የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ፣ ሬጅስትራር ጽ/ቤትየመጀመሪያ ዲግሪ ስፔሻሊቲ ፖስት ቤዚክ ነርሲንግ ትምህርት ምዝገባ ማስታወቂያየቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በአምስት የነርሲንግ ፖስት ቤዚክ ስፔሻሊቲ ማለትም በ Emergency and Critical Care Nursing፣ በ operating Theater Nurse፣ በ neonatal Nursing፣ በ pediatrics and child health Nursing እና በ surgical Nursing ለመማር የምትፈልጉ እና መስፈርቱ የምታሟሉ ከ 21/01/2019- 30/01/2019 ዓ.ም Online
https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement እንድትመዘገቡ እናሳወቃለን፡፡
የመመዝገቢያ መስፈርቶች፣· በነርሲንግ ዲፕሎማ ደረጃ 4 የተመረቀች/የተመረቀ በሁሉም ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች መወዳደር ይችላሉ፣
· የሚድዋይፍሪ ዲፕሎማ ደረጃ የተመረቀች /የተመረቀ በህፃናትና በጨቅላ ህፃናት ነርሲንግ መመዝገብ ይችላል፣
· ከመስሪያ ቤታቸው የስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ ማምጣት የሚችል/የሚትችል ወይም ከፍሎ መማር የሚችሉ ፡፡
· ኮሌጁ የሚያዘጋጀውን የቃል እና የፁሑፍ ፈተና ማለፍ የሚችል/የምትችል፣
· ሙሉ ጤነኛ የሆነ/የሆነች
· አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው/ ያላት
ማሳሰቢያ፡Ø የመመዝገቢያ የማይመለስ 400 ብር በኮሌጁ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000006577192 በማስገባት ደረሰኝ ማቅረብ
Ø ዲፕሎማ፤ትራንስክሪፕት እና የስራ ልምድ ማያያዝ
Ø አስፈላጊውን ዶክመንት ያላሟላ ፈተናው ላይ እንደማይቀመጥ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
Ø ኮሌጁ ማደሪያና ምግብ አያዘጋጅም