Postlar filtri


" የልጄን እውነት አፈላልጉኝ ! ... የፍትህ አካላት ተከታትለው የልጄን ሀቋን ያውጣልኝ ፤ ደሟን ያወጣልኝ " - አባት አቶ አዱኛ ዋቆ

#Ethiopia | የወጣቷ ቀነኒ አዱኛ ስርዓተ ቀብር ትናንት በአዲስ አበባ ፤ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ሰላት ሲመሩ የነበሩ ኢማም ላይ የወጣችው ድመት

በአልጀሪያ የሰላት ስነ ስርዓት በመምራት ላይ በነበሩ ኢማም ትከሻ ላይ የወጣችው ድመት መነጋገሪያ ሆናለች።
ከዚህ ቀደምም በፈረንጆቹ 2023 ላይ በአልጄሪያ መስጊድ ውስጥ በተመሳሳይ መልኩ ድምት ሰላት ሲመሩ የነበሩ ሼክ ትክሻ ላይ ወጥታ ስትቀመጥ መታየቱ ይታወሳል።
#alain


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በደብረጺዮን የሚመራው ህገወጡ ታጣቂ ቡድን ሰላማዊ ሰልፍ የወጣ ህዝብ ላይ የተኩስ እርሙታ ዛሬ ከፍቷል::




በአዲስ አበባ የንግድ ባንክ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ የጥበቃ ሠራተኛው ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለቢቢሲ ተናገረ።

ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ሲሆን፤ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው 'የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም' በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን እንዳጠፋ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን በጥይት ተኩሶ የገደለው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ እንደገለጹት ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ግድያውን ፈፅሟል።

ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ተጠርጣሪው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ መግደሉን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።

ግድያው ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ መፈፀሙን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቃል አቀባይ፤ በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት እንደነበረ አመለክተዋል።

ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ባልደረባውን ተኩሶ ከገደ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ እንዳልነበረ ተገልጿል።

ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ መግደሉን ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸው በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።

ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው እንደሚያጣራ ገልፀዋል።

ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

©️BBC


" የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ቀድመው ተገቢውን ሃላፊነታቸው ካልተወጡ የትግራይ ህዝብ መወጣት ወደ ማይችለው ዳግም አስከፊ ጦርነት ይገባል " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፌደራል መንግስት እና የዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ ድጋፍ ጠይቋል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ዛሬ መጋቢት 3/2017 ዓ..ም ባወጣው መግለጫ ፤ የፌደራል መንግስት በፀጥታ ሃይል ስም በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት አካላት የአንድ ቡድን ተላላኪዎች እንጂ ህዝብና ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማይወክሉ መሆናቸው ተረድቶ አስፈላጊ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቋል።

የፌደራል መንግስቲትህገ-ወጥ አካሄድ በተከተለ ቡድን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ፈርሶ ዳግም ወደ ጥፋት እየተገባ ዝም ብሎ መመልከት አይገባም ሲል አክሏል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ ለዓለምአቀፍ ማህበረሰብ ባስተላለፈው ግልፅ መልእክት ፤ " ቡድኑና አሽከሮቹ ወንጀሎቻቸው ለመደበቅ ሲሉ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሲያፈርሱ በዝምታ ማየት ትቶ አስፈላጊ ጫና ማድረግ አለበት " ብለዋል። 

የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ቀድመው ተገቢውን ሃላፊነታቸው ካልተወጡ  ግን የትግራይ ህዝብ መወጣት ወደ ማይችለው  ዳግም አስከፊ ጦርነት ይገባል ሲል የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል።

#tikvahethiopia 
@subitime


#Ethiopia  | በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቐለ እና በአክሱም ሪጅን በተፈፀመ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ስርቆት ከ24 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

ባለፉት ሰባት ወራት በመቐለ ከተማና ዙሪያ በፍሬወይኒ፣ ቀለምኒ፣ አዲግራት፣ እዳጋ ሀሙስ ለአየር መንገድ፣ ለውሃ እንዲሁም ለቴሌ አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ 4 ባለ 100 ኬቪኤ፣ 3 ባለ 200 ኬ.ቪኤ እና 2 ባለ 315 ኬቪኤ ትራንስፎርመሮች ላይ ስርቆት ተፈፅሟል፡፡

