ውዳሴ ማርያም የሚጸልይና የማይጸልይ🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋💠
የእመቤታችን ውዳሴ ማርያም የዕለቱን ውዳሴ ማርያም
በየዕለቱ የሚጸልይ ሰው የእናት አባቱን ርስት የወረሰ ይመስላል።
የሰባቱን ዕለት ውዳሴ ማርያም በእድሜዋ ልክ በየዕለቱ የሚጸልይ ደግሞ የዘመዶቹን ጨምሮ የወረሰ ይመስላል።
እመቤታችን ሳያመሰግን የሚውል ሰው ምን ይመስላል ቢሉ፦
ከሰው ቤት ድግስ ተጠርቶ ሂዶ በር ላይ ሲደርስ ውኃ ተደፍቶበት፥ ተቆጥቶ የሚመለስ፤ እንቅፋት እየመታው እየወደቀ እየተነሣ እየተሰበረ የሚሄድ ይመስላል።
ያ ሰው ካለመብላቱ በላይ እየተሰበረ እንደሄደ እመቤታችን የማያመሰግንም በመከራ ሥጋ ላይ መከራ ነፍስ ይጸናበታል። በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ይጨመርበታል።
እኛ ግን፦"አማንኬ ይደልወኬ አስተብፅዖ እስመ ኮንኪ እሞ ለእግዚአብሔር አዶናይ -የከሃሊ ኩሉ እግዚአብሔር እናት ሆነሻልና ብፅዕት መባል በእውነት ይገባሻል" እንላታለን።
ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
http://t.me/abagebrekidanhttp://t.me/abagebrekidan 🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋🎋💠