"𝚃𝚑𝚎𝚊𝚝𝚛𝚎 𝚘𝚏 𝚝𝚑𝚎 𝙰𝚋𝚜𝚞𝚛𝚍"
ይኽ ቦታ «የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት» ይባላል። ስሙ እንደሚገልጸው ሕዝብን የወከሉ ሰዎች የተሰበሰቡበት ቦታ ነው። እነዚኽ ሰዎች ሕዝብ የተባለው ባለ እልፍ ቅጽ መጽሐፍ አጠሬራ ናቸው።
በደንብ አድርገው መልካችንን ይናገራሉ። ተወካዮቻችን የሕዝቡን ኹኔታ ወክለው ለምክክር ይቀመጣሉ። ምክራቸው ግን የአኪጦፌል ነው።
እንደ ሕዝብ አንዳችን ሳንቀር እንዴት እንዳበድን፣ ድንቁርና በመካከላችን እንዴት እንደገነገነ፣ ሆድ አደርነት እንዴት የሚያኮራ ሙያ እንደኾነ፣ ፒ.ኤች.ዲ ሠርቶ ተራ ሎጂክ መረዳት እስካለመቻል መደንዘዝ እንደሚቻል ያስረዱናል። በየሰፈሩ ያለውን ቀን የሚጠብቅ የአምባገነን መዓት ስናያቸው ይገለጥልናል።
ሱፍ ለብሶ እንዴት አውሬ መሆን እንደሚቻል፣ አብረን እየዋልን እንዴት እንደማንተዋወቅ፣ አጽዳቂ እንጂ አርቃቂ እንዳልሆንን፣ በሚያስለቅሰው የመሳቅ በሽታ ( PBA, pseudobulbar affect ) እንደተለከፍን ያስገነዝቡናል።
ዕውቀት እንዴት እንደሚያሰቃይ፣ መፍትሔ ከማምጣት እንደ በግ መነዳት እንዴት እንደሚቀልል እኛ እንዲገባን የሕዝቡን ኹሉ ባሕርይ ይዘው በዚያ ተሰብስበዋል። በመኻላችን ያሉ ጤነኞችን እንዴት እንደምናሳቅቅ፣ በጋራ እብደታችን መሃል ለማሰብና ለመጠየቅ የመረጡትን እንዴት እንደምናሰቃይ ያሳዩናል።
የሕዝብ ተወካዮች ሆይ ባክቴሪያዊ፣ ፈንገሳዊ ጠባያችን የሚጠናበት “culture media” ሆናችኹ ስለከረማችኹ እናመሰግናለን። ምክር ቤታችኹ የበሽታችን ማሳያ “petri dish” ሆኖ ስላገለገለ እናመሰግናለን። ይኽ እናንተን ለመውቀስ አይደለም። ገጸ-ባሕርይ ሆናችሁ ይህንን ትራጆኮሜዲ በዓለም የቲያትር መድረክ ስለተወናችሁን አመሰግናለኹ። እንዲኹ ሳያችኹ ምንም ተስፋ አይሰማኝም።