የሉሲ እና የሰላም የፕራግ ቆይታ የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር ነው - የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ
ሉሲ እና ሰላም የአውሮፓ የባህል ማዕከል ወደ ሆነችው ፕራግ መጓዛቸው የኢትዮጵያን ምድረ ቀደምትነት ለማሳየት ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ተናገሩ።
ሚኒስትሯ ቅሪተ አካሎቹ በፕራግ ዓውደ-ርዕይ መጎብኘታቸው ኢትዮጵያ ትላልቅ ሀብቶች እና የቱሪዝም አቅም እንዳላት በይበልጥ የምናሳይበት ነው ብለዋል።
ፕራግ ቱሪስቶች የሚጎርፉባት ከተማ እንደመሆኗ ኢትዮጵያን በሰፊው የምናሳይበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ ተመራማሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ምርምር እንዲያደርጉም በር ይከፍታል ሲሉ አክለዋል።
ሁለቱ ሀገራት ከቱሪዝም ባሻገር በኢንቨስትመንት እና በፖለቲካ መስኮች ግንኙነታቸው እየተጠናከረ መሆኑን ያነሱት ሚንስትሯ፤ ሉሲ እና ሰላም ፕራግ ላይ ለዓውደ-ርዕይ መቅረባቸው የሀገራቱን የሁለትዮሽ ስምምነት ውጤት መሆኑንም ገልፀዋል።