❤ፍቅር ነው ያስረጀን!❤
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው መሆን ይቀድማል
ታላቁ ሲታዘዝ ታናሹ ይሰማል።
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው ማለት
ትርጉሙ አይደል መሄድ ቆሞ
ለእውነት መኖር
ነው እንጂ የአንዱን ህመም ታሞ።
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
መች እንዲህ ነበረ
ጊዜውስ መች ከፋ?
ያንቺ ቤት ሞልቶ ከኔ ቤት ቢጠፋ ,,
ችግር እና ሀዘን ደስታና መከራ
ስንቱን አሳለፍነው ተሳስበን በጋራ።
በልባችን የታተመ ፍቅር ስላበጀን
አምላክ እድሜ ሰጥቶን ,,,
ይኸው ሳንለያይ እንደዚህ አረጀን።
"ተ መ ስ ገ ን!"
👌ገጣሚ ዘሪሁን ከ አሰላ
መጋቢት 14/2015
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው መሆን ይቀድማል
ታላቁ ሲታዘዝ ታናሹ ይሰማል።
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
ሰው ማለት
ትርጉሙ አይደል መሄድ ቆሞ
ለእውነት መኖር
ነው እንጂ የአንዱን ህመም ታሞ።
ያኔ በእኛ ዘመን ,,,
መች እንዲህ ነበረ
ጊዜውስ መች ከፋ?
ያንቺ ቤት ሞልቶ ከኔ ቤት ቢጠፋ ,,
ችግር እና ሀዘን ደስታና መከራ
ስንቱን አሳለፍነው ተሳስበን በጋራ።
በልባችን የታተመ ፍቅር ስላበጀን
አምላክ እድሜ ሰጥቶን ,,,
ይኸው ሳንለያይ እንደዚህ አረጀን።
"ተ መ ስ ገ ን!"
👌ገጣሚ ዘሪሁን ከ አሰላ
መጋቢት 14/2015