዩ ምርቶችን በቅናሽ እንሸጣለን በሚል የምዝበራ ተግባር ላይ የተሠማሩ አጭበርባሪዎች አሉና ይጠንቀቁ፡፡

5. ክሊክቤይት (Clickbait)፡

ይህ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጠቃሚዎችን ትኩረት የሚስቡ ጉዳዮችን የያዙ ይዘቶችን በማውጣት ተጠቃሚዎች ይበልጥ ለማወቅ ሊንኩን እንዲጫኑ የማድረጊያ ዘዴ ነው፡፡ ይህን ዘዴ አጭበርባሪዎች ሲጠቀሙበት ተጠቂው ጥቃት አድራሾቹ ወደ ሚመሩት ማስፈንጠሪያ በሚገባበት ጊዜ የግል መረጃውን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።

6. የውሸት ጓደኛ ጥያቄዎች (Fake Friend Requests)፡

አጭበርባሪዎች የማኅበራዊ ሚዲያ አካውንቶችን በመክፈት ወይም የሌሎችን አካውንቶች በመጥለፍ ወደተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የጓደኝነት ጥያቄ ይልካሉ። እነዚህን ጥያቄዎች መቀበል የእርሶን እና የጓደኞቻችሁን መለያ እንዲጠለፍ እና የግል መረጃ እንዲያፈተልክ ያደርጋል።

7. የሥራ እድል ማጭበርበሮች

ሀሰተኛ የስራ እድል ማስታወቂያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት ይተዋወቃሉ። ገቢዎን ያሳድጉ ወይም ከቤት ሆነው ሥራ ይስሩ በማለት አጓጊ ጥቅማጥቅሞችን በመንገር ተጠቃሚው ቶሎ ውሳኔ እንዲወስን (sense of urgency) በማድርግ ማጭበርበሩን ይፈጽማሉ።
እነዚህ አጭበርባሪዎች የተጠቃሚውን መረጃ የግል እና ሊሎች መረጃዎች ይወስዳሉ ወይም ለሥልጠና ወይም ለሌላ ጉዳይ በቅድሚያ ክፍያ ይጠይቃሉ።

8. ስጦታ

በራሳቸውም ሆነ የሌሎችን ስምና ዝና በመጠቀም ሀሰተኛ የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመክፈት ተከታይ ስትሆኑ፣ ተከታይ ስታስገቡ፣ ልጥፎችን ስታጋሩ፣ አስተያየት ስትሰጡ፣ ስትወዱ ስጦታ እንሰጣለን በሚሉ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ያጭበረብራሉ፡፡ እነዚህ አጭበርባሪዎች የተከታዮችን ግላዊ መረጃ ለመውሰድ መልካም አጋጣሚ ይሆንላቸዋል፡፡

እንዴት ከአጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ?

• ከማያውቁት ግለሰብ የሚደርስዎትን የማኅበራዊ ሚዲያ እንወዳጅ ጥያቄ አይቀበሉ፡፡
• የቅናሽ ማስታወቂያዎችን በጥርጣሬ ይመልከቱ፤
• በኦንላይን ብቻ ለተዋወቁት ግለሰብ ገንዘብ አይላኩ፡፡
• በማኅበራዊ ሚዲያ የግል መረጃዎን አይስጡ።
• የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን ህጋዊነት ሳያረጋግጡ ምንም አይነት እርምጃ አይውሰዱ፡፡
• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ።
• ከማያውቁት አካል በሚደርስዎት አጭር የፅሁፍ መልእክት፣ ኢሜይል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልእክት የሚያገኙትን ማስፈንጠሪያ (link) አይክፈቱ፡፡
• ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፡፡




ጎግል ፕሌይ ስቶር ብልሽት ለማስተካከል

✅ Google Play Store በአብዛኛዎቹ የAndroid ዘመናዊ ስልኮች ላይ ተጭኖ የሚመጣ ሲሆን በሆነ ምክንያት በዲቫይሱ(ስልክ ወይም ታብሌት) ላይ መሥራት ሊያቆም ሊያጋጥም ይችላል፡፡

