አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ dan repost
#ለካስ_አባታችሁ_መቅደሱን_አጥነው_እየጠበቋችሁ_ነበር !!!
....ከዓመታት በፊት በታኅሣሥ ሃያ አራት የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓልን ለማክበር በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ቁስቋም ወዳለው የጻድቁ ቤተ መቅደስ በሌሊት ይደርሳሉ።
በስፍራው እንደደረሱም ከበሮ ይዘው « የኢቲሳ አንበሳ ተክልዬ ተነሣ» እያሉ እየዘመሩ በዛፎች እስከተከበበው እጅግ ሰፊው የገዳሙ ግቢ የውስጠኛ ክፍል ድረስ የጻድቁ አባታቸውን ስም እየጠሩ ገሠገሡ።
ይህንን የተመለከቱ የገዳሙ አባቶች በደስታ ተውጠው ሲመለከቱ አንድ አባት ግን እየተንሰቀሰቁ ያለቅሱ ጀመር እኚህ አባት የተክለ ሃይማኖት መቅደስ ያለበትን ቤተ ክርስቲያን ቁልፍ የሚይዙ መነኩሴ ናቸው።
የሚዘምሩትን ወጣቶች እያዩ በመደሰት ፈንታ ዕንባቸውን ለመግታት አልቻሉም ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ኢትዮጵያውያኑ ወጣቶች ዝማሬአቸውን ገታ አድርገው እኚህን አባት ቀርበው የለቅሷቸውን ምክንያት ለመጠየቅ ተገደዱ።
መነኩሴውም እንዲህ ሲሉ ከዕንባ ጋር ነገሯቸው።
ትናንት ማታ ከሠርክ ጸሎት በኋላ እንደተለመደው ቤተ ክርስቲያኑን ልቆልፍ ስል ከተክለ ሃይማኖት መቅደስ ውስጥ ጢስ ሲወጣ ተመለከትሁ ምናልባት የሚነድ ነገር ይኖር ይሆናል ብዬ ወደ ውስጥ ስገባ መቅደሱ በዕጣን ጢስ ተሞልቷል።
ምንም የሚነድ ነገር ግን የለም በነገሩ ተገርሜ ቤተ ክርስቲያኑን ቆልፌ ሔድኩ ለካስ አባታችሁ እናንተ ዛሬ እንደምትመጡ አውቀው መቅደሱን አጥነው እየጠበቋችሁ ነበር !! አሏቸው።
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ከመላእክት ጋር የዘመረ ቅዱስ ያሬድን ከካህናተ ሰማይ ጋር ያጠነ ተክለ ሃይማኖትን ያፈራች ቤተክርስቲያን ናት።
#ከግዮን_ወንዝ_መጽሐፍ_የተወሰደ
#እንኳን_ለበዓለ_ልደተ_ተክለ_ሃይማኖት_አደረሳችሁ
#የጻድቁ_በረከት_ይደርብን_ጸሎታቸዉ_ትራዳን!
#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!
አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube
Sador Sisay on Youtube
Sador Sisay on Instagram
Sador Sisay on Facebook
Sador Sisay on Tiktok
#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