አሁን ላይ ብዙዎቻችን የ Airdrop ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፍን እንገኛለን። ነገር ግን አብዛኛው በሚባል ደረጃ ስለ Airdrop ምንነት ትንሽም ብትሆን እውቀት የለውም የለንም ።
በዚህ ፅሁፍ Airdrop ምንድነው ፣ የ Airdrop አይነቶች እና የፕሮጀክቱ ባለቤቶች ምን ይጠቀማሉ የሚለውን በጣም በአጭር ለመግለፅ ልሞክር ( ለጠቅላላ እውቀት ያክል 😊 )
Airdrop ምንድነው?
በአጭሩ ኤርድሮፕ ማለት ነፃ የሆኑ ቶክኖችን ወይም ኮይኖች ለተለያዮ Wallet አድሬሶች ማከፋፈል ነው።
የተለያዮ የ Airdrop አይነቶች ቢኖሩም በስፋት የሚታወቀው እና አሁን በሀገራችን ብዙ ሰው የሚሳተፍባቸው Bounty የሚባለው የኤርድሮፕ አይነት ነው።
Bounty Airdrop ላይ ተጠቃሚዎች ነፃ ቶክኖችን ለማግኘት የተለያዮ ተግባራትን ማከናወን ( ሶሻል ሚዲያዎች መከተል ፣ ላይክ ማድረግ ፣ሼር ማድረግን እና ሌሎችን) ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ብዙ ሰው የሚያነሳው ጥያቄ ለእኛ ነፃ ገንዘብ እየሰጡን እነሱ ምን ይጠቀማሉ?
ፕሮጀክቶች ኤርድሮፕ በመስጠታቸው ከሚያገኙት ዋነኛ ጠቀሜታዎች ውስጥ ስንመለከት
✅ አዳዲስ ፕሮጀክታቸውን በስፋት ያስተዋውቃሉ።
✅ ሰለ ፕሮጀክታቸው ግንዛቤን ለመጨመር ይገለገሉበታል ። ከሁሉም በላይ
✅ ታማኝ ተጠቃሚዎችን እና ኢንቨስተሮችን ለመሳብ እና ፈንድ ለማግኘት…
ስለዚህ ነፃ ገንዘብ ሳይሆን ትኩረታችንን ነው የገዙት ማለት ነው ። 😁
@QIMEMMTECH@QIMEMMTECH