✅ በዚህም ምክንያት በዲቫይሱ ላይ የተጫኑ ሶፍትዌሮችን የቅርብ ግዜ ማድረግ፣ ሶፍትዌሮችን ዳውንሎድ አድርገን መጫን እና አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን የቅርብ ግዜ ማድረግ አንችልም፡፡

✅ Google Play መደብር በእርስዎ ዲቫይስ ላይ የማይሰራ ከሆነ ችግሩን ለመፍታት አንዳንድ መንገዶችን እጠቁማለሁ

1. የዲቫይሱን ቀን እና ሰዓት ቅንብር(ሴቲንግ) ያስተካክሉ
የተሳሳተ ቀን እና የጊዜ ገደብ ሲኖርዎት የGoogle አገልጋዮች ከአሳሽዎ ጋር ማመሳሰል ችግሮች ያጋጥማቸዋል ለማሰተካከል ወደ ሲስተም ሴቲንግ በመሄድ «ቀን እና ሰዓት» ማስተካከል ይጠበቅብዎታል፡፡
“Automatic date & time” and “Automatic time zone” እንዲሰራ ክፍት ያድርጉ ወይም ማኑዋሊ ቀን እና ሰዓት ያስተካክሉ፡፡

2. ጎግል ፕሌይ ስቶር ከዚህ በፊት ይዞት የነበረውን ዳታ ማጽዳት
በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ከዚህ በፊት ተጠቅመናቸው የነበረው ሶፍትዌሮች ዝርዝ ይዞ ይቀመጣል(Cached data) ይሄ በምንፈልገው ጊዜ በፍጥነት ለመክፈት ኢንተርኔት ግንኙነቱ ፍጥነት ባይኖረውም ይረዳናል ነገር ግን Cached data አንዳንድ ጊዜ በPlay Store ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡

✅ በGoogle Play ላይ Cached data ለማጽዳት እነዚህን ደረጃዎች ይከተሉ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: ስቶሬጂ በመክፈት “CLEAR CACHE“.

3. የቅርብ ግዜ የሆነ ጎግል ፕሌይ ስቶር መጫን
በየጊዜው ሶፍትዌሮችን የሚሰሩ ዴቨሎፐሮች ለሰሩት ሶፍትዌር የቅርብ ግዜ ማድረጊያ አብዴተር የሚለቁ ሲሆን በዚህ የቅር ማድረጊያ ላይ የተለያዩ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ይካተታል፡፡.
በተመሳሳይ መልኩ Google የ Play ስቶር አብዴተር በየጊዜው የሚያወጣ ሲሆን እንደሚኖሩበት አገር የሚለቀቀው አብዴት ሊዘገይ ይችላል በቀጥታ የቅርብ ማድረጊያውን(APK ፋይል) ማግኘት ከቸኮሉ APKMirror በማለት ኢንተርኔት መጠቀሚያ ብሮውዘር ላይ ፈልገው ማውረድ ይችላሉ፡፡

4. ጎግል ፕሌይ ስቶር ወደነበረበት የመጀመሪያው ቨርዥን መመለስ
አንዳንዴ የቅርብ ጊዜ የተደረገ የጎግል ፕሌይ ስቶር ስሪት በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ስለሆንም አብዴት የተደረገው በማጥፋት ዲቫይሱን ስንገዛ የነበረውን(factory version ) ጊዜ መመለስ፡፡ እነዚህን ደረጃዎች በመከተል እናጥፋ:
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Uninstall Updates”

5. ጎግል ፕሌይ ሰርቪስ መስራቱን ማረጋገጥ
Google Play Services ዋናው ተግባራት የGoogle አገልግሎቶች የሆኑትን Google Play ስቶር፣ ጎግል ማፕ፣ ጎግል ፕላስ ወዘተ አገልግሎቶች አውቶማቲካሊ ግንኙነት እንዲያደርጉ እና አብዴት የሚያደርግ የሚረዳ በመሆኑ እንደ ተጨማሪ መፍትሄ በመውሰድ Google Play Services መስራቱን ያረጋግጡ፡፡

