በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha


Every one comment us about the informations that we are uploading. you are also very wellcommed to give us nominations which helps us to improve our capability with regard to the concerns of the organization.

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri




የኢሬቻ የአደባባይ በዓል ህብረተሰቡ የመዲናችንን የውበትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በጥልቀት እንዲረዳ ትልቅ አጋጣሚን ይዞ መጥቷል።

የአደባባይ በዓላት ህዝባዊ አንድነትንና ባህላዊ እሴቶችን ከማሳደግ ባለፈ የመዲናችንን ውበትና አረንጓዴ ልማት ለመንከባከብና ዘላቂ ለማድረግ ትልቅ መድረክ በመሆን ያገለግላሉ።

በዓላቱ በሰፊው የህብረተሰብ ክፍል ዘንድ የሚጠበቁና በከፍተኛ ድምቀት የሚከበሩ በመሆናቸው ስለ አካባቢ ጥበቃና ውበት የላቀ የህዝብ ግንዛቤን ለመፍጠር ምቹ አጋጣሚዎችን ይፈጥራሉ።

የውበትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ከባህላዊ በዓላቶቻችን ጋር በተደራጀ መልኩ ሲተሳሰሩ ውበትን የመጠበቅ ልማድ ቀስ በቀስ ህብረተሰባዊ ባህል እየሆነ ይመጣል።

ይህም በህዝቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ከማሳደጉም በላይ ህብረተሰቡ ከአረንጓዴ ልማት የሚገኙትን ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች—ከአየር ንብረት መስተካከል ጀምሮ እስከ ስነ-ልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች—በሚገባ እንዲረዳ ያደርገዋል።

በዚህ ሂደት ውስጥ አካባቢን መንከባከብ የአንድ ወገን ብቻ ሳይሆን የጋራ ኃላፊነት መሆኑን እያንዳንዱ ዜጋ እንዲገነዘብ ያስችላል።
በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚከበረው የኢሬቻ የአደባባይ በዓል ህብረተሰቡ የመዲናችንን የውበትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች በጥልቀት እንዲረዳ ትልቅ አጋጣሚን ይዞ መጥቷል።

ይህ በዓል ከተፈጥሮና ከባህል ጋር በጥብቅ የተሳሰረ በመሆኑ ህዝቡ ልክ እንደ ባህላዊ በዓሉ ሁሉ የአረንጓዴነትንና የጽዳትን ባህል ወደ ውስጡ በማስረጽ ከተማችንን ለኑሮ ምቹና ለዓይን ማራኪ የማድረግን ራዕይ በተግባር እንዲያሳካ የላቀ ዕድል ይሰጣል።




አቶ ግርማ ሰይፉ አዲስ ለተሾሙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ በተሰጡ ሹመቶች መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ  ኃላፊ የነበሩት አቶ ግርማ ሳይፉ አዲስ ለተሾሙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል የስራ ርክክብ አድርገዋል።

በከተማዋ በሁሉም መዳረሻ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ መሰረተ ልማት ስራዎች ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከሁሉም ማህበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ለአንድ ግብ በጋራ ተግባብተው መስራት እንዳለባቸው አቶ ግርማ ሰይፉ ምክረ ሃሳብ ሰጥተዋል።

ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል በበኩላቸው ተቋሙ የሚሰራቸው ተግባራት በበርካታ የስራ አጋጣሚዎች እንደሚረዱት ጠቅሰው በቀጣይም ከቢሮው አመራር እና ሰራተኞች ጋር በአንድ መንፈስ ተግባብተንና ተስማምተን በጥሩ የስራ መንፈስ ጥሩ ዉጤት ማምጣት እንደሚጠበቅ እና ለዚህም ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።

ቢሮው ለቀድሞው ኃላፊ ለነበሩት አቶ ግርማ ሳይፉ በነበራቸው ቆይታ በዘርፉ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመሰገነ አዲስ ለተሸሙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል መልካም የስራ ዘመን ተመኝቷል።




