መንግሥት አሰቃቂ ግድያውን በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር ተጠቅሞበታል ሲል የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አስታወቀ
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ባንድ ወጣት ላይ የተፈጸመውን ግድያ መንግሥት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና ፋኖ በአካባቢው ሕዝብ ላይ በጋራ ጥቃት ይፈጽማሉ ለሚል ቅስቀሳ ወደፊት ሊጠቀምበት አቅዶ ነበር ሲልም ወቅሷል።
ሆኖም የግድያው ተንቀሳቃሽ ምስል በድንገት ይፋ መሆኑን ተከትሎ፤ መንግሥት በኦሮሞና አማራ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ ለመፍጠር ተጠቅሞበታል በማለት ቡድኑ ከሷል።
ቡድኑ፤ በወጣቱ ላይ ግድያውን የፈጸሙት፣ ባካባቢው በመንግሥት ወኪሎች የሚደገፉ ራሳቸውን ፋኖ ብለው የሚጠሩ ቡድኖች መሆናቸው ደርሼበታለሁ ብሏል።
የመንግሥት አካሄድ በአገሪቱ ሕልውና ላይ ከባድ አደጋ ደቅኗል ያለው ቡድኑ፤ ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ በመንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድር ጠይቋል ::
via#ዋዜማ