በአዲጉዶም የ3 ሺህ ሜትር የኤሌክትሪክ ኬብል ስርቆት፤ በሰምረ በ2 ኮንክሪት ምሰሶ ላይ የደረሰ ጉዳት በአካባቢው ለ3 ወራት ኃይል እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል፡፡ በመቐለ ከተማና ዙሪያ የተፈፀመው ስርቆትም ከ 15 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በተመሳሳይ በአክሱም ከተማና ዙሪያ ለአየር መንገድ፣ ለቴሌና እና ለመንደር ማስፋፊያ ሥራ አገልግሎት የሚሰጡ 2 ባለ 315 ኬቪኤ፤ 1 ባለ 200 ኬቪኤ፤ 2 ባለ 50 ኬቪኤ እንዲሁም 1 ባለ 25 ኬቪኤ ትራንስፎርመሮች ስርቆት ተፈፅሞባቸዋል፡፡

በተጨማሪም በማዕከላዊ ዞን ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ከአድዋ – ሽሬ ከተዘረጉ 66 ኬ.ቪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ 32 የታወር ብረቶች ተዘርፈዋል፡፡

በከተማዋ በተፈፀመ ስርቆት ከ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ በሁለቱም ከተሞች 24 ሚሊየን 405 ሺህ 908 ብር የሚገመት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ጉዳት ደርሷል፡፡

የወንጀሉን ፈፃሚዎች ለህግ ለማቅረብ ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ ሲሆን በህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለውን ስርቆት ለመከላከል ከተቋሙ ጥረት ባሻገር የሚመለከታቸው አካላት ለመሠረተ ልማቱ ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
#getutemesgen
@SubiTime


" ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ አልፏል " - ፖሊስ

በሟች ቀነኒ አዱኛ አሟሟት ዙሪያ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰንሻይን ቤቶች ፊት ለፊት ከሚገኘው ውዳሴ ህንፃ ላይ ነዋሪ የነበረችው ሟች ቀነኒ አዱኛ መጋቢት 01 ቀን 2017 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሠዓት አካባቢ ከቤቷ የማብሰያ ክፍል በኩል ካለው በረንዳ 5ኛ ፎቅ ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወድቃ ለህክምና እርዳታ ወደ ያኔት ሆስፒታል እየተወሰደች ባለበት ወቅት ህይወቷ እንዳለፈ ፖሊስ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃው ከደረሰው በኋላ የምርመራ ቡድን በማዋቀርና ቦታው ድረስ በመሄድ ተገቢውን የቴክኒክና የታክቲክ መረጃዎችን ያሰባሰበ ሲሆን የሟችንም አስከሬን ወደ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለተጨማሪ ለምርመራ እንዲሄድ አድርጓል፡፡

ሟች ቀነኒ አዱኛ በወቅቱ ከበረዳ ላይ በወደቀችበት ሰዓት ፖሊስ በቤቱ ውስጥ የነበረውን ባለቤቷን ድምፃዊ አንዷለም ጎሳን በቁጥጥር ስር በማዋልም ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

በቀጣይ የመጨረሻውን የምርመራ ውጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ያስታወቀ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ከፖሊስ የወንጀል ምርመራ ውጤት በፊት የሚናፈሱ መረጃዎች ተገቢነት የሌላቸው ናቸው ብሏል።

ከዚህ ባሻገር የሚናፈሱት መረጃዎች በምርምራ ሒደቱ ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅህኖ በመገንዘብ የተሳሳተ መረጃ የሚያስተላልፉ እና የሚያሰራጩ ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#AddisAbabaPolice
@subitime


