ኢትዮጵያ ስንዴን በገፍ አምርታ እነ WFP ሳይቀር ውጤቱን አድንቀው ሲያወሩ ያኔ የኛዎቹ ባንዳዎች ነጠላ አዘቅዝቀው በየሚዲያው ሲያጣጥሉ ነበር። ዛሬ ድሮን ማምረት ስንጀምር "ለምን ስንዴ አላመረትንም?" እያሉ እያለቀሱ ነው። በተነገረ ዜና ሁሉ ማልቀስ ምን የሚሉት ፖለቲካ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።
የአንድ ሐገር ጥንካሬ በብዙ መንገድ ይለካል። ከነዚህ ውስጥ ዋነኞቹ ኢኮኖሚያዊ፥ ወታደራዊ፥ ፖለቲካዊ ጥንካሬዎች ናቸው። Military strength የሌላት ሐገር በርና ጥበቃ የሌለው የጌጣጌጥ ሱቅ ማለት ነች። ዱርየውም ቀማኛውም እንደጠላ ቤት ይረግጣታል። ወታደራዊ ጥንካሬ ደግሞ Advanced Technology መጠቀምና ማምረትን ያካትታል። ይሄን ደግሞ ማሳካት ችለናል።
አንድ የሮማ ፀሀፊ De Re Militari በሚል መፅሀፉ "ሰላም ከፈለግክ ለጦርነት ተዘጋጅ" ይላል። በጦር ሀይል ራስህን ምታጠናክረው ጦርነት ለማድረግ ስለምትፈልግ አይደለም። ጠላቶችህ ካንተ ጋር ጦርነት ውስጥ መግባትን ከአጀንዳቸው ላይ እንዲሰርዙም ጭምር ነው። ምክኒያቱም እንደኢትዮጵያ ያለችን መቶ ሰላሳ ሚሊየን ህዝብና ድሮን የሚያመርት መከላከያ ሰራዊት ያላትን ሐገር መግጠም ከባድ consequence አለውና!!!!
ለማንኛውም ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ በመከራ ያገኘችውን ዶላር ተሸክማ ተተኳሽ ለመግዛት በየሐገሩ አትንከራተትም። በራሳችን እውቀትና አቅም ተተኳሾችን አምርተን በአጭር ግዜ በሚሊዮን ዶላሮች ሸጠናል። ይህ ተአምር ነው። በዚህ አልበቃንም ሚሊየን ዶላሮች የሚወጣበትን ድሮን እዚችው ሐገራችን ላይ አምርተን ራሳችንን አስታጥቀናል። ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያ ድሮን የታጠቀች ብቻ ሳትሆን ድሮን አምርታ ለአለም የምትሸጥ ሐገር ነች። ኢትዮጵያን ከነችግሯ የምትወዱ ውድ ልጆቿ እንኳን ደስ አላችሁ። አልቃሾችና ባንዳዎች እግዜር ፅናቱን ይስጣችሁ