በሁሉም ነጻ ቀጠናዎች የተከናወኑ ሕዝባዊ ሰልፎች ሰላማዊና ሕዝባችን በፈለገበት መንገድ የልቡን እንዲናገር፣ የሚያምንበትን ስሜቱን እንዲያንጸባርቅ፣ ነጻነት በመፍጠር ረገድ የፀጥታ ማስከበር ሚናችሁን ለተወጣችሁ፣ የሁለቱ ኮር አመራሮች፣ የክፍለጦር አዛዦች እና የብርጌድና የሠራዊት አባላት በሙሉ በሰማዕታት የትግል ወንድሞች ሥም ክብርና ሞገስ ይገባችኋል፡፡
በቀጣይ ትግላችን በጠላት ቁጥጥር ስር የሚገኙ ከተሞች እንደአብዛኛዎቹ የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አካባቢዎች ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ የሕይወትና የደም ዋጋ ለመክፈል ዝግጁነታችንን ስናረጋግጥ የትግሉን ሰማዕታት አደራ በማሰብ ጭምር ነው!!
አብዛኛው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አካባቢ ያገኘውን ነጻነት በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ቀሪ ከተሞች በፋኖ ተጋድሎ በቅርቡ ነፃ ይወጣሉ!! የትግሉ ባለቤት የሆነው ሕዝባችን የትግሉ መሪ ከሆነው ፋኖ ጎን ተሰልፎ እስከአባቶቹ መንበር አራት ኪሎ ድረስ በፅናት እንደሚፋለም በድጋፉ ስላሳየን የትግል መስመራችንን ሀቀኝነት በድጋሚ አረጋግጠንበታል!!
ዕውነተኛ የሕዝብ ድጋፍ የሀቀኛ ትግል ማረጋገጫ ነው!!
ድል ለአማራ ሕዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
ክብር ለትግሉ ሰማዕታት አርበኞች
የዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ
ታኀሳስ 11/2017 ዓ.ም.
ሸዋ-ዐማራ-ኢትዮጵያየዐማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ በተቆጣጠራቸው ነጻ ቀጠናዎች በተደረጉ
የተቃውሞ ሰልፎች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ‼️
ዕውነተኛ የሕዝብ ድጋፍ የሀቀኛ ትግል ማረጋገጫ ነው!!
ታላቁ የዐማራ ሕዝብ በፋሽስት ጣሊያን በተተከለ የሐሰት ትርክት፣ የፋሽዝም ተማሪ በሆኑት ህወሓት እና ኦነግ-ኦሕዴድ ተከታታይ የዘር ማጥፋት ፕሮጀክት ተከፍቶበት ሕልውናው አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡
ዐማራ ጠል ኃይሎች ሥልጣን ከተቆናጠጡ ያለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን በተለይም ደግሞ ድኀረ-1983 በሐሰት ትርክት ላይ የተመሠረተ መዋቅራዊና ሕግ ሰራሽ ጭቆናና ጥቃት በሕዝባችን ላይ ሲፈፀም ቆይቷል። እየተፈፀመም ይገኛል።
