እስካሁን ከ499,000 በላይ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠናቀቀቂያ ፈተና ለመውሰድ እስካሁን 499,200 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡
በመደበኛ እና በግል 750,000 ተማሪዎች ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በአገልግሎቱ የተፈታኞች ምዝገባ፣ የፈተና ዕርማትና ውጤት ጥንቅር ዴስክ ኃላፊ ማዕረፉ ሌሬቦ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።
የመደበኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ በኦንላይን ከታህሳስ 8/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ሲሆን፤ ጥር 6/2017 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ኃላፊው ገልፀዋል።
በመደበኛው ፕሮግራም 600,000 ተማሪዎች ለመመዝገብ ዕቅድ መያዙን የገለፁት ኃላፊው፤ እስካሁን 82 በመቶ የሚሆኑ መደበኛ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል። በግል የሚፈተኑ 150,000 ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ሲጠበቅ፤ እስካሁን 1,100 ተማሪዎች ብቻ ምዝገባ አድርገዋል፡፡
የኢንተርኔት አማራጭ በሌለባቸው አካባቢዎች ተማሪዎች በወረቀት ከተመዘገቡ በኋላ ኢንተርኔት የሚሠራበት አካባቢ በመሔድ መረጃቸውን ወደ ኦንላይን መጫን እንደሚችሉ ኃላፊው ተናግረዋል። #FMC
@Qesemacademy