7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተ
ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ በሻራተን ሆቴል የመክፈቻ ዝግጅቱን ያደረገ ሲሆን እስከ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግሉ የቤት ልማት ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከገዥዎች፣ ከሻጮች፣ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን መሆኑ ተገልጿል።
በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ በተደረገው ውይይት ሪል ስቴቶች በታሰበው ፍጥነት እድገት እንዳያስመዘግቡ ተግዳሮቶች መኖራቸውን እና ከእነሱም ውስጥ የፋይናንስ እጥረት እና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት ህግ አለመኖር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም ለውጭ ሀገር ባንኮች ገበያው ክፍት መደረጉ መልካም ለውጥ ይዞ እንደሚመጣ እና ከውጪ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ መኖሩን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡
የመኖሪያ ቤት የዋጋ ንረትን የሚያስከትለው ሌላኛው ነገር የጥሬ እቃ እና የግንባታ እቃዎች የዋጋ ውድነት እንደሆነ እና ሁሉንም የማህበረሰብ አቅም ያማከለ ንድፍና ዋጋ ለማቅረብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የተለያዩ በግንባታ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ላይ መሰብሰብ ተጠቃሚው የተሻለ አማራጮችን እንዲያገኝ እንደሚያደርግ የካዝና ግሩፕ ሊቀመንበር አዲስ አለማየሁ ጠቁመዋል፡፡
ኤግዚቢሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመቅረፍ ወሳኝ የሆኑ ዘላቂ የግንባታ አሰራሮችን፣ ተመጣጣኝ የቤት መፍትሄዎችን እና የፋይናንስ አማራጮችን የሚያጎላ ነው የተባለለት ሲሆን ከመንግስት ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት በኤግዚቢሽኑ ተገኝተዋል፡፡