የኢሬቻ በዓል ተከትሎ ለእንግዶች በቂ የተንቀሳቃሽ የንፅህና ቤት አቅርቦት ልዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መጠናቀቁ ተገለፀ ፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ የአደባባይ ክብረ በዓል ባህላዊ እሴቱን እና ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል ከፍተኛ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም በመዲናዋ የሚከበረውን ይህንን ታላቅ በዓል ለመታደም ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እንግዶችን በደስታ ለመቀበል ከተማዋ ራሷን እያዘጋጀች ነው።

ለበዓሉ ታዳሚዎች ምቾትና ደህንነት ቀዳሚ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን ከተማዋን ውብና ንጹህ የማድረግ ዘመቻ በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።

በተለይም በበዓሉ ዕለት የባህሉ ተከታዮች ምንም ዓይነት እንግልት እንዳይገጥማቸው ለማድረግ ተንቀሳቃሽ የንፅህና መጠበቂያ ክፍሎች (ሞባይል መጸዳጃ ቤቶች) በአስፈላጊ ስፍራዎች ላይ እንዲዘጋጁ ተደርጓል።

ህዝቡም እነዚህን የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎቶች ያለምንም ክፍያ ሙሉ በሙሉ በነፃ መጠቀም የሚያስችልበት ሰፊ ዝግጅት መመቻቸቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ጌታሁን እንደገለጹት በቅርቡ በተከበረው የመስቀል በዓል ወቅት የተከናወኑት የተቀናጁ የውበትና የጽዳት ሥራዎች እጅግ ስኬታማ ነበሩ።

ይህንኑ መልካም ተሞክሮ መነሻ በማድረግ ለኢሬቻ ክብረ በዓልም የጽዳትና የማስዋብ ሥራው ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተደረገ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት መዲናዋ እንግዶቿን በደመቀ ሁኔታ ለመቀበል የአረንጓዴ መሠረተ ልማቶችን በመንከባከብ መናፈሻዎችንና አደባባዮችን በማስዋብ ረገድ የተለያዩ ተቋማት በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ።

ይህ ዝግጅት በዓሉ በሰላም በፍቅርና በታላቅ ድምቀት እንዲጠናቀቅ ከማስቻሉም በላይ የከተማዋን ገጽታ ለባዕዳንና ለአገር ውስጥ ጎብኚዎች በጥሩ ሁኔታ ለማሳየት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።




ከክረምቱ መገባደድ ጋር ተያይዞ የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶቻችንን እንክብካቤ ማጠናከርና መዲናችንን ማፍካት ወቅታዊና ወሳኝ ተግባር ነው።

የክረምቱ ዝናብ ማብቂያ ላይ በደረስንበት በዚህ ወቅት ለአረንጓዴ መሰረተ ልማቶቻችን የምናደርገውን እንክብካቤ ማጠናከር የአዲስ አበባን ውበትና አረንጓዴነት በዘላቂነት ለማስቀጠል ዋነኛው መንገድ ነው።

ይህ ተግባር በከተማችን ላይ አዲስ ተስፋን የሚያለመልም ከመሆኑም በላይ መዲናችንን በማፍካት የአዕምሮንና የዕይታችንን እርካታ የሚያበለፅግ ልዩ የተፈጥሮ ስጦታ ነው።

ለከተማችን መዘመንና ንፅህና በንቃት መሳተፍ የሚጠበቅብንን የዜግነት ኃላፊነት መወጣት ነው። ራሳችንን ከተፈጥሮ ጋር በማስተሳሰር እውነተኛና ያልተበረዘ ጤናማ ህይወት ለመምራት የአካባቢ ጥበቃ ሚናው የላቀ ነው። በመሆኑም እያንዳንዱ ነዋሪ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እንደ የዕለት ተዕለት ተግባሩ ሊቀበላቸው ይገባል።

