በኦሮሚያ ክልል የሽብር ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች እስከ 23 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ተቀጡ
ዓርብ ታህሳስ 11 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እና አካባቢው የሽብር ወንጀል በፈፀሙ ግለሰቦች ከ1 ዓመት ከ 6 ወር እስከ 23 ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ተፈርዶባቸዋል።
ግለሰቦቹ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን እና አካባቢው የሽብር ወንጀል ሲፈፅሙ በፀጥታ ኃይሎች በተካሄደው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ምርምራ ሲካሄድባቸው መቆየቱን ፖሊስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሽብር ጥቃት በፈፀሙ ግለሰቦች ላይ የሰው እና የሠነድ ማስረጃ ማቅረቡን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ በግለሰቦቹ ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ታሕሣሥ 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ወንጀለኞቹን ያስተምራል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል በሚል ውሳኔውን ማስተላለፉን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