መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) dan repost
[ስለ ሕዋ ዐለቶች በምዕራብ ኢትዮጵያ ስለወደቀው ዐለት]
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 በቅርቡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ይልቁኑ በጅማ የቡ ከተማ ስለተሰማው ድምፅና ስለታየው የተሰባበረ ዐለት ጥቂት ለማለት ወደድኹ።
ከሰማይ ስለሚወድቁ የሕዋ ዐለቶች ለመረዳት፦
1. አስትሮይድ
2. ሜትዮራይድ
3. ሚትዮር
4. በሜትሮይት
መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት መረዳት ያስፈልጋል፡-
1. አስትሮይድ
💥 በዋነኛነት በማርስ እና በጁፒተር መካከል ባለው የአስትሮይድ ቀበቶ ውስጥ የሚገኙት ዐለታማ ሥሪትነት ያላቸው አካላት ናቸው። መጠናቸውን ለመረዳት ለምሳሌ አስትሮይድ ቬስታ መጠኑ 329 ማይል (530 ኪሎ ሜትር) ዲያሜትር ያለው ሲኾን ከታናናሾቹ ውስጥ ከ33 ጫማ (10 ሜትር) በታች የኾኑም ይገኙበታል። የኹሉም አስትሮይድ አጠቃላይ ክብደት ግን ከምድር ጨረቃ ያነሰ ነው።
👉 በዚኹ አጋጣሚ በኢትዮጵያ አቆጣጠር ዐርብ ሚያዝያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠር ኤፕሪል 13/ 2029 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ከምድር በላይ 30,600 ኪሎ ሜትር (19,000 ማይል) ርቀት ላይ የሚያልፍ ሲኾን ቢሊዮኖች በዐይናቸው ያዩታል። መሬትን የመመታት ዕድሉ 2.7 ፐርሰንት ብቻ ነው። (አንድሮሜዳ ክፍል 2 ገጽ 388 - 394 )
2. ሜትዮራይድ
💥 ሜትዮራይዶች በሕዋ ያሉ ትናንሽ ዐለቶች ሲኾኑ መጠናቸው ከከሸዋ ቅንጣት እስከ 1 ሜትር አካባቢ ይደርሳሉ። አንዳንድ ሜትዮራይድ ዐለቶች ሲሆኑ ሌሎቹ ደግሞ ብረታ ብረት ወይም የድንጋይ እና የብረት ውሕዶች ናቸው። ሜትዮራይድ ብዙ ጊዜ ከአስትሮይድ ወይም ከኮሜት ወይም ከሌሎች ፕላኔቶች ጭምር የሚመጡ ናቸው። በአጠቃላይ ሜትዮራይድ ስንል ገና በሕዋ ላይ ያሉትን ነው።
3. ሚትየር
💥 ከላይ እንዳየነው ሜትዮራይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ወይም ወደ ሌላ ፕላኔት በከፍተኛ ፍጥነት ሲገቡ እና ሲቃጠሉ ሚትዮር ይባላሉ። በሌላ አጠራር “ተወርዋሪ ኮከቦች” ብለን የምንጠራቸው ሲኾን አንዳንድ ጊዜ ሜትየሮች ከቬኑስ የበለጠ ብሩህ ኾነው ሊታዩ ይችላሉ። ያን ጊዜ “የእሳት ኳሶች” ተብለው ይጠራሉ። ብዙ ተወርዋሪ ከዋክብት በአንድ ላይ በሰዓታት ሲታዩ "ሜትየር ሻወር" በመባል ይታወቃሉ።
4. ሜትሮይት
💥 ሳይቃጠል የምድርን ከባቢ አየር ዐልፎ በምድር ላይ የሚያርፍ የሜትሮይድ ቁራጭ መጠሪያ ነው። በሰዓት በዐሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኃይለኛ ግፊት ወድቆ ሲበታተን ብሩህ ነበልባል ይመስላል።
ሜትሮይትስ በሦስት ዋና ዋና ዓይነቶች ይከፈላሉ፡-
1) ድንጋያማ ሜትሮይትስ (በዋነኛነት ከሲልኬት) ማዕድናት የተውጣጡ ናቸው)፣
2) የብረት ሜትሮዮትስ (በአብዛኛው ከብረት-ኒኬል ውሕዶች የተውጣጡ ናቸው)
3) ድንጋያማ ብረት ሜትሮይትስ (በግምት እኩል መጠን ያላቸው የሲሊኬት ማዕድናት እና ብረት ኒኬል ይዘዋል)
👉 ሜትሮይቶች ሲታዩ የምድር ዐለቶችን ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ የሚያብረቀርቅ ሊመስል የሚችል የተቃጠለ ውጫዊ ክፍል አላቸው። ይኸውም በከባቢ አየር ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ የሜትሮይት ውጫዊ ገጽታ ሲቀልጥ የሚፈጠር ነው።
👉በምድር ላይ ከ 50,000 በላይ ሜትሮይትስ ተገኝተዋል.
ከእነዚህ ውስጥ 99.8% የሚሆኑት ከአስትሮይድ የሚመጡ ናቸው።
👉 በየቀኑ 48.5 ቶን የሜትሮይት ቁስ አካል ወደ ምድር ይወድቃል። ይህም በዓመት 17,000 ሚቴዮራይትስ እንደማለት ነው። አብዛኛው ግን በከባቢ አየር ውስጥ ተንኖ ተወርዋሪ ኮከብ ይኾናል።
👉 በቅርብ የተከሰቱ አደገኛ የሜትሮይትስ ክስተቶች ውስጥ ኹለቱን በማንሣት ጽሑፌን ልቋጭ፦
1ኛ) በዘመናዊ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ሜትሮይድ ወደ ምድር ከባቢ አየር ውስጥ የገባው እኤአ በ1908 ሲኾን የቱንጉስካ ክስተት በመባል ይታወቃል። ይህ ሜትዮር በሩሲያ በሳይቤሪያ ላይ የተከሰተ ሲኾን ምድሩን ሳይመታ በፊት በአየር ላይ ጥቂት ማይል ርቀት ላይ ፈነዳ።
👉 የፍንዳታው ኃይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ስፋት ባለው ክልል ውስጥ ዛፎችን ለማውደም የሚያስችል ኃይለኛ ነበር። ሜትዮሩ 120 ጫማ (37 ሜትር) ስፋት ያለው እና 220 ሚሊዮን ፓውንድ (100 ሚሊዮን ኪሎ ግራም) ይመዝን ነበረ። በአካባቢው በመቶዎች የሚቆጠሩ አጋዘኖች ሲሞቱ ነገር ግን ማንም ሰው በፍንዳታው መሞቱን የሚያሳይ ቀጥተኛ መረጃ የለም።
2ኛ) እ.ኤ.አ. በ 2013 በቼልያቢንስክ ሩሲያ ሰማይ ላይ ቤትን የሚያህል ሜትሮይድ በሰከንድ ከ11 ማይል (18 ኪሎ ሜትር) በላይ ወደ ከባቢ አየር በመግባት ከመሬት በላይ 14 ማይል (23 ኪሎ ሜትር) ላይ ፈነዳ። ፍንዳታው ወደ 440,000 ቶን የሚገመተውን የቲኤንቲ ኃይል በመልቀቁ ከ200 ስኩዌር ማይል (518 ስኩዌር ኪሎ ሜትር) በላይ መስኮቶችን የሰባበረ እና ሕንፃዎችን ያበላሽ አስደንጋጭ ኹኔታን ፈጠረ። በፍንዳታው ይልቁኑ በመስታወት ስብርባሪ ከ1,600 በላይ ሰዎች ቆስለዋል።
(ስለ ሥነ ፈለክ ለመረዳት አንድሮሜዳ ክፍል 1፤ አንድሮሜዳ ክፍል 2፤ ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ)