ልቤን ነካኝና ላካፍላችሁ ወደድኩ
እዲህ ነበሩ የኛ ነብይ ፣የኛ ረሱል ﷺ
ረሱል ﷺ ወደ መስጂድ ለመሄድ የሚጠቀሙት መንገድ ጠብቃ
"ቆሻሻ" የምትወረውርባቸው አንዲት አዛውንት ነበረች። ነብያችንﷺ በየቀኑ ወደመስጂድ ሲመላለሱ እየጠበቀች "ቆሻሻውን "ትደፍባቸዋለች ነብያችንም ﷺ ችለውት በዝምታ ምንም አይነት መቆጣትን ሳያሳዩ ያልፍሉ። ይህ የተለመደ ክስተት ሆኗል። አንድ ቀን የአሏህ መላዕክተኛ ﷺ በመንገዱ ሲያልፍ እንደ ወትሮው ቆሻሻ የምትደፍባቸው ሴት የለችም። ነብያችንﷺ በቦታው ላይ ቆመው ስለ ጤንነቷ ጎረቤቷን ጠየቁ።
የሴትዬዋ ጎረቤትም አዛውንትዋ ታማ አልጋ ላይ እንደተኛች ነገሯቸው። የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ ወደ አዛውቷ ቤት መግባት እንደሚችሉ በትህትና በመጠየቅ ሲፈቀድላቸው ገቡ።
ሴትዪዋ ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ን ስትመለከት ለበቀል እንደመጡ በማሰብ አቅሜ ሲደክም በሽታ አልጋ ላይ ሲያስተኛኝ ልትበቀለኝ መጣህ?
አለቻቸው።"እርሳቸውም" የመጡት ለበቀል ሳይሆን መታመሟን በመስማታቸው አዝነው ሊጠይቋትና የምትፈልገው ነገር ካለ ሊያሟሉ ፍቃደኛ መሆናቸውን ገለጹላት።
አዛውቷም ከመገረሟ የተነሳ መናገር አቃታት። በአትኩሮት ትመለከታቸው ጀመር "ከዚያም እንዲህ አለች አንተ " እውነተኛ "የአሏህ መልዕክተኛ" መሆንህን እና አሏህም ጌታህ መሆኑን እመሰክራለሁ በማለት እስልምናን ተቀበለች። ሱበሃን አሏህ!!
እንዲህ ነበሩ ነብያችን ﷺ እጅግ በጣም አዛኝ ተፈቃሪ ፦አዛውቱ ህጻን ሳይሉ ሁሉንም በቸርነት የሚያስተናግዱ ምርጥ ነብይ!!!!ﷺ ﷺﷺﷺﷺﷺ
በቀን በቀን 1የረሱል ...🌹 ﷺሀዲስ መስማት ከፈለጉ ቴሌግራም ጉሩፓችን ይቀላቀላሉ
https://t.me/+W3eSM3pq7E5mNDc0 ✨━┅┉┈ሱብሀን አላህ┈┉┅━✨
አንተ ረሱልን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የተሳደብከው ሰው እንዲህ በሰደብካቸው ግዜ እሳቸው በሀያት ቢኖሩና
በስድብህ ንዴት የአለም ሙስሊም ህዝብ በሙሉ አንተን ሊገድል ቢመጣ
እሳቸው ግን ከኋላቸው ሸሽገው እንዳትገደል ይከላከሉልህ ነበር እሳቸው እንዲ ናቸው አንተ ሰደብካቸው።
ፊዳ ልሁንልሎ ያሀቢበላህ❤️❤️❤️