ይህንን የተፈጥሮ ውበት በህፃናትና በታዳጊዎች ውስጥ ገና በለጋነታቸው ማስረፅ የነገውን ብሩህ ተስፋ ማረጋገጥ ነው። በዚህም የአርዓያነት መንፈስ የተላበሰ እና የአካባቢ ጤናማነት አቀንቃኝ የሆነ ንቁ ትውልድ ወደፊት ማምጣት ይቻላል። ዛሬ የምንተክለውና የምንንከባከበው እያንዳንዱ ተክል የነገው ጤናማና ማራኪ መዲናችን መሰረት ነው።




የአደባባይ በዓላት ላይ ማህበረሰቡ ለአረንጓዴ መሠረተ ልማት የሚያሳየው ጥንቃቄ የባለቤትነት መንፈስ ማረጋገጫ ነው ።

የአደባባይ በዓላት የባህል፣ የአንድነትና የደስታ መገለጫዎቻችን ናቸው። በእነዚህ ልዩ ወቅቶች በየአካባቢያችን የተገነቡትን የውበትና የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶች መጎብኘት ትልቅ መንፈሳዊ እርካታን ይሰጣል።

እነዚህ ውብ መናፈሻዎችና አደባባዮች የሀገራችንን እድገትና ስልጣኔ የሚያንጸባርቁ በመሆናቸው፣ በበዓላቱ ወቅት በእነዚህ ስፍራዎች እየተገኘን መዝናናትና መደሰት ተገቢ ነው። ከቤተሰብና ከወዳጅ ዘመድ ጋር የምናሳልፋቸው እነዚህ የደስታ ጊዜያት የማህበራዊ ትስስራችንን ይበልጥ ያጠናክሩታል።

ይሁን እንጂ በእነዚህ የደስታ ስፍራዎች ስንዝናና ትልቅ ጥንቃቄና ሃላፊነት ሊሰማን ይገባል። ለውበትና ለአረንጓዴ መሰረተ ልማቶቻችን ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግና ንጽህናቸውን መጠበቅ የሁላችንም ግዴታ ነው።

በተለይም ቆሻሻዎችን በየቦታው ከመጣል ተቆጥቦ በተዘጋጁላቸው ሳጥኖች ውስጥ ብቻ መጣል ያስፈልጋል። ፍጹም ስልጣኔ በተሞላበት መንገድ በተገቢው ቦታ መጸዳዳትና የህዝብ መገልገያዎችን በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል። እነዚህን የንጽህና ልማዶች በተግባር በማሳየት ለሌሎች ዜጎችና ለታዳጊዎች በጎ አርአያ መሆን መቻል አለብን።

ሌላውና እጅግ ወሳኝ የሆነው ነጥብ በበዓላት ወቅት ወደ ሀገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችን የምናስተናግድበት መንገድ ነው። በንግግራችን፣ በአቀባበላችንና በአጠቃላይ በድርጊታችን ጨዋነትን በማሳየት የሀገራችንን በጎ ገጽታ ለአለም ማስተዋወቅ ይኖርብናል።

እንግዶችን በፈገግታ መቀበል፣ ሲቸገሩ አቅጣጫና መረጃ በመስጠት መርዳት እና ታዋቂውን የኢትዮጵያዊያን የእንግዳ ተቀባይነት እሴት በተግባር ማሳየት የሁላችንም የዜግነት ድርሻ መሆን አለበት። ይህም የሀገራችንን የቱሪዝም ክፍለ ኢኮኖሚ ከማሳደጉም በላይ ዘላቂ ወዳጅነትን ይፈጥራል።

ባጠቃላይ፣ በዓላትን ስናከብር ውበትን ከአካባቢ ጥበቃ፣ ደስታን ደግሞ ከባህላዊ ጨዋነት ጋር በማጣመር መሆን አለበት። የአካባቢያችንን ንጽህና ጠብቀን፣ መሰረተ ልማቶችን ተንክብክበን እና እርስ በእርስም ሆነ ለእንግዶች ክብር ሰጥተን ስናከብር በዓላቱ ይበልጥ ትርጉም ይኖራቸዋል።
ውብና ንጹህ አካባቢ፣ ስልጡንና አርአያ የሚሆን ማህበረሰብ መፍጠር የምንችለው ከእያንዳንዳችን በሚጀምር መልካም ተግባር ብቻ ነው።




