ዜና!!!!
ዋተር ስቶንስ የተሰኘው መፅሀፍ አሳታሚ ድርጅት የአንጋፋው ደራሲ በአሉ ግርማን ‹‹ኦሮማይ›› መፅሀፍ እንግሊዘኛ ትርጉም ለአንባቢያን ማቅረቡን አስታወቀ፡፡
ይህ መፅሀፍ ዛሬ ለገበያ ከመዋሉ በፊት ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ መፅሀፉን ወደእንግሊዘኛ የተረጎሙት ዴቪድ ደጉስታና መስፍን ፈለቀ ይርጉ ሲሆኑ አራት መቶ ገፆች ያሉት ነው፡፡
አሳታሚ ድርጅቱ የመፅሀፉ ዋጋ ሀያ ፓውንድ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ስለእንግሊዘኛው ትርጉም ከመፅሀፉ ጀርባ አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል ዘ ሻዶ ኪንግ የተሰኘ አለም አቀፍ ተወዳጅነትና ሽልማት ያገኘው መፅሀፍ ደራሲዋ መአዛ መንግስቴ አንዷ ናት፡፡ መአዛ ‹‹ኦሮማይ አስገራሚ የአብዮትና የክህደት ታሪክ ነው፡፡
በተጨማሪም የጥበበኛው፣ አስተዋዩና ቁርጠኛው የፀጋዬ ታሪክ ነው፡፡ በአሉ ይህን መፅሀፍ እንደፃፈ መሰወሩ የቃላት ሀይል ከአገዛዞች በላይ ያለውን ሀይል የሚያሳይ ምስክር ነው›› ብላለች፡፡ ጨምራም ኦሮማይ ለአዲሱ አንባቢ ትውልድ ስጦታ መሆኑን ጠቅሳለች፡፡