🔴ውድ የ XE COMBO ቤተሰቦች፣ ዛሬ ደግሞ እስቲ ስለ ጊዜ 🕐 እናውራ።
ሁላችንም ስለ ጊዜ ትርጉምና አጠቃቀም በደምብ መረዳትና አስተሳሰባችንና እንቅስቃሴያችን በጊዜ ላይ የተቃኘ መሆን አለበት።
ሁላችንም ቢሆን ማወቅ ያለብን ጊዜ ማለት ልክ በእፍኛችን የያዝነው አሸዋ ሳይታወቀን ፈሶ እንደሚቀው ሁሉ ሳይታወቀን ዳግም ሳይመለሰ እንደሚያልፍ ነው። ⏳
ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ጊዜን በአግባቡ የሚጠቀሙ ስኬታማ ህይወት ነው የሚኖራቸው። በአንጻሩ ደግሞ ጊዜን መገንዘብ ህይወትን መገንዘብ ነው የሚለውን መርህ ያልተገነዘቡ መቼም ቢሆን በ ዉስጣቸው ያለውን እምቅ ችሎታ አይገነዘቡም።
ሁሉንም እኩል የሚያደርገው ጊዜ ነው። ሃብታም ብንሆን ደሃ አሜሪካ ብንሆን ኢትዮጵያ ለእያንዳንዳችን በ24 ሰአት የተከፋፈሉ ቀናት ናቸው ያሉት።
እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ከ ቀሽሞች የሚለዩት በ ጊዜ አጠቃቀማቸው ነው። ጊዜን መጠቀም ማለት ያለ እረፍት በስራ መጠመድ ማለት አይደለም። ይልቅስ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም መቻል በህይወታችን ትርጉም ያላቸውንና መስራት የሚያስደስተንን ነገሮች ዘና ባለ መልኩ እንድናከናውን ነው የሚያስችለው።
✔️ቅድሚያ መስጠት በሚገባህ ነገሮች ላይ የማተኮርን ባህል አዳብር።
✔️በህይወት ውስጥ የበለጥ ትርጉም ያላቸውን ነገሮች ለመናኛ ነገሮች የበለጠ ጊዜ በመስጠት በከንቱ መስዋት ማድረግ የለብህም።
✔️ጊዜን በተመለከተ ኮስታራ መሆን አለብህ። አይሆንም ለማለት መድፈር አለብህ ለጥቃቅን ነገሮች በርህን የመዝጋት ልምድ ማዳበር ለትላልቅ ነገሮች በርህን በቶሎ ለመክፈት ያስችልሃል።
✔️በወሳኝ ነገሮች ላይ ሰትጠመድ ስልክህን ዝጋ።
✔️ስልክህ በጮኸ ቁጥር አታንሳ። ስልክህ አንተ ስትፈልገው የምትጠቀምበት ቁስ ነው እንጂ የሌሎች መገልገያ አይደለም።
የሚገርመው ነገር ሰዎች የበለጠ የሚያከብሩህ ጊዜህን በተመለከተ ቀልድ ያማታውቅ መሆንህን ሲያውቁ ነው። አንተ ለጊዜህ ክብር ስትሰጥ ሌሎችም ጊዜህን ያከብሩልሃል። ✔️