6. ጎግል ፕሌይ ስቶርን ዘግቶ መክፈት
ይህ በአብዛኛው ተጠቃሚዎች የሚተገበሩበት የተለመደ ዘዴ ነው፡፡ ማድረግ ያለብዎት ነገር Google Play Storeን በመዝጋት እንደገና ማስጀመር( ለሌሎች አፕ ይሰራል) ችግሩን ሊፈታው ይችላል
ደረጃ # 1: ሲስተም ሴቲንግ
ደረጃ # 2: አፕስ (Apps)
ደረጃ # 3: Google Play Store ይክፈቱ
ደረጃ # 4: “Force Stop” የሚለውን በመጠቀም መዝጋት እና እንደገና ይክፈቱ

7. ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት
ዲቫይሱን አጥፍቶ ማብራት ተመራጭ መፍትሄ ሲሆን ብዙውን ግዜ ይሰራል ምክንያቱም ስማርትፎን ስልኮች አጥፍተን ዳግም ማስጀመር በዲቫይሱ ላይ ያሉትን አፕ ያረጋጋል፡፡ በተቻለ መጠን አንድ አፕ ከወትሮው የተለየ ተግባር ካመጣ ዳግም አጥፍተን ስናስጀምር የተሻለ አፈጻጸም እና ችግሩን መፍታት ይችላል፡፡

8. ዲቫይሱን አንድሮድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ዳግም ማስጀመር
ከላይ በጠቀስኩት መፍትሄ ምንም የማይሰራ ከሆነ ዲቫይሱን ፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ማድረግ በዚህ ሂደት በዲቫይሱ ላይ ያሉትን ዳታ፣ የተጫኑ አፕሊኬሽን ሶፍትዌር እንደዚሁም የተጠቃሚውን አካውንት የመሳሰሉትን ሁሉ ያጠፋል፡፡
በርካታ ችግሮች በዲቫይሱ ላይ ካልገጠመዎት በስተቀር የፋብሪካ ዳግም ማስጀመር (hard reset) ባትጠቀሙ እመርጣለሁ ዳግም ለማስጀመር ከወሰኑ ሚሞሪው ያውጡ መጠባበቂያ መውሰድዎን አይርሱ፡፡

ይሄን ችግር ለመፍታት ሊያግዝ የሚችል የተሻለ መፍትሄዎች ካለዎት አስተያየትዎን ይስጡን እንዲሁም ለ ጉዋደኞቹዎ ያካፍሉ


📌 SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?
✅ SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።

✅ HDD አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ሁኔታ የድሮ ቴክኖሎጂ እየተባ የሚጠራ ሲሆን አሁን ላይ ይህንን ቴክኖሎጂ ሁሉም የኮምፒውተር አምራች ድርጅቶች Hard disk Drive መጠቀምን በማቆም ላይ ናቸው።

✅ SSD Solid State Drive አሁን ላይ HDD በመተካት አዲስ የመረጃ ማከማቻ ቴክኖሎጂ እየሆነ ነው። አሁን ላይ ሁሉም የኮምፒውተር አምራች ድርጅቶች የመረጃ ማከማቻ ቴክኖሎጂን ከHDD በላይ SSD እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

✅ HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው።

✅ HDD መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው።

✅ HDD መረጃውን ለማንበብና ለመጻፍ ዲስኩን የሚያሽከረክረው ሞተር ሲኖረው ዲስኩ ሲሽከረከር አንባቢ እጀታ ተገጥሞለታል።

✅ ለHDD ላፕቶፖች 2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን ለዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች 3.5 ኢንች ነው።
HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።

✅ SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።

✅ ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም።

✅ SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።

✅ እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ።

✅ አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።

✅ HDD ከSSD ርካሽ ነው
✅ HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው
✅ HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል
✅ HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል
✅ HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው
✅ HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል

⚠️ ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ Enter ይጫኑ.
Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።








