🐪 ትራምፕ ኢራን እንድትደመሰስ ትዕዛዝ ሰጡ!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፥ ኢራን እርሳቸውን የምትገድላቸው ከሆነ፥ አሜሪካ ኢራንን እንድታወድም የሚያደርግ ትዕዛዝ ለአማካሪዎቻቸው ማስተላለፋቸውን ተናገሩ።
ትራምፕ ይህን የተናገሩት፥ እርሳቸው የሚመሩት የአሜሪካ መንግስት ኢራን ላይ ከፍተኛ ጫና ለማሳደር የሚያግዙ ፖሊሲዎችን ማስፈጸሚያ ትዕዛዝ ላይ ፊርማቸውን ባኖሩበት ወቅት መሆኑን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።
ከኢራን መሪዎች ጋር በቴህራን ፊት ለፊት ተገናኝቶ የመምከር ፍላጎት እንዳላቸው የተናገሩት ትራምፕ፥ "እነርሱ እኔን የሚገድሉኝ ከሆነ፥ ኢራን እንድትወድም ለአማካሪዎቼ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ። ይህም አንዳች ነገር እንዳይቀራቸው ያደርጋል" ማለታቸውን ዘገባው አክሏል።
ሆኖም ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ቢገደሉ ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ መንበረ ስልጣኑን የሚረከቡ ይሆናል የሚለው የአሶሼትድ ፕረስ ዘገባ፥ ይህ ደግሞ ቀዳሚው ፕሬዝዳንት ያስቀመጠውን ትዕዛዝ እንዲያስፈጽም የሚያስገድደው አለመሆኑን ጠቅሷል።
የ78 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ታዲያ "ኢራን እኔን ከገደለችኝ፣ እንድትወድም ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ" ማለታቸው፥ በምን አግባብ ይፈጸማል የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።
ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ማገባደጃ ማለትም እ.ኤ.አ 2020 ላይ የኢራን እስላማዊ አብዮት ዘብ መሪ የነበሩትን ቃሲም ሶሌይማኒን ካስገደሉ በኋላ፥ የትራምፕና ኢራን ፍጥጫ ከፍ ወደአለ ምዕራፍ መሸጋገሩ ይነገራል።
ከኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮግራም ጋር በተያያዘ ዶናልድ ትራምፕ የሚያንጸባርቁት አቋምና እርሱን በተመለከተ የሚከተሉት ፖሊሲ ደግሞ ጡዘቱን አንሮታል።
ፕሬዝዳንቱ ኢራን በዚህ ሰዓት "እጅግ ጠንካራ" በሚባል ቁመና ላይ ስለመሆኗ ግን ከመናገር አልተቆጠቡም።