የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰ’ጠው ገንዘብ ቁጥር ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው እጅግ ትበልጣለች፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡
አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠውን ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡
ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ:
🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿🌹🌿
@TIBEBnegni