'ግራ የተጋቡ ዕለት'
ከዕለታት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነሣ
ወደ ውጭ ልወጣ ጫማዬን ሳነሣ
ሸተተኝ ... 'ሳምቡሳ ... ሳምቡሳ'
ወዲያው ወጣኹና ሻይ ቤት ገሰገስኩኝ
ገብቼ ስቀመጥ ብርጭቆ ሰበርኩኝ
ለማንሣት ሲሯሯጥ ደግ አስተናጋጁ
ከአፈር ደባልቄ አቆምኩበት በእጁ
የተሰበረውን ከመሬት ሲያነሣ
እኔም አልኩት . . .
አምጣልኝ አንድ 'ሳምቡሳ'
"አኹን አታገኝም ማታ ተመለሳ!?"
አለኝ . . .
እኔም ተመዘግዝጌ ስወጣ ከቤቱ
ከጓሮ መጣና ጠራኝ ባለቤቱ
"በጠዋቱ መጥተህ ልባችንን ሰበርከው
ና ክፈል ለሰበርከው"
አለኝ . . .
ሳየው ዓይኑ ሲንፈራፈር
አጎንብሼ ወደ አፈር . . .
አረመምኩ . . . ቻልኩት
'ለዚች ጥቂት ነገር ልባችሁን ሰበርኩት?!'
እያልኩኝ በውስጤ ...
ጠፋኝ መላቅጤ
ምክንያቱም ...
ብርጭቆውን ከመስበሬ የተነሣ
ሳልበላ ላድር ነው ያማረኝን 'ሳምቡሳ'😁
እንግዲህ ወዳጄ ሕይወት እንዲህ ናት፥ አትማረር!!
@Yoppoem
ከዕለታት አንድ ቀን ከእንቅልፌ ስነሣ
ወደ ውጭ ልወጣ ጫማዬን ሳነሣ
ሸተተኝ ... 'ሳምቡሳ ... ሳምቡሳ'
ወዲያው ወጣኹና ሻይ ቤት ገሰገስኩኝ
ገብቼ ስቀመጥ ብርጭቆ ሰበርኩኝ
ለማንሣት ሲሯሯጥ ደግ አስተናጋጁ
ከአፈር ደባልቄ አቆምኩበት በእጁ
የተሰበረውን ከመሬት ሲያነሣ
እኔም አልኩት . . .
አምጣልኝ አንድ 'ሳምቡሳ'
"አኹን አታገኝም ማታ ተመለሳ!?"
አለኝ . . .
እኔም ተመዘግዝጌ ስወጣ ከቤቱ
ከጓሮ መጣና ጠራኝ ባለቤቱ
"በጠዋቱ መጥተህ ልባችንን ሰበርከው
ና ክፈል ለሰበርከው"
አለኝ . . .
ሳየው ዓይኑ ሲንፈራፈር
አጎንብሼ ወደ አፈር . . .
አረመምኩ . . . ቻልኩት
'ለዚች ጥቂት ነገር ልባችሁን ሰበርኩት?!'
እያልኩኝ በውስጤ ...
ጠፋኝ መላቅጤ
ምክንያቱም ...
ብርጭቆውን ከመስበሬ የተነሣ
ሳልበላ ላድር ነው ያማረኝን 'ሳምቡሳ'😁
እንግዲህ ወዳጄ ሕይወት እንዲህ ናት፥ አትማረር!!
@Yoppoem