Abrham2319
#ጾምን ቀድሱ ጉባኤውንም አውጁ
ት•ኢዩ 1:14
ጾም ማለት "ጾመ" ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተከለከለ ተወ ታቀበ ታረመ ማለት ነው::
ጾም ማለት ራስን ከእህል ከውሃ ብሎም እግዚአብሔር ከሚጠላቸው ነገሮች ወይም ከክፉ ምግባራት ሁሉ ራስን መከልከል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ በማስገዛት መቆየት ማለት ነው::
"ራሳችሁን ጠብቁ በመብልና በመጠጥ በመቀማጠልና የዓለምን ኑሮ በማሰብ ልባችሁን አታደንድኑ ያ ቀንም በድንገት እንዳይመጣባችሁ"
...