እርሱ ያግዛችኋል
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ (ሮሜ 8፡26)፡፡
አንዳንድ ጊዜ እጅግ በርካታ በሆኑ ችግሮች ትከበቡና፣ “አሁን ለእነዚህ ሁሉ ችግሮች እንዴት ነው የምጸልየው? “ብላችሁ ልታስቡ ትችላላችሁ፡፡ እውነቱ ግን በዙርያችሁ ስለሚገኙ እያንዳንዱ ችግሮች ተራ በተራ እንጸልያለን ካላችሁ፣ ለዘላለም በጉልበታችሁ ተንበርክካችሁ መቆየት ሊኖርባችሁ ነው ማለት ነው። በተጨማሪም ሁሉንም ችግሮች ላታስታውሷቸው ትችላላችሁ፡፡
መልካሙ ዜና ግን፣ እግዚአብሄር የራሳችሁን መከራ እንደትሸከሙ አይጠብቅባችሁም፡፡ መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።” (1ኛ ጴጥሮስ 5፡7) ይላል፡፡ እንዲያውም ስለችግሮቻችሁ ሁሉ እንድትጸልዩም አይጠብቅም፤ ምክንያቱም ሁሉንም ላታውቋቸውም ትችላላችሁ፡፡ ይህ ከሆነ ታዲያ ምን ማድረግ ነው ያለባችሁ? መንፈስ ቅዱስን ከሰጣችሁ ምክንያቶችም አንዱ ይህ ነው፡፡
በድካምና በእጦት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያግዛችኋል። ምን ማድረግ እንዳለባቸሁ፣ ምን መጸለይ እንዳለባችሁ ወይንም ስለ አንድ ሁኔታ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማወቅ ሲሳናችሁ እርሱ ጣልቃ ይገባል። እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን የሰጠን በህይወት ማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲመራን ነው፡፡ የየእለት ተግዳሮቶችን መጋፈጥን በተመለከተ፣ በመክፈቻ ጥቅሳችን ላይ እንደተነበበው፣ መንፈስ ቅዱስ በክፍተታችን ይተካል ወይም ይማልድልናል፡፡ በእኛ ምትክ ሆኖ ነገሩን ይቆጣጠራል፡፡
በግላዊ ህይወታችሁ ስለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት እወቁ፣ ራሳችሁንም ለእርሱ አስገዙ፡፡ በእናንተ አማካኝነት በማይነገርና በተለመደው ንግግር መገለጽ በማይቻል መቃተት በእግዚአብሄር ፈቃድ መሰረት ለእናንተ በመማለድ ይጸልያል፡፡ በልሳኖቻችሁ መጸለይ እጅግ አስፈላጊ የሆነበትም ምክንያትም ይህ ነው ፡፡ መንፈሳችሁን ለማነቃቃትና የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ንግግር እንዲወጣ ለማድረግ ይረዳል። በመንፈሳችሁ ስትጸልዩ፣ በህይወታችሁ ትኩረት የሚስፈልጋቸውን ነገሮች በሙሉ በማያጠራጥር ሁኔታ ትፈታላችሁ፡፡
መዝሙረኛው እንዲህ አለ፡- “እግዚአብሔር ብድራትን ይመልስልኛል…” (መዝሙረ ዳዊት 138፡8)። በመንፈስ ስትጸልዩ፣ ጌታ በእርግጥ የሚመለከታችሁን ሁሉ የማታውቋቸውን ነገሮችንም ጨምሮ ያስተካክላል፡፡ ልታደርጉት የሚገባ ነገር ቢኖር፣ እርሱ ታላቅ መሆኑንና ሊንከባከባችሁ ፈቃደኛ መሆኑን በማወቅ በህይወታችሁ ሙሉ በሙሉ በእርሱ መተማመን ብቻ ነው፡፡ ስሙ ለዘላለም ይባረክ!
@new_life_ministry