በ1 ደቂቃ Students Mark total and average using Excel የተማሪዎች ውጤት ድምርና አማካይ ውጤት ማስላት በኤክሴል
https://youtu.be/ohAN-Nr06gE
https://youtu.be/ohAN-Nr06gE
https://youtu.be/ohAN-Nr06gE




ሞክሩት አዲስ ኘላትፎርም ነው ክፍያ አይጠይቅም ቪዲዮ በመመልከት በዶላር ገቢ ያስገኛል
https://aaaonline.info/ZYtTh8
https://aaaonline.info/ZYtTh8
https://aaaonline.info/ZYtTh8








ከYoutube ቪድዮ እና ኦድዮ ማውረጃ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ
እንዴት ከዩቱብ ቪዲዮ(video)እና ኦድዮ(audio) ያለ ሶፍትዌር እናወርዳለን( dawnload ) እናደርጋለን ቀላል ዘዴ ተከታተሉኝ መልካም ቆይታ።
ስቴፑን ከስር በ ፎቶውም ታገግኙታላችሁ
1.ከስልክ ውይም ከኮምፕውተር ብሮውሰር( browser) ላይ y2mate ብላችሁ ጽፋችሁ search ታደርጋላችሁ
2.dawnload video and audeo from youtube የምልና ከስር በቀይ ሳጥን search or past link here የሚል ይመጣል
3.እዛ ቦታ ላይ የቪድዮውን ሊንኩ past ታደርጋላችሁ
4.ከዛ በተላያየ መየን(size) አማራጭ ይመጣል ከጎን dawnload የሚለውን እንጫናለን
5.ከዛ ዳውንሎድ (dawnlod) የሚል ያመጣል ከዛ ቀጥታ ይወርዳል
6. ኦድዮውንም ቪድዮ ከሚለው ጎን mp3 የሚልለውን ተጭናችሁ ልክ እንደዛው mp3 ይሚለውን ስንጫን ይመጣል።
ሊንኩን በቀጥታ ከፈለጉ ከስር ያለውን ይጠቀሙ
https://www.y2mate.com/en19


Microsoft Office 2010 (full activated).zip
665.4Mb
⚠️Microsoft Office Proffesional Plus 2010 (full activated)

⚠️Full active, don't need to have product key or any software activater.

Minimum system requirements

⚠️Operating System: Windows XP/Vista/7/8/10
⚠️ Memory (RAM): 256MB of RAM required.
⚠️Hard Disk Space: 3GB of free space required.
⚠️Processor: 500MHz Intel processor or later.

💯working
.


Ethiopian Digital Library (EDL) dan repost
Action Research Training Module.pdf
901.5Kb
Action Research Training Module

TECHNICAL AND VOCATIONAL TRAINING INSTITUTE
Written by Genene Abebe(PhD)
November, 2021

Action Research Training Module
Addis Ababa, Ethiopia

📌Join and share 👇👇👇

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


የኮምፒውተር ሀርድ ዲስክን እንዴት መክፈል እንችላለን?
ዛሬ የምናየው እንዴት አድርገን አንድ ሎካል ዲስክን ወደ ሁለት ከዚያ በላይ ክፍልፋዮች እንደምንቀይር ነው።
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ከሁለት ለመክፈል ለምሳሌ
#1_right click on My computer
#2_ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
#3_ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
#4_ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:
በመምረጥ right click እናደርጋለን
#5_ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
#6-ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
ማስጠንቀቂያ:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈክ ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
#7_ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
#8_click on "new simple volume
ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም።
እስኪ ለምሳሌ 152 GB ለመክፈል ብንፈልግ ስንት ብለን መጻፍ ይጠበቅብናል? ኮሜንት ላይ ይጻፉልኝ!
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅#ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology


