የትግራይ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸውን እንዳይማሩ ማደረጉ ልክ አለመሆኑን የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ
ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ከሃይማኖታዊ ስርዓት ውጪ በሆነ ሁኔታ ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ ስለተደረገው ክልከላ እና የመብት ጥሰት አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
በአክሱም ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ የተከለከሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ የሆኑ 160 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ችግር እንዲፈታ ካለፈው ጥቅምት 2017 ጀምሮ የተለያዩ ጥረቶች እንዳደረገ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡
ትምህርት ቤቱ በያዝነው ሳምንት የትግራይ ትምህርት ቢሮ አዲስ ህግ እና ደንብ ባልወጣበት ሁኔታ ተማሪዎቹ ሂጃብ ለብሰው ትምህርታቸው እንዳይማሩ መደረጉ ልክ እንዳልሆነ አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ ባለመቀበል ተማሪዎቹ በማስፈራራት እና በማሰር ከእውቀት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉ ምክር ቤቱ አመላክቷል፡፡
በመግለጫውም የሂጃብ ክልከላው በህገ-መንግስት የተቀመጡ የጋራ እና የግል መብቶች የሚፃረር ፣ በትምህርት ሚንስቴር እና በክልሉ መከበር ያለባቸው ደንቦች የጣሰ ነው ብሏል፡፡
በመሆኑም በትምህርት ሚንስቴር ደንብ ቁጥር -6 ንኡስ ቁጥር -3 ሂጃብ መልበስ እንደሚፈቅድ በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ እና ትግራይ አሁን ባለችበት ፓለቲካዊ ቀውስ በሃይማኖት ምክንያት ሌላ ቀውስ መጨመር ተገቢ ስላልሆነ ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመለስልን ሲል ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡
በተጨማሪም ጦርነቱ ምክንያት ከእውቀት መአድ ርቀው የነበሩ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ እንዲበረታቱ የሚገባቸው ሙስሊም ሴቶች ማበረታታት ሲገባ ሂጃብ በመልበሳቸው ብቻ ከትምህርት ገበታ መከልከል ፍፁም ኢ-ህጋዊ እና ኢ-ፍትሃዊ ተግባር መሆኑን አሳስቧል፡፡
በመጨረሻም ፍትሃዊ ጥያቄው በሦስት ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የክልሉ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ከህዝበ ሙስሊሙ ጋር በመምከር በቀጣይ የሚወስዳቸው ሰላማዊ የትግል እርምጃዎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