የቅዱስ ፋሲል ባህረ ጥምቀት
| አርባ_አራቱ_ታቦታት
"ጎንደር"ማለት "ጉንደ ሀገር" ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም "የሃገር ግንድ፣ የሀገር መሰረት፣ ርዕሰ ሃገር ወይም የሀገር ራስ ማለት ነው።
ይኼውም ኖህ ከጥፋት ውሐ በኋላ የተቀመጠበት በእንተላ፣ በአይዋርካ፣ በሽሌ፣ በአይከል፣ በኩል አድርጎ ጎንደር ላይ ብዙ ዘመን ፈጣሪውን እያመሰገነ እየቀደሰ የኖረባትና የተቀበረባት ቦታ በመሇኗ የሃገር መጀመሪያ ዋና ግንድ ተባለች።
እንዲያውም በ950 ዓ.ዓ ኖህ ሲሞት መቃብሩ ላይ ምንጭ ፈልቆ በርካታ ሰዎችን ይፈውስ ነበር። ከዚያም ለኖህ መታሠቢያ ይሆን ዘንድ አምላክ በቤተመንግስት አሳቦ የኖህ የመቃብር ሐውልት እንዲታነጽ ፈቀደ። ይህም በኋለኛው ዘመን በንጉሥ ፋሲለደስ የታነጸው የፋሲል ግንብ ነው።
ዐፄ ፋሲለደስም በ1629 ዓ.ም በመሀንዲስ አባ ገብረክርስቶስ መሪነት የእደ ጥበብ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ከኖህ መቃብር ላይ የቤተመንግሥቱን ታላቅ መሰረት ጥለውታል። ግንባታውም በ7 አመት ውስጥ ተጠናቀቀ።
ከዚህ በኋላ ዐፄ ፋሲል በቀሐ ወንዝ አጠገብ "ማንኪት" የሚባለውን ህንጻ በ17ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ግቢ መሀል ላይ 50 ሜትር በ25 ሜትር ስፋትና 2 ሜትር ጥልቀት ያለው የባህረ ጥምቀት ገንዳ አስገነቡ፡፡ ከቀሃ ወንዝ በተቆፈረ ቦይ ውሐ ተጠልፎ እንዲገባ አደረጉ።
ከዛን ጊዜ ጀምሮ ገንዳው ለጥምቀት በዓል መጠመቂያነት የሚያገለግል ሲሆን፣ ዐፄ ፋሲል ባሰሩት ጥንታዊ ህንፃ ደግሞ የታቦታቱ ማደሪያ ሆኖ ያገለግላል። መዋኛ ገንዳው በባእሉ ሰሞን የባንዲራ መቀነት ይታጠቃል፡፡
ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከሆነችበት እስከ ጎንደር ዘመን ማክተሚያ ፈፃሜ መንግሥት አፄ ተክለ ጊዮርጊስ ድረስ 18 ነገሥታት የነገሱ ሲሆን እነዚህም አብዛኛዎቹ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተዋል፡፡
44 የሚባሉት አብያተ ክርስቲያናት ጎንደር የመንግሥት ከተማ ከመሆኗ አስቀድሞ የተተከሉበትን ጨምሮ እስከ ፈፃሜ መንግሥት ተክለ ጊዮርጊስ ድረስ የተተከሉትን ብቻ ሲሆን ቁጥራቸውም 44 ነው፡፡
ከዚያ ወዲህ ከዘመነ መሣፍንት እስከ አሁን የተተከሉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም ከ44ቱ የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ በአጠቃላይ አርባአራቱ ታቦታተ በጎንደር ዘመን በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚገኙና የነበሩ 44 አብያተ ክርስቲያናት ጥቅል ስም ነው፡፡
ይህም ማለት አሁን ባለው የጎንደር ከተማ ክልል እና ዙሪያውን በሚገኙ አዋሳኝ የገጠር ቀበሌዎች ለምሳሌ፣ ጠዳ፣ ፈንጠር፣ ብላጅግ፣ ደፈጫ እና በመሳሰሉት ቦታዎች የሚገኙ አጠቃላይ የአድባራት ቁጥር ነው፡፡
#የአርባ_አራቱ_ታቦታት_ስም_ዝርዝር፦
1-አዘዞ ተ/ሃይማኖት
2-ፊት አቦ
3-ፊት ሚካኤል