የመዲናችን የውበትና አረንጓዴ ገፅታ ለቱሪዝም ስበት ማዕከልነት እየዋለ ነዉ፡፡

ውበትና አረንጓዴነት የመዲናችን አዲስ አበባ መገለጫ ከመሆን ተሻግረው፣የቱሪስቶች ቀዳሚ የስበት ማዕከል እየሆኑ ይገኛሉ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተለያዩ ዘመናዊ ዲዛይኖች ተቀርጸው የለሙት የአረንጓዴ መሰረተ ልማቶችና ሌሎች የውበት ስራዎች የከተማዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።

እነዚህ ልማቶች ተራ መናፈሻዎች ሳይሆኑ፣ እያንዳንዳቸው የራሳቸው የሆነ ጥልቅ ታሪክና ጥበባዊ እሴት ይዘው የተገነቡ፣ በራሳቸው እንደ አዲስ ዘመን ቅርስ የሚጎበኙ ታላላቅ ማዕከላት ለመሆን በቅተዋል።

እነዚህ አረንጓዴ ስራዎች ለአይን ከሚሰጡት ማራኪ ውበት ባሻገር፣ እርስ በእርስ የተሳሰረ ዘላቂ ፋይዳ አላቸው። ለአካባቢ ጥበቃና ለስነ-ምህዳር ሚዛን መጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ከመሆናቸውም በላይ፣ የከተማዋን ነዋሪዎች አካላዊና አእምሯዊ ጤንነት የሚያድሱ የህዝብ መዝናኛዎች ናቸው።

ከዚህም ባለፈ፣ አዲስ አበባን በዓለም መድረክ ላይ በበጎ ገጽታ የሚያስተዋውቁ፣ የኢትዮጵያን የእድገትና የብልጽግና ጉዞ የሚያሳዩ ህያው አምባሳደሮች ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።

ይሁን እንጂ እነዚህ የተሰሩ ድንቅ የውበት ጸዳሎች የተሰጣቸውን ታላቅ ግልጋሎት ሳያቋርጡ፣ ውበታቸውንና ትኩስነታቸውን ጠብቀው እንዲቀጥሉ የህዝቡ የቅርብ ክትትልና እንክብካቤ ወሳኝ ነው።

እያንዳንዱ የከተማዋ ነዋሪ እነዚህን የጋራ ሀብቶች እንደ ገዛ ንብረቱ በመቁጠር፣ ከብክለትና ከጉዳት የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። የህዝቡ ንቁ ተሳትፎና ባለቤትነት ሲታከልበት ብቻ ነው መዲናችን አረንጓዴነቷን አጽንታ፣ የቱሪዝም ማማ ሆና መዝለቅ የምትችለው።






የመስቀልና የኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ አዲስ አበባን ውብና ማራኪ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበሩትን ታላላቅ የመስቀልና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላትን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር መዲናዋን ለእንግዶች ውብና ማራኪ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በተለይም በሁሉም የከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት የእንክብካቤና የተለያዩ የማስተካከያ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል።

የዚህ ሰፊ ንቅናቄ ዋና ዓላማ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ከሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበራዊ እሴቶች ጋር በማስተሳሰር የኅብረተሰቡን ንቁ ተሳትፎ ማረጋገጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ይህም የመዲናዋን ገጽታ በተሻለ መልክ በማጉላት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ቀጣይነትና የመጨረሻ ግብ ለማሳካት ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር ታምኖበታል።

እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት የከተማዋ የአረንጓዴና የውበት መሠረተ ልማቶች አበረታች ደረጃ ላይ በመድረሳቸው የውበትና የአረንጓዴ ሥራዎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የሚመጡ በርካታ ጎብኚዎች ወደ መዲናዋ ሲገቡ የሀገርን ገጽታ ከመገንባትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ከማሳደግ አንጻር ትልቅ መድረክ ሆነው እንደሚያገለግሉ ተመልክቷል።

የበዓላቱን መቃረብ ተከትሎ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት፣ በተቋሙ የአረንጓዴ ልማት እንክብካቤና የውበት ሥራዎች ላይ የአመራሮችና የሠራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተነግሯል።
በመሆኑም ሁሉም የሥራ ባልደረቦች እርስ በርስ በመቀናጀት፣ በዓላቱ ከተቋሙ ግብ ጋር በተጣጣመ መልኩ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎላቸው በውጤታማነት እንዲከበሩና እንዲጠናቀቁ በጋራ መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው ጥሪ ቀርቧል።






ኮሪደር ልማት--- ከከተማ ውበት በላይ

በአዲስ አበባ በፍጥነት እና በጥራት እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት፣ የከተሞችን መልክዓ-ምድር ከመቀየር ባሻገር፣ የዜጎችን የእለት ተእለት ህይወት እና የከተሞችን የወደፊት እጣ ፈንታ እየለወጠ ይገኛል።

የከተሞችን አሮጌ ገጽታ በመቀየር፣ ለኑሮና ለንግድ ምቹ፣ ማራኪ እና ለመጪው ትውልድ የሚመጥኑ ዘመናዊና ውብ ከተሞች እያደረጋቸው ይገኛል።

ልማቱ በከተሞች ለዘመናት ሳይሟሉ የቆዩትን የጎዳና ላይ መብራቶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የእግረኛ መንገዶችን፣ ልዩ የብስክሌት መስመሮችን እና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መተላለፊያዎችን፤ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮችን አካቶ የተሰራ ነው፡፡

ይህም ነዋሪዎች ያለስጋት እንዲንቀሳቀሱ ከማስቻሉም ባሻገር፤ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ምቹ ሜዳዎችና የህጻናት መጫዎቻዎች በመሰራታቸው በጤናውም ረገድ የራሱ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

የትራፊክ እና የእግረኛ መንገዶችን በማስፋት፣ የቴሌኮም፣ የመብራት እና የውሃ መስመሮችን በጥበብ በማስተጋበር የከተሞች የመሰረተ ልማት ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሯል። እንዲሁም የቆሻሻ ማስወገጃ አውታሮችን በአንድ ላይ አቀናጅቶ በመገንባት ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ አድርጓል።

አረንጓዴ ፓርኮች፣ የህዝብ መዝናኛዎች እና የኪነ-ጥበብ ስፍራዎች መስፋፋታቸውም ነዋሪዎች ማህበራዊ ትስስራቸውን እንዲያጠናክሩ እና ከከተማ ውጥረት እፎይታ እንዲያገኙ እያስቻለ ነው።

በልማቱ ወቅት ከተፈጠረው ሰፊ የስራ እድል ባሻገር፣ ከተሞች ውበት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያቸው በ24 ሰዓት እንዲንቀሳቀስ እድል ከፍቷል፡፡

የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ለአለም አቀፍ ዲፕሎማሲ፣ ስብሰባዎችና ለቱሪዝም ሳቢና ተመራጭ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ ገቢን እያሳደገ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ ያለፈውን ታሪኳን አክብራ፣ የዛሬውን ጉድለቷን ሞልታ፣ ነገን በብልጽግና እና በዘመናዊነት ለመቀበል እያደረገች ያለችውን ጉዞ ያሳያል።

በአጠቃላይም የኮሪደር ልማቱ የዜጎችን የኑሮ ጥራት ያሻሻለና ኢትዮጵያ በዘመናዊነት፣ በውበትና በብልፅግና ጎዳና እየገሰገሰች መሆኗን የሚያረጋግጥ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሲሆን፤ በመላው ሀገሪቱ ሲተገበር ደግሞ እንደ ሰንደቅ አላማ የኢትየጵያ አንዱ መለያ መሆኑ አይቀርም።





20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.