ሰላም የአብይ መጥፊያ; ሰላም-በትግል ብቸኛው መፍትሔ!
===============
አብይ አህመድ ያለ ግጭትና ጦርነት መኖር ኣይችልም:: ብቸኛው የህልውናው መሠረት ጦርነት ነው:: ሰላም: የአብይ አህመድና ሥርዓቱ መጥፊያው ነው:: በድርድርም ሆነ በትግል ሰላምን የትኩረቱ ማዕከል ያደረገ ማንኛውም ኃይል በቀላሉ ሊረታው እንደሚችል ስለሚያውቅ: የሰላምን ሂደት ለማደናቀፍ ብዙ ርቀት ይጏዛል::
የፕሪቶሪያውን የሥምምነት ቃል እንዳይፈጸም: ይዘቱም በተግባር በሥራ ላይ እንዳይውል መቆየቱም ለዚህ ማሳያ ሆኖ ሊወሰድ ይችላል::
ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (WBO) ጋርየተደረጉ የድርድር ጅማሬዎችን ማጨንገፉም ሌላው ማሳያ ነው::
ከአማራ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ድርድር ለማድረግ አለመፈለጉና ልዩነቱን በኃይል ብቻ ለመፈጸም መጣጣሩም ይሄኑ የሰላም ፍራቻ የሚያጎላ ባህርይ ነው::
በተደጋጋሚ ልዩነትን በጉልበትና በወታደራዊ መንገድ ብቻ ለመፍታት መሞከሩ: ይሄንንም ለማስፈጸም በየጊዜው የሚፈበረኩ የሴራ ትርክቶችን ማሰራጨቱ: በእነሱም ላይ ተንተርሶ ርካሽ የፕሮፓጋንዳ ሥራ መሥራቱ: ... ይሄ ሁሉ: ጦርነትን ለማጀገን የሚጠቀምበት መንገድ ነው::
ይሄ: የሥርዓቱን ነፍጠኛነት: የሚያረጋግጥ ባህሪ ነው:: በጉልበት ረግጦ መግዛት የአሰራር ዘይቤው መሆኑን የሚይሳይ ሁለተኛ ተፈጥሮው (second nature) ነው::
ሰሞኑን በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተነዛ ያለው የጦርነት ዛቻና ማስፈራራትም (በትግርኛ የተላለፈው መግለጫውም ሆነ በፊንፊኔ የተመደረከው 'ሰላማዊ' ሰል)የዚሁ አካል ነው:: የአብይን ጸረ-ሰላምነት በድጋሚ ያረጋገጠ ተግባር ነው: የሥርዓቱን ጦረኝነት የሚመሰክር ሁነት ነው:: በኦሮሚያና በኦሮሚያ ሚሊሻን በማሰልጠንና በማስታጠቅ ሥም እየተካሄደ ያለው መንግሥት-መር ማሕበረሰባዊ ጦረኝነትም የዚሁ ሥርዓታዊ ጦረኝነትና መንግሥታዊ አሸባሪነት መገለጫ ነው::
በመሆኑም: ይሄንን ጸረ-ሰላም ኃይል ለማንበርከክ (ወይም ለማስወገድ): ሰላምን ማዕከል ያደረገ ትግል አማራጭ የለውም::
እስካሁን ያሉት ሙከራዎች ይሄን አላሳዩም እንጂ: ከተቻለ በድርድር ሰላምን ማዕክላዊ ኣጀንዳ ማድረግ: ካልተቻለ በትግል ሰላምን ለማስፈን (እፎይታን ለማምጣት) በትብብርና በቅንጅት መታገል ኣማራጭ-የለሽ የመፍትሔ ኣቅጣጫ ነው::
ሰላምን በትግል ለመመሥረት መንቀሳቀስ የወቅቱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው:: ብቸኛው የፖለቲካ መሰባሰቢያም ነው::
In some circumstances, especially in the face of fascistic war-mongers and genocidaires, war becomes the only means to establish peace. War becomes the only politics that can counter the politics of war.
#ሰላም_በትግል_ብቸኛው_መፍትሄ_ነው!!
#No_to_Abiys_wars!