ሰላም እንዴት ናችሁ? ትንሽ በ ሂወቴ ላይ ግራ የገባኝ ነገር እየተፈጠረ ስላለ ላካፍላቺሁ ብዬ ነው. ባለትዳር እና ሁለት ልጆች አሉኝ. ባለቤቴ ያው ለልጆቹ መልካም አባት ነው.ነገሩን ባጭሩ ላርገዉና... ባለቤቴ በፊት በጣም የሚወዳት ሴት ነበረች. እና ብዙ ነገር ካሳለፉ በሁዋላ.... ያው ፍቅራቸዉን ሳይጨርሱ እሱዋ ወደ ዉጭ ሄደች ግን ሄዳ አልተመለሰቺም. በዚህም የተነሳ በጣም ተጎድቶ ነበር... ለረጅም ጊዜ ሴት አልቀረበም ነበር ቢያንስ ለ 7 አመታት ትመጣለች ብሎ እየጠበቃት ነበር. ግን ፈጣሪ አልፈቀድዉምና አልሆነም. በዚህ መሃል ነበር ከኔ ጋር የተዋወቅነው. ከዛ ቢያንስ 3 ዓመት ከቆየን በሁዋላ እኔ አንቺን ማግባት እፈልጋለሁ.. ሲለኝ እኔም ጥሩ ሰው ስለሆነና ስለወደድኩት እሺ ብዬ ተገባን. እሱን ሳገባ እኔ ሌላ ወንድ አላዉቅም ነበር. ድንግል ነበርኩ 😊በቃ እንዲህ እያልን እየኖርን... ስልክ ተደወለ ድንገት እና እንደመጣች ነገረቺው.. 😔እና ያው እንዳገኛት ሄዶ ደርሼበታለው ግን ስጠይቀው ዋሸኝ. ከዛ በሁዋላ ስልኩን ማየት ጀመርኩ. እና ልጅ ዉለጅልኝ ስልሽ አንቺ እንቢ አልሽ.... የወለድኩት ካንቺ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር... 😔😔 ብዙ የማይረሱ ጊዜ አሳልፈናል መቼም አረሳሺም... 😔.. በህልሜ አየሁሽ የኔ እመቤት... እነዚህ እንኩዋን አሁን በቅርብ ያነበብኩት ነው.. ዉዶቼ እና ቆይ እኔን ሳይወደኝ ነው ማለት ነው ያገባኝ... የጎደለበትን ነገር እንድሞላለት ማለት ነው? ብዬ በቃ ማልቀስ ሆነ ስራዬ. በዛ ላይ እሱ 47 ዓመቱ ነው እኔ ደሞ 27 አመቴ ነው. በቃ ሁሌ እኔ በሱ አይን ስህተት እንደሰራሁ ነው... ጥሩ ነገር ሰራሁ ስል በሱ አይን ጥፋት ሆኖ ይታየዋል. ይቆጣል... አሁን አሁን ጭራሽ ያመናጭቀኛል እና በቃ ይከፋኝ ጀመር. ሳይወደኝ ነው ያገባኝ ብዬ አስባለሁ 😔በዛ ላይ የድሮ photo እቤት ሰብስቦ አስቀምጦ እሱን ባየሁ ቁጥር ያመኛል.የድሮ ደብዳቤ አግንቼ አንብቤ ምን ያህል ይወዳት እንደነበር ያስታዉቃል. እኔ ለምን ወደዳት ሳይሆን በቃ የተቁዋረጠ ነገር እንዴት ሰው ትዳር እና ልጆች አፍርቶ ስላለፈ ታሪክ እና ሰው እንዴት ይታሰባል. በቃ እኔን የፈለገኝ በትዳር እራሱን አስሮ ለመኖር ነው በቃ ብዙ ሴቶች ጋር ወሲብ እንዳይፈትጽም በአንድ ተወስኖ ለመኖር እንጂ እኔን ከልቡ አፍቅሮኝ እንዳልሆነ እያሰብኩ ነው.... 😔😔😔. ባጠቃላይ ድብርት ዉስጥ ነኝ ዉዶቼ ምን ባደርግ ይሻለኛል?