#ፍላሽ_ዲስክ_እንዴት_በፓስዎርድ_ማሰር_ይቻላል?
በፍላሽ ዲስክ የተለያዪ ሚስጥራዊ ዳታዎች እንይዛለን! ከራሳችሁ ውጪ ሌላ ማንም ሰው እንዳያየው የምትፈልጉት ዳታ(ፋይል፣ቪድዮ፣ፎቶዎች ወዘተ) በፍላሽ ዲስክ ትይዛላችሁ።
ስለዚህ ሚስጥራዊ ዳታችሁን ከናንተ ውጪ ማንም ሰው እንዳያየው ወይም እንዳይጠቀምበት የግድ ፍላሽ ዲስኩን በፓስወርድ መቆለፍ ይኖርባችኋል።
እሺ windows 10 የምትጠቀሙ ሰዎች ፍላሽ ዲስካችሁን በፖስወርድ ለመቆለፍ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል መቆለፍ ትችላላችሁ።
1-ፍላሽ ዲስኩን ኮምፒውተራችሁ ላይ ሰኩት እና"This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ አድርጉት
2- "This PC" የሚለው አይከን ደብል ክሊክ ስታደርጉት የሚመጣው ቦክስ ውስጥ ፍላሽ ዲስካችሁ ይመጣል
3- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አድርጉ
4- ፍላሽ ዲስኩን "right click" አ.ስታደርጉ "Turn BitLocker on" የሚለውን ሴሌክት ማድረግ
5- ከዚያ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል፣ የማትረሱት ፓስወርድ አስገቡና "next" በሉት
6- ከዚያ "Encrypt entire drive" የሚለውን ሴሌክት በማድረግ "next" ማለት። በቃ አለቀ።ፍላሽ ዲስኩ በፓስውርድ ተቆለፈ።
ከዚህ በኋላ ያለ እናንት ሌላ ማንም ሰው ፍላሹን መጠቀም አይችልም።
ፍላሽ ዲስኩን መጠቀም ስትፈልጉ ኮምፒውተራችሁ ላይ ፍላሹን ደብል ክሊክ ስታደርጉ ፓስወርድ አስገቡ ይላችኋል።ፓስወርድ በማስገባት መጠቀም ትችላላችሁ
#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏


አዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በዲጂታላይዜሽን ቴክኖሎጂ የወረቀት አልባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ።

አዘና ጥር 22/2017 ዓ.ም (አየሁ ጓ/ኮሙኒኬሽን)
በአዊ ብሔ/አስ/አየሁ ጓ/ወ/የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓትን በማዘመን የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ ለተጠቃሚው/ለደንበኛው  ማህበረሰብ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በራሱ አቅም ሶፍት ዌር በማበልጸግ በቅርብ ጊዜ ማስመረቁ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተቋሙ በዲጂታላይዜሽን ስርዓት አገልግሎት ለመስጠት አጠቃላይ ስራው አጠናቆ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

የተቋሙ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረት የወረቀት አልባ አገልግሎትን ለመስጠት  በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ ከአደጋ ስጋት ነፃ፣ ለአገልግሎቱ ፈጣን፣ የባለይዞታውን የፋይል ደህንነት የሚጠብቅ፣ ዋስትናው የተረጋገጠ፣ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ከተቋሙ በተሠጠው መለያ ኮድ መሠረት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከሐሜት የፀዳ አገልግሎት የሚያገኝበት መሆኑን አብራርተዋል።

ከተቋሙ አገልግሎት ተጠቃሚው ማህበረሰብ በያዘው መለያ ኮድ መሠረት ከዛሬው ቀን ጀምሮ የወረቀት አልባ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ይፋ ያደረጉት አቶ ወንድም ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ እውን በመሆን በሲስተም የወረቀት አልባ አገልግሎት በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን ብለዋል።

የአዘና ከተማ መሪ ማ/ቤት የወረቀት አልባ ሲስተም ይፋ ባደረገበት በዛሬው ዕለት በቦታው የተገኙት የወረዳው ከተማና መሠረተ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየነው ዋሲሁን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ቴክኖሎጂ እውን እንዲሆን  ለስኬት እስከሚደርስ የተሳተፉ ለአቶ መሀመድ አሚን፣ ለተቋሙ ስራአስኪያጅና መላ ሠራተኞች፣ ለከተማው ማህበረሰብና የድርሻውን ለተወጡ ሁሉ  ምስጋናቸውን አቅርበዋል።



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.