😪• ከንቱ ነኝ •😪
ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ ነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
አዝ-----
ከፀሀይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ/2/
አዝ-----
❤️• ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ LIKE እንዳይረሳ •❤️
➪ @Name33O
➪ @Name33O
ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ ነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
አዝ-----
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝአዝ-----
ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ
የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ
በመጨረሻው ቀን በሞት ተወሰድኩኝ/2/
ከፀሀይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ/2/
አዝ-----
ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉአዝ-----
አፈር ተጭኗቸው ከመቃብር አሉ
እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው
ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው/2/
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩትአዝ-----
አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት
የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ
እኔ በዚህ ምድር ጎስቋላ ነኝ
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት
የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት
ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር
ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር/2/
❤️• ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ LIKE እንዳይረሳ •❤️
➪ @Name33O
➪ @Name33O