አሮጌውን አዳም ሊገርዝ ሊገራ፣
ተወለደ መሲህ በተናቀ ስፍራ፣
ከበደል ኩነኔ ከፍጥረት 'ሀ' አመፃ፣
ሊያድነዉ ወረደ በደሙ ሊያነፃ።
ከመብል ያለፈ ትርጉም ምንሰራበት፣
ካሰበልን ጋራ ምንገናኝበት፣
በደም ታጥቦ በምህረቱ እንደቆመ፣
መኖር ይሁንልን ታሞ እንደታከመ።
ተወለደ መሲህ በተናቀ ስፍራ፣
ከበደል ኩነኔ ከፍጥረት 'ሀ' አመፃ፣
ሊያድነዉ ወረደ በደሙ ሊያነፃ።
ከመብል ያለፈ ትርጉም ምንሰራበት፣
ካሰበልን ጋራ ምንገናኝበት፣
በደም ታጥቦ በምህረቱ እንደቆመ፣
መኖር ይሁንልን ታሞ እንደታከመ።
እንኳን የጌታችን የመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ የዜማ Tube ቤተሰቦች