"የ2017 የት/ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2017 የት/ዘመን ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ-12ኛ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ለስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በናሙናነት ተመርጠው የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡
በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ2016 የት/ዘመን ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 የት/ዘመን የሚፈተኑም አሉ፡፡
የፈተና ዝግጅቱ:
የኢኮኖሚክስ ትምህርት በአዲሱ ስራአተ ትምህርት የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ ይዘጋጃል ተብሏል።
@Temari_podcast

በመሆኑም በ2017 የት/ዘመን የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና "ከላይ የተገለፁትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባና ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል" ብሏል አገልግሎቱ።
የፈተና ዝግጅቱ:
1. ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣
2. ከ10ኛ ክፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
3. ከ11ኛ ከፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
4. ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።