ባለጸጋ ያደርጋል በሚል በ120 ዶላር እየተሸጠ ያለው አፈር

አፈሩ የባንክ ህንጻዎች ከተገነቡባቸው ቦታዎች ላይ የተቆፈረ ነው ተብሏል

ይህን አፈር መጠቀም ሀብታም ያደርጋል በሚል በርካቶች እየሸመቱት ይገኛሉ

ባለጸጋ ያደርጋል በሚል በ120 ዶላር እየተሸጠ ያለው አፈር
የዓለማችን ቁጥር ሁለት ሀብታም ሀገር በሆነችው ቻይና በአነስተኛ ካርቶን ወይም ከረጢት መሳይ እቃ መያዣ እየተሸጠ ያለው ነገር ብዙዎችን አስገርሟል።
ይህ እቃ ባንኮች ከተገነቡባቸው መሬት ላይ የተቆፈረ አፈር ሲሆን አንድ ከረጢት አፈር በ880 ዩዋን ወይም 120 ዶላር እየተሸጠ ይገኛል።
ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት እንደዘገበው ከሆነ ይህ ከባንኮች ህንጻ ስር ይወጣል የተባለው አፈር ሰዎችን ባለጸጋ ያደርጋል የሚል ዕምነት አሳድሯል።
በንግዳቸው እንዲሳካላቸው የፈለጉ ቻይናዊያን ይህን አፈር እየሸመቱ እንደሆነም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
አፈሩ በበይነ መረብ የንግድ አውታሮች አማካኝነት ለሽያጭ የቀረበ ሲሆን የአፈሩ ተፈላጊነት መጨመሩን ተከትሎ እስከ አንድ ሺህ ዩዋን ደርሷል ተብሏል።
ለሽያጭ የቀረበው ይህ አፈር ከአራት የቻይና ግዙፍ ባንኮች ማለትም ከቻይና ግብርና ባንክ፣ ከኢንዱስትሪ ባንክ ኦፍ ቻይና፣ ከንግብ ባንክ እና ከቻይና ኮንስትራክሽን ባንክ ህንጻዎች ስር የተቆፈረ እንደሆነ ተገልጿል።
የሀብት መጠንን ይጨምራል የተባለው ይህ አፈር ከንግድ እና ኢንቨስትመንት ጋር ያሉ መጥፎ ነገሮችን ያስወግዳል ተብሎም ይታመንበታል።
አፈር ሻጭ ነጋዴዎች አፈሩን በሌሊት ይቆፍራሉ የተባለ ሲሆን እንደተባለው ይህ አፈር የተባለውን ያህል ሀብት ያስገኛል የሚለው አመለካከት እስካሁን በሳይንስ አልተረጋገጠም።
በቅርቡ ተዓምረኛ የተባለውን አፈር የገዛ እና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ቻይናዊ እንዳለው ብዙ ጓደኞቹ አፈሩን እንደገዙ እና እንደተባለው አፈሩ ሀብት ካስገኘ በሚል እሱም እንደገዛ ተናግሯል።
ድርጊቱ በመላው ቻይና መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ብዙዎች ሰዎች አፈር ከመግዛት እንዲቆጠቡ እና ገንዘባቸውን እንዳይጭበረበሩ ሲሉ አሳስበዋል።
#alain
@subitime


«ከቀን እስከ ማታ የልደት ፎቶዎችን ሳነሳት ነበር፣ ጠዋት መርዶ አረዱኝ» ወንደወሰን በጋሻው

በፎቶግራፍ ስራዎች ካፈራዋቸው ወዳጆቼ መካከል የቀኝ እጄ የምላት እህቴ ቀነኒ አዱኛ መካሪዬ ጎደኛዬ የክፉ ቀን ወዳጄ ነበረች ::

ትላንት መጋቢት 1/2017 ከቀኑ 10:00 ጀምሮ እነዚን የልደት ፎቶዎች ሳነሳት ነበር ማታ 1:00 በሰላም ተለያየትን ዛሬ ጠዋት መጋቢት 2/2017 ጠዋት ማረፏን አረዱኝ::

ወንዴክስ ስቱዲዮ (ወንደሰን በጋሻው) ለቤተሰቦቿ እና ለመላው አድናቂዎቿ መፅናናትን ይመኛል::
@subitime


ነብስ ይማር

😭😭😭

#የድምጻዊ አንዷለም ጎሳ ሚስት ቀነኒ አዱኛ በድገንት ህይወቷ አልፏል፤ ስለአሟሟቷ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።

ነብስ ይማር

😭😭😭



12 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.