ይሕንን በጠባብ ቡድኖችና የፋሽስም ተማሪዎች፣ የተጫነ መዋቅራዊ ጥቃት ተከትሎ በሕዝባችን ላይ አፈና፣ ግድያና ማፈናቀሎች ሲፈፀሙ፤ ከርስትና ማንነቱ የመንቀል፤ ዘር ተኮር ጥቃቶች በተደራጀ መልኩ ሲፈጸም የዐማራ ሕዝብ ወቅትና ጊዜ እየቀያየረ ለዓመታት በሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና በአደባባይ ሰልፎች "አትግደሉኝ" በማለት ቢጠይቅም ምላሹ ስላቅ ነበር፡፡
ዐማራ ርስትና ማንነቱን ለማረጋገጥ በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቅ "ነፍጠኛን አከርካሪውን ሰብረነዋል"፣ ለረዥም ዓመታት አገር አቅንቶ አልምቶ በሚኖርበት ቀዬ "ሰፋሪ መጤ ውጣ" የአርሶ አደሩን የግብርና ጥያቄ "የጅራፍ ፖለቲካ" በሚል ፍረጃና ስላቅ ሲሳለቁ፤ የዐማራ ወጣት የመብትና የፍትህ ጥያቄን ደግሞ "የከተማ ጩኸት" አድርገው ሲሳለቁበት ቆይተዋል፤ "አትግደሉን፣ አታፈናቅሉን፣…" በሚል ሕዝባዊ የቁጣ ድምፅ ሲሰማ ደግሞ የፋሽስት ተማሪዎች ምላሻቸው "ዐማራዎች ያልቅሱ ሶፍት እናቀብላቸዋለን" በሚል እንደተፌዘብን የቅርብ ጊዜ የቁጭት ትዝታችን ነው።
ዐማራ በላቡ በገነባት የሸዋም የኢትዮጵያም እምብርት በሆነችው አዲስ አበባ መግባት አትችልም ተብሎ ሲታገድ፣ የሌላ አገር ድንበር የሚቋርጥ በሚመስል መልኩ ሲንገላታ መላ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ዓለም እየታዘበ ነበር፡፡
ይህ ከአፓርታይድም የከፋ ከስውር ያለፈ ግልጽና ተጨባጭ የዘር ጥቃት በአደባባይ ሲፈጸም የዐማራ ሕዝብ በአደባባይ ሰልፍና በሰላማዊ መንገድ ጥያቄዎቹን ሲያቀርብ የነበረ ቢሆንም ሰላም ወዳድነቱ እንደድክመት፤ ታጋሽነቱ እንደፍርሃት ተቆጠረበት፡፡
ይልቁንም ከመዋቅራዊ ጥቃት ወደቀጥታ የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው ጦርነት እወጃ የገባው ተረኛው ኦነግ-ኦሕዴድ፣ የዐማራ ሕዝብ እሴት የሆነውን ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ቀበቶቸውንም እናስፈታቸዋለን በሚል እብሪት ጦርነት አወጁብን፡፡
ቀደም ሲል በወለጋ፣ አርሲ፣ ሐረርጌ፣ ቤኒሻንጉል፣…. ወዘተ ከሚደርስበት ተከታታይ ጥቃት የሚናበብ ሸዋን ማዕከሉ ያደረገ ልዩ ጥቃት በይፋት፣ መርሃ-ቤቴ ደራ፣ ምንጃር ቀጣናዎችን በተለይም አጣየ ከተማን የአጼ ዳዊት መናገሻ በረራ በጠፋችበት መንገድ ለማጥፋት ከአስር ጊዜ በላይ የማንደድ፣ የማጥፋት መከራ ሲደረግ፣ ዐማራ ከመጠነኛ ራስን የመከላከል ሙከራ ውጭ ሁሉንም በሰላማዊ ትግል ለመመከት ቢሞክርም ተጋላጭነቱን በእጥፍ ከማሳደግ በቀር ያተረፈው ነገር አልነበረም።
ዛሬ የዐማራ ሕዝብ የሰልፍ ዘመኑን ጨርሶ ሰይፉን ካነሳ ሁለተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡
ከዛ ቀደም ብሎ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከተስፋፊ ወራሪ ኃይል ራስን የመከላከል፤ ዐማራዊ ማንነትን የማስከበር፤ ትጥቅና እሴትን በክንድ የማጽናት ተጋድሎዎች መልክና ቅርጽ መያዝ እንደቻሉ ይታወሳል፡፡ የፋኖነት መልክ ወዙ መመለስ የጀመረው በሸዋ ምድር በጀመረው በዚህ መሰሉ የትግል እርሾ ነበር፡፡
ዛሬ የዐማራ ሕዝብ ኀልውናውን ለማስከበር በሚያደርገው ተጋድሎ፣ የትግሉ መሪ ፋኖ ከታች ወደላይ እያደገ በመጣ የትግል አደረጃጀቱ፣ መራር መስዋዕትነት በመክፈል ትግሉን በማይቀለበስበት ምዕራፍ ላይ አድርሶታል፡፡
የትላንት ሰላማዊ ሰልፍ መሪዎች ዛሬ የክፍለጦር መሪዎች ሆነዋል። ይህ የመገፋታችን ውጤት ነው። ይህ የትውልዱ ልዩ የአርበኝነት ታሪክ ምዕራፍ ነው። ይህ ትውልዱ ከሰልፍ ወደ ሰይፍ የተሻገረበት፣ የነዚያ የዓድዋ ድል አዝማችና ዘማች የታሪክ ሰሪዎቹ ልጆች መሆኑን ለፋሽስት ተማሪዎች በተግባር ያሳየበት ልዩ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
እንደ ዐማራ በተለይም ደግሞ የዚህ ትውልድ አካል እንደሆነ የትግል አርበኛ፡- ፋኖነት እሴት፣ ፋኖነት ማንነት እንደሆነ በሕይወትና የደም ዋጋ የተረጋገጠበት በወርቅ ቀለም የሚፃፍ የታሪካችን ክፍል ላይ እንገኛለን፡፡
ትላንት በዐማራ ሕዝብ የ"አትግደሉኝ" ሰልፍ የተሳለቁና የመብት ጥያቄውን ወርውረው እግራቸው ስር የጣሉት ተረኞች፤ ዛሬ "የዐማራ ሕዝብ ሰይፍ ወገባቸውን እየቆረጠ ሲጥላቸው" "ከትጥቅ አስፍታለሁ" ፉከራ ወደ "ተሰለፉልን" ልመናና ማባበል ተሻግረዋል፡፡
ይህ የሆነው ሁለት ዓመት ባልሞላ ተጋድሎ ነው፡፡ በአስራ ስምንት ወራት የፋኖ ትጥቅ ትግል ታሪካችን ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ፈጣን ማጥቃት፣ የሰራዊት ግንባታና ሰፊ መሠረት ያለው የሕዝብ ድጋፍ አሳክተናል፡፡
የብልጽግና ሠራዊት የውጊያ አቅም ከመዳከሙም በላይ የውጊያ ጭንቅላቱን በውጊያ ጥበባችን ቆርጠነዋል፡፡ መሬት ላይ የውጊያ እውነታዎችን መቀየር ያልቻለው ተሸናፊው አገዛዝ፣ ዓለማቀፍ ፖለቲካ እሰራበታለሁ በሚል በማባበልና በማስፈራራት የታጀበ ሰልፍ ቢጠራም ሰልፉ እንደውጊያ ዕቅዱ ሁሉ በአየር ላይ ከሽፏል፡፡
ይህ አስገዳጅ የጠመንጃ ሰልፍ በዐማራ ክልል ከተሞች ንፁኃንን በማስገደድ፣ ነጋዴውን በግብር በማጨናነቅ፣ የኃይማኖት አባቶችን በሰላም ስም በመለማመጥ፣ የመንግስት ሰራተኛውን በላብ ደም ወዙ በማስፈራራት በተለያዩ ከተሞች የተሞከረው ሰልፍ ዋጋ ቢስ ሆኖ ፋሽስቱ ሥርዓት በገዛ ፕሮፖጋንዳው ራቁቱን ቀርቶ ታይቷል፡፡
ይህን ፋሽስቱ ሥርዓት ይዞት በመጣው በገዛ ፕሮፖጋዳው መልሶ ራቁቱን የማስቀረት ስራ፣ በአማራ ሕዝብ ከሽፏል፡፡
የጦር ወንጀል እየተፈፀመበት ያለው የአማራ ሕዝብ በተለያዩ ማህበራዊ አደረጃጀቶች ተጠራርቶ በመውጣት ፤የብልፅግናን አማተር የፖለቲካ ሰልፍ፤ ያልበሰለ ጮርቃ ፕሮፖጋንዳ በመግፈፍ ርቃኑን እንዲቀር ማድረግ ተችሏል፡፡