4-አደባባይ ኢየሱስ
5-ግምጃ ቤት ማርያም
6-እልፍኝ ጊዮርጊስ
7-መ/መ/መድኃኔዓለም
8-አቡን ቤት ገብርኤል
9-ፋሲለደስ
10-አባ እንጦንስ
11-ጠዳ እግዚአብሔር አብ
12-አርባዕቱ እንስሳ
13-ቀሐ ኢየሱስ
14-አበራ ጊዮርጊስ
15-አደባባይ ተ/ሃይማኖት
16-ደብረ ብርሃን ሥላሴ
17-ዳረገንዳ ኤዎስጣቴዎስ
18-አጣጣሚ ሚካኤል
19-ጐንደር ሩፋኤል-
20-ደፈጫ ኪዳነ ምህረት
21-ቅ.ዮሐንስ መጥምቅ
22-ጐንደር ልደታ ማርያም
23-ሠለስቱ ምዕት
24-ጎንደር በአታ ለማርያም
25-ወ/ነጐድጓድ ዮሐንስ
26-ጐንደር ቂርቆስ
27-ጐንደር ሐዋርያት(ጴጥሮስ ወጳውሎስ )
28-ፈንጠር ልደታ
29-ሰሖር ማርያም
30-ወራንገብ ጊዮርጊስ
31-ምንዝሮ ተ/ሃይማኖት
32-ደ/ፀሐይ ቊስቋም
33-ደ/ምጥማቅ ማርያም
34-አባ ሳሙኤል
35-ጐንደሮች ማርያም
36-ጐንደሮች ጊዮርጊስ
37-አባ ጃሌ ተ/ሃይማኖት
38-ዐቢየ እግዚእ.ኪ/ምህረት
39-ብላጅግ ሚካኤል
40-አሮጌ ልደታ
41-ጫጭቁና ማርያም
42-ጋና ዮሐንስ
43-አይራ ሚካኤል
44-ዳሞት ጊዮርጊስ
***
ነገረ
ጥምቀት፤
“ጥምቀት” ለሚለው ቃል መነከር፣ መታጠብ የሚሉ ትርጓሜዎች ይሰጣሉ፡፡ የጥምቀት ዋዜማ የሆነው ከተራ ደግሞ ውኃውን/ባህሩን አገደ፣ ከበበ፣ አጠራቀመ እንደማለት ነው።
በኦርቶዶክሳዊቷ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በ30 ዓመቱ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 11 ቀን 31 ዓ.ም. (5531 ዓመተ ዓለም) በአጥማቂው ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ባሕር የተጠመቀበትን ዕለት የሚያስታውስ ነው፡፡ ‹‹ኤጲፋንያ›› በመባልም ይታወቃል፡፡
በየዓመቱ በመላ ኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ክርስትያን አማኞች ዘንድ የሚከበረው የጥምቀት በዓል፣ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው፣ በየባሕረ ጥምቀቱ የሚከበሩ በመሆናቸው፣ አገሬውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መስህብነትን በመጎናጸፉ፣ ቱሪስቶችን እንደሳበ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ እስከ ላሊበላ፣ ከአክሱም እስከ ጎንደር፣ ከሐዋሳ እስከ ጅማ፣ ከአሶሳ እስከ ጋምቤላ በሁሉም ሥፍራዎች በዚሁ ዓይነት ደምቆ ይከበራል። የምእመናኑም ሆነ የካህናትና ዲያቆናት አለባበስ በሚማርኩ ባህላዊ አልባሳት የተዋበ በመሆኑ ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ ለሚመጡ ጎብኚዎች ሁልጊዜ አዲስ ነው።
ከሃይማኖታዊው ሥነ ሥርዓት በኋላ ካህኑ በሃሌታ፣ ወንዱ በሆታ፣ ሴቱ በእልልታ ታቦተ ሕጉን አጅበው፣ እንደየአመጣጣቸው ወደየአጥቢያቸው ይመለሳሉ።
የጥምቀት በዓል ልክ እንደ መስቀል በዓል ሁሉ ታህሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም በ UNESCO በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል።